Directives

Directives and Guidelines of Ethiopian Civil Service Agency

በኮንትራት/ በጊዜያዊነት በፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚገኙ ሠራተኞችን ቋሚ ለማድረግ የወጣ የአፈጻጸም መመሪያ

pdf

የፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ስለሚቀጠሩበት እና ስለሚተዳደሩበት አጠቃላይ አሰራር በአዋጁ ቁጥር 515/99 በዝርዝር መደንገጉ ይታወቃል፡፡ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 1 የመንግስት ሠራተኛ ማለት በፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው መሆኑን በግልጽ ተመልክቷል፡፡ በሌላም በኩል በአዋጁ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 22 ላይ ጊዜያዊ ሠራተኛ ማለት በመንግስት መ/ቤት ውስጥ የዘላቂነት ባህርይ በሌለው ሥራ ወይም ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ለአጭር ጊዜ የሚቀጠር እና ሥራው ሲጠናቀቅ የሚሰናበት መሆኑ ግልጽ ቢሆንም በፌዴራል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ከሚታዩ ያልተስተካከሉ የቅጥር አፈጻጸም አሠራሮች ውስጥ የኮንትራት/ ጊዜያዊ ቅጥር ዋነኛው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ አሠራር በመንግሥት የበጀት አጠቃቀምና በዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ ከመሆኑም ባሻገር ሰራተኞቹ ዘላቂነት ባላቸው የተቋሙ ሥራ መደቦች ላይ በመቀጠራቸው ይኸው የኮንትራት ውል ለረዥም ዓመታት እየተንከባለለ መቆጣጠር እማይቻልበት ደረጃ ከመድረሱም ባሻገር አሁን ያለው በእቅድ ያለመመራት የሰው ኃይል ቅጥር ችግር የሚቀጥል ከሆነ በመንግስትና በዜጐች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል እንዲሁም በየተቋሙ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች የሚቆዩት ቋሚ ሥራ እስኪያገኙ ድረስ ብቻ በመሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሰው ኃይል ልማት ማረጋገጥ ስለማያስችል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ችግሩ መፍትሄ ማግኘት እንዳለበት በመንግስት ታምኖበታል፡፡

በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ህዳር 18 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በቁጥር መ8ዐ- 839/1 በተጻፈ ደብዳቤ ዘላቂነት ባለውና በተመደበ የሥራ መደብ ላይ በኮንትራት/በጊዜያዊነት/ በፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው ያልተቋረጠ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ሠራተኞች በክፍት የቋሚ የሥራ መደቦች ላይ በቋሚነት እንዲመደቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ማንኛውም የፌዴራል መንግስት መሥሪያ ቤት ይህ መመሪያ እስከተላለፈበት ቀን ድረስ ዘላቂነት ባለውና በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በተመደበ የሥራ ደረጃ ላይ በኮንትራት/በጊዜያዊነት

ቀጥሮ ሲያሰራቸው የነበሩ ሠራተኞችን በመለየት፣

ሀ/ ቋሚ ምደባ ከመከናወኑ በፊት በስሩ የሚገኙና ይህ መመሪያ የሚመለከታቸውን የኮንትራት/ጊዜያዊ ሠራተኞችን ዝርዝር እና ሌሎች ሁኔታዎች ከዚህ መመሪያ ጋር ተያይዞ በተላከው ቅጽ ላይ በመሙላት ለሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር እንዲላክ፣

ለ/ የጊዜያዊ/የኮንትራት ሠራተኞቹ ቋሚ የመንግስት ሠራተኛነት በተቋሙ ውስጥ ለመቀጠል ፍላጐት ያላቸው መሆኑ ተረጋግጦ የቅጥር ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ ሠራተኞቹ በፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች የተፈላጊ ችሎታዎች መመሪያ መሠረት በኮንትራት/በጊዜያዊነት ተቀጥረው ሲያገለግሉ ለነበረበት የሥራ ደረጃ ዝቅተኛውን የተፈላጊ ችሎታ ማሟላታቸውን እየተረጋገጠ በዚሁ የሥራ መደብ ላይ መመሪያው ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ቋሚ እንዲሆኑ፣

ሐ. ቋሚ የመንግስት ሠራተኛ ሆነው መቀጠል የማይፈልጉ ጊዜያዊ/ኮንትራት ሠራተኞች ይህ መመሪያ በተላለፈበት አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውላቸው ተቋርጦ እንዲሰናበቱ ፡፡

መ. ከጊዜያዊ/ከኮንትራት ወደ ቋሚ የመንግስት ሠራተኝነት ለመቀጠር የተስማሙ ሠራተኞች በተቋሙ የሚመደቡበት /የሚደለደሉት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

 1. ተቋሙ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት አከናውኖ አዲስ ድርጅታዊ መዋቅር አጥንቶ አጠቃላይ የሠራተኛ ድልድል የሚያካሂድበት ደረጃ ላይ ካለ ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር ተወዳድረው በሚያሟሉበት የሥራ ደረጃ ይመደባሉ፡፡
 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ቢኖርም ቋሚ ሰራተኛና ጊዚያዊ/ኮንትራት ሰራተኛ ተወዳድረው እኩል ነጥብ ካገኙ ቋሚ ሰራተኛው ቅድሚያ ይደለደላል፡፡
 3. መሥሪያ ቤቱ በአዲስ መዋቅር ሠራተኞችን ደልድሎ ያጠናቀቀ ሆኖ ባሉት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚያገለግሉት በጊዜያዊነት/በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ከሆኑ አጠቃላይ የሠራተኞች እንደገና ድልድል ማድረግ ሳያስፈልግ ጊዜያዊ/ኮንትራት ሠራተኞቹ ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገው ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ይመደባሉ፡፡
 4. ከፍ ሲል በፊደል ‘ሀ’ የተጠቀሰው ቢኖርም በተመሳሳይ የሥራ መደቦች ላይ ያሉ የኮንትራት ሠራተኞችን ቋሚ በማድረጉ ሂደት የሠራተኞች ቁጥር ከሥራ መደቦች ቁጥር የበለጠ ከሆነ ሠራተኞችን በማወዳደር ብልጫ ያገኙት በስራ መደቡ ላይ በቋሚነት እንዲቀጠሩ ይደረጋል፣
 5. በኮንትራት ቅጥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ ወይም ዝቅ የለ ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ካሉ በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ለሥራ ደረጃው የተፈቀደው ደመወዝ በቋሚነት ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ይከፈላቸዋል፡፡
 6. በቋሚነት እንዲቀጠሩ የተደረጉ የኮንትራት/ጊዜያዊ ሠራተኞች አገልግሎታቸው ለጡረታ የሚታሰብላቸው ቋሚ የመንግስት ሠራተኛ እንዲሆኑ ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሆን፣
 7. ሠራተኞቹ ቀደም ሲል በሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቋሚነት ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩ ከሆነ አገልግሎታቸው ከዚህ በኋላ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር እየተደመረ እንዲያዝላቸው፣

ሠ/ በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ባልተመደበና ዘላቂነት በሌለው የሥራ መደብ ላይ በኮንትራት/በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩ ሠራተኞች ቅጥር እንዲቋረጥ ሆኖ በአስቸኳይ እንዲሰናበቱ፣

ረ/ በኘሮጀክት የሚፈፀም የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር ቀደም ሲል በነበረው አሠራር እንዲቀጥል፣ እንዲደረግና አፈጻጸሙ በአስቸኳይ እንዲገለጽልን እያሳሰብን፣ ይህ መመሪያ ለአንድ ጊዜ አፈፃፀም ብቻ የሚያገለግል ሲሆን ከየካቲት 30/2005 ዓ.ም በኋላ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ ከዚህ በኋላ በማንኛውም የፌዴራል መንግስት መሥ/ቤት እጅግ አስፈላጊ ለሆነና ለአጭር ጊዜ ብቻ የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር መፈፀም አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ ጥያቄው በቅድሚያ ለመሥሪያ ቤታችን እየቀረበ ተቀባይነት ማግኘቱ መረጋገጥ ያለበት መሆኑን እየገለጽን፣ ከዚህ ውጭ በማንኛውም መልኩ የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር ፈጽሞ የተገኘ የሥራ ኃላፊ በሕጉ መሠረት ተጠያቂ እንደሚደረግ እናስታውቃለን፡፡

Pages: 1 2 3

10 replies »

 1. Thank you for your effort.However, they are not updated. I was looking for Ethiopian civil service directive 3/2012 on per diem?

 2. በጣም ደስ የሚል መረጃ ነው ምስጋናዬ ከልብ ነው ነገር ግን ተፈፃሚነቱ እስከ ምን ድረስ ነው። በእውነት ብዙ ማውራት የምፈልገው ነገር አለ ቦታውን ጠቁሙኝ።

 3. አዳዲሶቹ አዋጆች መመሪያዎች ቢካተቱልን( 1064/2010)
  ምስጋናው ዋሴ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ

 4. Dear Sir/Madam
  I would like to inform you Sivil Service promotion in our Zone(Arsi Asella)
  I am graduated From Ambo University By Natural Resource Management 2012 now i am Aseko Woreda about 25 km from Woreda.Every time if i heard Vaccancy I apply it and I haven’t succeed why because every year the requared No does not exceed 3 pleace by these condition the thing is hard on this I am from Remout and poor family so what can I do. If it is on Woreda level it is ok.

 5. first of all, thank you for the information you have furnishing to us, are very valuable, for now i have some question on the pdf file i have downloaded from your site “Circular on Proclamation No 515-1999 EC -Explanation of Federal Civil Service Agency”. on page 5, in the last paragraph refers about article 45/1/ of 515/1999 and also in the next page refers some regulation ‘….. 1/5…’ which talk about project transfer, i am a little confused and if this is clear, please can you provide me with that regulation, i am in need of it.
  Thank You in advance

 6. some body responsible..pls come and see how we are being treated in BONGA HOSPITAL(kefa zone)

 7. please , please,come visite(invite) how sivil servants in wollega unversity are treated. UUUUUUUUU….we have many complicated things.

 8. Dear sir/madam
  I would like to inform about sivil service promotion ways in our woreda.
  I am employee in oromiya region,Arsi zone D/tijo woreda,i do have seven year service and doctor of veterinary medicine but in the name of merit i lost the place and salary i deserved.
  The woreda cabonet simply offer sivil coded placeses for the person they like with out any comptition with no legal post,i am sefering from injustice i also asked the biros from woreda upto region but yet get justice.what can i do,where can i go
  They emasculate my constitiutional right.
  Would you help me
  Thank you

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.