Directives

Directives and Guidelines of Ethiopian Civil Service Agency

በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች በሚገኙና ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ በዘላቂነት አገልግሎት መስጠት በሚያስገድዱ የሾፌር መደቦች ላይ ተመድበው ለሚሠሩ ሠራተኞች ልዩ አበል ስለሚፈቀድበት ሁኔታና ስለክፍያው መጠን ለመወሰን የወጣ መመሪያ

pdf

መግቢያ

አገራችንን ከድህነት በማላቀቅ በልማትና በዕድገት ጎዳና ለማራመድ በሚደረገው እልህ አስጨራሸ ትግል አመርቂ ስኬቶች እየተገኙ መሆኑ በገሀድ የሚታይ ዕውነታ ነው፡፡ ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመተግበርና በማስተባበር እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ነው፡፡ ሠራተኛውና የስራ ኃላፊዎች የስራ ሰዓት ሳይገድባቸው እንዲሁም ከማዕከል እስከ ገጠር ቀበሌዎች በአገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በመንቀሳቀስ የልማት ዕቅዶችን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ የሚያደርጉት እንቅስቃሴና የሚያሳዩት ተነሳሽነት መጪው ጊዜ ለአገራችንና ለህዝቦቻችን ብሩህ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ሆኖም መንግስት ያለውን ውሱን አቅም በልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ እያዋለ በተጓዳኝ ደግሞ የመክፈል አቅሙን ባገናዘበ መልኩ ለመንግስት ሠራተኛው የተለያዩ የደመወዝ ማስተካከያዎችና ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች በማድረግ ሠራተኛው በባለቤትነት ስሜትና በተነሳሽነት መንፈስ የልማት ዕቅዶቹን ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማበረታታት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳን የመንግስት ፍላጐትና አሁን ያለውን የመክፈል አቅም ለማጣጣም መፈተሸ ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በተለይ በዝቅተኛ የክፍያ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በተለይ የስራ ባህሪያቸው ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ ለመስራት የሚያስገድዳቸው በተወሰኑ የሾፌር የስራ መደቦች ላይ የሚያገለግሉ ሠራተኞች ለተለያዩ ተጨማሪ ወጪዎች መዳረጋቸውን በመግለጽ በተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረቡ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጥናት በማድረግ አስፈላጊው የማካካሻ ክፍያ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በመታመኑ ይህን መመሪያ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አዘጋጅቷል፡፡

 1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሾፌርነት ተቀጥረው የስራው ባህሪ በዘላቂነት ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ ስራ እንዲሰሩ የሚገደዱ ሾፌሮች ልዩ አበል ስለመክፈል የወጣ መመሪያ” ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

 1. ትርጓሜ

2.1. በዚህ መመሪያ “የፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች” በሚል የተጠቀሱት በአዋጅ 515/99 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚል በተሰጠው ትርጓሜ የተጠቀሱትን ይመለከታል፡፡

2.2. “የትርፍ ሰዓት ስራ” ማለት የመንግስት ሠራተኞችን የስራ ሰዓት ለመወሰን በወጣው አዋጅ 43/85 አንቀጽ 3 እና በፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 515/99 አንቀጽ 32 ከተመለከተው ውጨ የሚከናወን ስራ ነው፡፡

2.3. በዚህ መመሪያ “ሾፌር” ማለት በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ለማሽከርከር በቋሚነት ተቀጥሮ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችና ለቤተሰቦቻቸው፣ እንዲሁም ከመደበኛው የሥራ መግቢያ ሰዓት አስቀድመው ወደ ስራ ለሚሠማሩ ሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠተ ተመድቦ የሚያገለግል አሽከርካሪ ነው፡፡

2.4. “ልዩ አበል” ማለት በዚህ መመሪያ ተራ ቁጥር 2.3 ላይ በተገለጹ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች የስራውን ባህሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ክፍያ ነው፡፡

 1. የመመሪያው አስፈላጊነት ከሥራ ባህርያቸው የተነሳ በዘላቂነት ትርፍ ሰዓት እንዲሰሩ የሚገደዱ ሠራተኞች በየቀኑ ከ2-3 ሰዓት በበዓላት ቀናት ጭምር ተጨማሪ ሰዓት ይሰራሉ፡፡ ለዚህ አገልግሎታቸው አሁን በስራ ላይ ያለው የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ አፈጻጸም መመሪያ በወር ከ60 ሰዓት በላይ ለማሰራት የማይፈቅድ ከመሆኑም በላይ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ስሌት መሰረት ይፈጸም ቢባልም በመንግስት ላይ ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል በመሆኑ እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ይህም በወጪ ሲሰላ በዝቅተኛው የደመወዝ መጠን መደበኛው የሰዓት ደመወዙ በ1.5 ተባዝቶ ስለሚከፈል የወር ደመወዝ ብር 961 30 X 1.5 X 20 = ብር 960 ወጪ ይጠይቃል፡፡

በከፍተኛው የሾፌር የሥራ መደብ ደግሞ በመነሻ የወር ደመወዝ ብር 2298 30 X 1.5 X 20 = ብር 2298 የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሰወጪ ይጠይቃል፡፡ ይህም በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ወጪ ያስከትላል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር በተወሰነ ደረጃ ለመቀነስ የተወሰኑ ተቋማት በራሳቸው መንገድ ለመፍታት የተለያየ የአፈጻጸም እርምጃ ተግባራዊ እያደረጉ ቢሆኑም ይህ ችግር በሁሉም የፌደራል ተቋማት ወጥነት ባለው ሄኔታ ባለመፈታቱ ተመሳሳይ ስራ በሚሰሩ ሾፌሮች መካከል ልዩነት ከመፍጠሩም በላይ በተለያየ ጊዜ ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን የተለያዩ ተቋማትና ሰራተኞች እያነሱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ችግሩን በመቅረፍ ሠራተኞቹ በሙሉ ተነሳሽነት በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ ማገልገል እንዲችሉ በቁርጥ የተወሰነ የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ አበል መወሰን ተገቢነቱ ስለታመነበት ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

 1. የልዩ አበል ክፍያ አፈፃጸም

4.1. የልዩ አበል ክፍያ የሚፈጸመው በዚህ መመሪያ በተራ ቁጥር 2.3 በተዘረዘሩት የስራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሠሩ ሾፌሮች ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ ለስራ በሚፈለጉበት ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ለዚሁ አገልግሎት የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

4.2. የልዩ አበል ክፍያው የሚፈጸመው በየወሩ ሲሆን አከፋፈሉም፣

 1. በመንግስት ለተሾሙ የበላይ ኃላፊዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሾፌሮች የበላይ ኃላፊዎች በመደበኛው የሥራ ቀናት አምሽተው ከሥራ የሚወጡና ከሥራ መግቢያ ሰዓት በፊት ቀድመው ወደ ሥራ የሚገቡ ስለሆነ በዕረፍት ቀናትና በበዓላት ቀናት ጭምር በመሥራት ኃላፊነታቸውን የሚወጡ በመሆኑ ለእነዚህ የበላይ ኃላፊዎች አገልግሎች ለሚሰጡ ሾፌሮች በወር ብር 600 (ስድስት መቶ ብር)፣
 2. በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከመደበኛ ስራ ሰዓት በፊት ወደ ሥራ የሚገቡና አምሽተው የሚወጡ ሰራተኞችን የሚያገለግሉ የሰርቪስ ሾፌሮች፣ የዩኒቨርሲቲዎችና የፌዴራል ሆስፒታሎች አምቡላንስ አሽከርካሪዎች፣በመንግሥት ለተሾሙ የበላይ ኃላፊዎች ለቤተሰቦቻቸው አገልግሎት ለሚሰጡ ሾፌሮች ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ ለሚያበረክቱት ሥራ በወር ብር 4ዐዐ (አራት መቶ ብር) ይከፈላቸዋል፡፡
 3. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

5.1. ለፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ስራ ስለሚፈቀድባቸው ሁኔታዎችና ስለክፍያው መጠን እና የማካካሻ እረፍት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የወጣው መመሪያ በዚህ መመሪያ “ሾፌር” በሚል ትርጓሜ ስር በሚካተቱ ሠራተኞች ላይ ተግባራዊ አይደረግም፡፡

5.2. ማንኛውም በዚህ መመሪያ በተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ የተመደበና ልዩ አበል የሚከፈለው ሠራተኛ ለስራ በተፈለገ ጊዜ በስራ መደቡ ላይ መገኘት ግዴታ አለበት፡፡

5.3. በዚህ መመሪያ የተመለከቱ የስራ መደቦች ላይ ተመድቦ ልዩ አበል እየተከፈለው በማገልገል ላይ ያለ ሠራተኛ ከ15 ቀን በላይ ለሚያቆይ ለሌላ ስራ የተመደበ ከሆነ የልዩ አበል ክፍያው ተቋርጦ በምትኩ በጊዜያዊነት ለተመደበ ሾፌር እንዲከፈል መደረግ አለበት፡፡

5.4. ከፍ ሲል በተራ ቁጥር 4.3 የተገለጸው ቢኖርም የልዩ አበል ተጠቃሚ የሆነው ሠራተኛ ከ15 ቀን በታች ለሆነ ጊዜ በሌላ ስራ የተመደበ ከሆነ የአበል ክፍያው አይቋረጥም፡፡ ሆኖም በምትኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የተመደበው ሠራተኛ አገልግሎት የሰጠባቸው ቀናት በትርፍ ሰዓት ስሌት ታስቦ እንዲከፈል መደረግ አለበት፡፡

5.5. ቀደም ሲል ሀምሌ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. በቁጥር መ30/ጠ13/36/815 በተላለፈ መመሪያ ለመንግስት ተሿሚዎች ለተመደቡ ሾፌሮች ተፈቅዶ የነበረው 70 ብር አበል በዚህ ተሽሯል፡፡

5.6. በተለያዩ ተቋማት ይከፈሉ የነበሩ የተወሰኑ የሙያ አበል፣ የትርፍ ሰዓት አበል እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በዚህ መመሪያ ለተካተቱ ሠራተኞች ይህ መመሪያ ከወጣ ጀምሮ ተፈጻሚ ማድረግ አይቻልም፡፡

 1. መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ ይህ መመሪያ ከየካቲት 1/2007 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር

Pages: 1 2 3

10 replies »

 1. Thank you for your effort.However, they are not updated. I was looking for Ethiopian civil service directive 3/2012 on per diem?

 2. በጣም ደስ የሚል መረጃ ነው ምስጋናዬ ከልብ ነው ነገር ግን ተፈፃሚነቱ እስከ ምን ድረስ ነው። በእውነት ብዙ ማውራት የምፈልገው ነገር አለ ቦታውን ጠቁሙኝ።

 3. አዳዲሶቹ አዋጆች መመሪያዎች ቢካተቱልን( 1064/2010)
  ምስጋናው ዋሴ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ

 4. Dear Sir/Madam
  I would like to inform you Sivil Service promotion in our Zone(Arsi Asella)
  I am graduated From Ambo University By Natural Resource Management 2012 now i am Aseko Woreda about 25 km from Woreda.Every time if i heard Vaccancy I apply it and I haven’t succeed why because every year the requared No does not exceed 3 pleace by these condition the thing is hard on this I am from Remout and poor family so what can I do. If it is on Woreda level it is ok.

 5. first of all, thank you for the information you have furnishing to us, are very valuable, for now i have some question on the pdf file i have downloaded from your site “Circular on Proclamation No 515-1999 EC -Explanation of Federal Civil Service Agency”. on page 5, in the last paragraph refers about article 45/1/ of 515/1999 and also in the next page refers some regulation ‘….. 1/5…’ which talk about project transfer, i am a little confused and if this is clear, please can you provide me with that regulation, i am in need of it.
  Thank You in advance

 6. some body responsible..pls come and see how we are being treated in BONGA HOSPITAL(kefa zone)

 7. please , please,come visite(invite) how sivil servants in wollega unversity are treated. UUUUUUUUU….we have many complicated things.

 8. Dear sir/madam
  I would like to inform about sivil service promotion ways in our woreda.
  I am employee in oromiya region,Arsi zone D/tijo woreda,i do have seven year service and doctor of veterinary medicine but in the name of merit i lost the place and salary i deserved.
  The woreda cabonet simply offer sivil coded placeses for the person they like with out any comptition with no legal post,i am sefering from injustice i also asked the biros from woreda upto region but yet get justice.what can i do,where can i go
  They emasculate my constitiutional right.
  Would you help me
  Thank you

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.