Advertisements
//
you're reading...
Uncategorized

የችሎት ገጠመኞች እና ቀልዶች


የችሎት ገጠመኞች

በለጬ በችሎት

በአንድ የቀለብ ይቆረጥልኝ ክርክር ዳኛው የተጠሪን የገቢ መጠን ለማጣራት ስራውን ይጠይቁታል፡፡
“ስራህ ምንድነው?” እሱም “ጫት እሸጣለው፡፡ በለጬ ጫት እሸጣለው፡፡” ዳኛው የገቢውን መጠን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት “አንድ እስር በለጬ ጫት በስንት ብር ይሸጣል?” ሲሉ ጥያቄ ያቀርቡለታል፡፡ እሱም መቼም ዳኛው የበለጬን የመሸጫ ዋጋ አያውቁም በሚል ግምት “40 ብር!” ብሎ ሲናገር ዳኛው የጥያቄውን እንደምታ ባለመረዳት “አንተ! በችሎት ትዋሻለህ?” በለጬ 60 ብር አይደለም?” በማለት አፋጠውታል፡፡

ኮንስታብልና ኮብልስቶን

በአካል ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል ምስክሩ የምስክርነት ቃሉን እየሰጠ ነው፡፡ በምስርነቱ መሐል “…እና ተከሳሹ በኮንስታብል አናቱን ሲለው መሬት ላይ ተፈጠፈጠ..” በማለት ሲናገር ዳኛው አቋረጡትና “በኮብልስቶን ለማለት ፈልገህ ነው? ኮንስታብል እኮ ፖሊስ ነው፡፡”
ምስክር— “ያው ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡”

የሞተ ነገር

የከሳሽ ጠበቃ በስር ፍርድ ቤት በተወሰነው ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለበላይ ፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡ ሆኖም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጸናው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በድጋሚ ይግባኝ ማለት አይቻልም፡፡ የቀረችው አንዲት ጠባብ መንገድ “መሰረታዊ የህግ ስህተት አለ” ብሎ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ማቅረብ ብቻ ነው፡፡ የሰበር አቤቱታ ቀርቦ ተቀባይነት ካጣ ነገሩ ተሰበረ አለቀ ደቀቀ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ ካልተነሳ በቀር ወዴትም መሄድ አይቻልም፡፡ ጠበቃው የሰበር አቤቱታውን ፅፎ አቀረበ፡፡ በሰበር የሚቀርብ አቤቱታ ወደ ዋናው ክርክር ሳይገባ መልስ ሰጭ ሳይጠራ ወዲውኑ “አያስቀርብም!” ተብሎ ሊዘጋ ይችላል፡፡ “አያስቀርብም!” ከተባለ ነገሩ ሞተ ማለት ነው፡፡ የመጨረሻ ዕድሉን በጉጉት የሚጠባበቀው ጠበቃ በቀጠሮው ቀን ሲቀርብ የፈራው አልቀረ የሰበር አቤቱታው “አያስቀርብም!” ተባለ፡፡ በመጨረሻም ዳኛው “መዝገቡ ተዘግቷል! ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ” ብለው መዝገቡን ዘጉ፡፡ ጠበቃው ግን እጅ ነስቶ ዝም ብሎ ከመውጣት ይልቅ አንዲት ነገር ተናግሮ ተንፈስ ማለት ስለፈለገ “የተከበረው ፍርድ ቤት መቼ ነው የሚከፈተው?” ብሎ በመጠየቅ ዳኞቹንም ራሱንም ዘና አድርጎ ወጥቷል፡፡

ክቡር ዳኛ
አንድ ተከራካሪ በችሎት ቆሞ ዳኛው ሓሳቡን እንዲረዱለት በተደጋጋሚ “ክቡር ፍርድ ቤት! ክቡር ፍርድ ቤት!” እያለ አቤቱታውን ያሰማል፡፡ አሁንም ባለማቋረጥ “ክቡር ፍርድ ቤት!” ብሎ ሲጀምር ትዕግስት ያጡት ዳኛ “እባክህ ክቡር ፍርድ ቤት! ክቡር ፍርድ ቤት! እያልክ ፍርድ ቤቱን አታሰልቸው፡፡” ይሉታል፡፡ የልቡ ያልደረሰለት ተከራካሪ ግን አነጋገሩን ቀይሮ “ክቡር ዳኛ! ክቡር ዳኛ!” ማለት ሲጀምር ዳኛው “ደሞ ወደእኔ መጣህ?” ብለው ሲያፋጥጡት እንደገና ተስፋ በመቁረጥ ስሜት “ኧረ በእግዚአብሔር!” ማለት ጀመረ:: በመጨረሻ ዳኛው “!እንዴ ደሞ ብለህ ብለህ ወደእሱ ሄድክ?” በማለት ለዛ በተሞላበት መልኩ እንዲረጋጋ አድርገውታል፡፡

የችሎት ቀልዶች

ተከሳሽ– “ክቡር ፍርድ ቤት ሌላ ተከላካይ ጠበቃ እንዲሾምልኝ እጠይቃለሁ፡፡”
ዳኛ– “ምንድነው ምክንያትህ?”
ተከሳሽ– “ይሄኛው ተከላካይ ጠበቃ የኔን ጉዳይ ችላ ብሎታል፡፡”
ዳኛው ወደ ተከላካይ ጠበቃ ዞረው “እህ! ለተከሳሹ ቅሬታ የምትለው ነገር አለህ?”
ተከላካይ ጠበቃ– “ኧ!? ምን አሉኝ? ይቅርታ ጌታዬ እየሰማሁ አልነበረም::”
* * *
ዳኛው ተከሳሹን “ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ይጠይቁታል::
ተከሳሽ –“አይ በራሴ ብከራከር እመርጣለሁ፡፡ የቀረበብኝ ክስ እኮ በጣም ከባድ ነው!”
* * *
በአንድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ዐቃቤ ህጉ ዳኛውን “ጌታዬ ይህ ድርጊት የተፈጸመው ተስተናጋጅ ጢም ብሎ በሞላበት ሬስቶራንት ውስጥ ነው፡፡” ብሎ መናገር ሲጀምር በነገሩ የተደመሙት ዳኛ “በእኔ ተሞክሮ ግን ይህን መሰል ድርጊቶች የሚፈጸሙት ተስተናጋጅ በሌለበትና ሬስቶራንቱ ዝግ በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡” ሲሉት ዐቃቤ ህጉ ነገረኛ ቢጤ ነበረና “አይ ጌታዬ! እኔ እንኳን እንደዛ ዐይነት ተሞክሮ የለኝም!” በማለት የተከበሩት ዳኛ ላይ አላግጦባቸዋል፡፡
* * *
አንድ ሰው ኒዮርክ ከተማ ውስጥ በሐሰት ጠበቃ ነኝ እያለ በማታለል በፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከቀረበ በኋላ ተደርሶበት በፈፀመው የማጭበርበር ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ ተብሎ ዘብጥያ ይወርዳል፡፡ ታሪኩ በእርግጥ ያጋጠመ ሲሆን በወቅቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ ታዲያ በየቀኑ በእሳቸው ፊት ሲቀርብ አንዴም ያልጠረጠሩት ዳኛ “ጠበቃ እንዳልሆነ መጠርጠር ነበረብኝ፡፡ ሁል ጊዜ ቀጠሮ አክባሪና ትሁት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
* * *
ዳኛው የተምታታ ክርክር እያቀረበ ሃሳቡ አልጨበጥ ያላቸውን ጠበቃ “ያንተን ክርክር ጭራውን እንኳን ለመያዝ አቅቶኛል፡፡ በአንዱ ጆሮ ገብቶ በሌላኛው ይወጣል” ይሉታል፡፡ ጠበቃውም የሚሸነፍ ዓይነት አልነበረምና “ጌታዬ በመሀል ሆኖ የሚያቆመው ነገር ምን አለ?” ሲል መልሶላቸዋል፡፡
* * *
ከግራ ወደቀኝ እየተመላለሰ ባለማቋረጥ ለረጅም ጊዜ ክርክሩን በማቅረብ ላይ ያለ አንድ ሞቅ ያለው ጠበቃ በወሬው መሐል ቆም ብሎ “እየተከተሉኝ ነው ጌታዬ?” ሲል ዳኛውን ይጠይቃቸዋል፡፡ ዳኛውም “አዎ በቅርበት እተከተልኩህ ነው፡፡ ግን ግራ የገባኝ ነገር ወዴት ነው የምትሄደው?” በማለት መልሰው በነገር ጠቅ አድርገውታል፡፡

Advertisements

About Abrham Yohannes

Abrham Yohannes Hailu Licensed Lawyer & Consultant

Discussion

9 thoughts on “የችሎት ገጠመኞች እና ቀልዶች

 1. Its’ good…!!

  Like

  Posted by aberatekle | January 9, 2017, 12:05 pm
 2. this is good

  Like

  Posted by mamo | March 2, 2016, 8:03 am
 3. Wow it is good!!!

  Like

  Posted by Manyazewal Alemayehu | July 27, 2015, 11:14 am
 4. Thank you

  Like

  Posted by Alelign Asra | July 23, 2015, 2:40 pm
 5. Abresh I was learn in haromya uni.u are my teacher .I am proud to keep it ur fun.

  Like

  Posted by Habtamu kassa | July 6, 2015, 4:24 pm
 6. Thank you Abresh. Be Blessed!

  Like

  Posted by Getachew Adera | July 6, 2015, 12:13 pm
 7. I really like to express my appreciation !

  Zenna Debassu

  Like

  Posted by Zenna Debassu | July 2, 2015, 6:45 pm
 8. Abrish
  u made me laugh alone
  thanks bro for sharing ur time to make us fun in this worisome nation.

  Like

  Posted by Yonas | July 2, 2015, 5:11 pm
 9. Thanks man, good to laugh in the morning,

  Like

  Posted by yared, | July 1, 2015, 5:17 am

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

Advertisements

Enter your email address to subscribe to this blog and receive notifications of new posts by email.

Join 12,118 other followers

Follow Ethiopian Legal Brief on WordPress.com
%d bloggers like this: