Articles

የአስተዳደር ህግ አስፈላጊነት

የአስተዳደር ህግ ባለሙያዎች የአስተዳደር ህግን አስፈላጊነት ሲያስረግጡ “የአስተዳደር ህግ ባይኖር ኖሮ ልንፈጥረው ይገባ ነበር፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ ጥማት የሁሉም ዜጋ ችግር እንደመሆኑ በተለይ በኛ አገር የአባባሉ ትክክለኛት ከተገቢ ጥራጣሬ በላይ ነው፡፡ በህንዳዊ የአስተዳደር ህግ ምሁር አይ.ፒ. ማሴይ “የአስተዳደር ህግ” መጽሐፍ ላይ መግቢያቸውን ያሰፈሩትና ራሳቸውም ታዋቂ ምሁርና ዳኛ የሆኑት ባክሲ በአንጽኦት እንደገለጹት “የአንድን አገር የአስተዳደር ህግ ማወቅ የዛችን አገር አጠቃላይ የህግ ስርዓት ማወቅ ነው፡፡”

የአስተዳደር ህግ ተግባራቱ ብዙ ሚናውም እጥፍ ድርብ ነው፡፡ ተልዕኮው የመንግስት ስልጣን ከግለሰቦች መብትና ነፃነት ጋር ማስታረቅ በዚህም የአስተዳደር ፍትሕን እውን ማድረግ ነው፡፡ በአንድ በኩል የመንግስት ባለስልጣናትና የአስተዳደር መስሪያ ቤት በህግ የተሰጣቸውን የስልጣን ገደብ አልፈው እንዳይሄዱ በመቆጣጠር የህግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብት እንዲከበር በማድረግ ህገ መንግስቱን በተግባር ያስፈጽማል፡፡ በሌላ በኩል የመንግስት አስተዳደር የሚመራበትን መርህና ደንብ በዝርዝር በማስቀመጥ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን አዎንታዊ ፋይዳ ያበረክታል፡፡

ስለሆነም ህገ መንግስታዊ ስርዓት በተዘረጋበት ዲሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ ህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ መርሆች እውን ይሆኑ ዘንድ ሁሉን አቀፍና የዳበረ የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ህግ ስርዓት ሊኖር ይገባል፡፡

የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ዓላማና ተግባር ስልጣንን መቆጣጠር ስለመሆኑ በመስኩ ምሁራን ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም በዚህ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ እንደ ብዙዎች የአስተዳደር ህግ ሊቃውንት የአስተዳደር ህግ ዋነኛ ግብ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡፡

. ስልጣንን መቆጣጠር (control function)

የአስተዳደር ህግ ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካልና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ባለስልጣናት ሌሎች ሹመኞች በህግ ተለይቶ የተሰጣቸው ስልጣን አልፈው እንዳይሄዱና ህጋዊ ስልጣናቸውንም አለአግባብ እንዳይገለገሉበት ለመቆጣጠር የሚያስችለን የህግ ክፍል ነው፡፡ መንግስት በተለይም ስራ አስፈፃሚ ስልጣኑን በህገ ወጥ መንገድ አለ አግባብ እንዳይገለገል በመከላከል እንደ መገደቢያ መሳሪያነት ያገለግላል፡፡

. ግዴታን ማስፈፀም (የአስገዳጅነት ሚና) (command function)

የአስተዳደር ህግ ስልጣን በልኩና በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውል ከመቆጣጠር ባሻገር የአስተዳደር አካላት በህግ ተለይቶ የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲወጡ የሚገደዱበት ህግ ጭምር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ በሌለበት የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት ግዴታቸውን ተገደው የሚፈጽሙበት ማስገደጃ መንገድ አይኖርም፡፡ በሌላ አነጋገር ህጋዊ ግዴታ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ የውዴታ ግዴታ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡

. የአስተዳደር ፍትሕ ማስፈን

በየትኛውም ህግን ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና እርምጃዎች የህዝብ አመኔታና ተቀባይነት እንዲያገኙ ፍትሐዊነታቸው በተጨባጭ ሊታይ ይገባል፡፡ የአስተዳደር ህግ አይነተኛ ተልዕኮ የአስተዳደር ፍትህን ማስፈን ነው፡፡[1]

የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር ፍትሕን እውን ከማድረግ አንፃር ህጉ ስልጣን በመገልገል ሂደት ተፈጻሚ መሆን ያለባቸውን መርሆዎች፣ መሪ ደንቦችና ስነ ስርዓቶች በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ህገ-ወጥ እና ኢ-ፍትሐዊ አስተዳደራዊ ውሳኔ ወይም እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ስህተቱ ወይም ጉድለቱ በመደበኛ ፍርድ ቤት እና በአስተዳደር ፍርድ ቤቶች የሚታረምበትን ስርዓት በመዘርጋት ማንኛውም ጉዳት የደረሰበት ወገን ፍትህ እንዲጎናፀፍ ያደርጋል፡፡

. ግልጽነት፤ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ

የአስተዳደር ህግ በመንግስት አስተዳደር ስራ ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖርና የህዝብ ተሳትፎ እውን እንዲሆን ብሎም ተፈፃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ተግባራዊ መሳሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ የስልጣን ልኩ ሳይታወቅና ከልክ በላይ የሆነ ስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቱ ሳይቀመጥ ስለተጠያቂነት ማውራት የማይመስል ነገር ነው፡፡ ተጠያቂነትን እውን በማድረግ ረገድ የአስተዳደር ህግ የተለያዩ የስልጣን መቆጣጠሪያ ስልቶችን ይዘረጋል፡፡ የአስተዳደር ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን በህግ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ በተመሳሳይ መልኩ ዜጎች በደንብና መመሪያ አወጣጥ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ ለማስቻል አስገዳጅ ስነ- ስርዓት ደንቦችን በመዘርጋት የህዝብ ተሳትፎን በተግባር ያረጋግጣል፡፡

. ለተበደለ ወገን መፍትሔ መስጠት

የአስተዳደር ህግ ዜጎች ለደረሰባቸው በደል በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ መንገዶች አቤቱታ አቅርበው በአነስተኛ ወጪ እና በቀሉ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ስለ አስተዳደር ህግ በተደጋጋሚ ቢወራ አንጀት ጠብ የሚል፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ መፍትሔ እስከሌለ ድረስ ረብ የለሽነቱን ያጎላው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደውን ነገር የለም፡፡ የአስተዳደር ህጋቸው በዳበረ አገራት የመንግስት ባለስልጣናት በህዝብ ላይ ለሚፈፅሟቸው አስተዳደራዊ በደሎች በዝርዝር የተቀመጡ የመፍትሔ መንገዶች አሏቸው፡፡

በአንድ አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ እነዚህን ተግባራቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተወጥቷል ለማለት ከአገሪቱ የመንግስት አወቃቀር ስርዓት፤ ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ዕድገትና የአስተዳደር ህግ ተቋማት መዳበር ከግምት ውስጥ በማስገባት አንፃራዊ በሆነ መልኩ የሚለካ ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በአንድ አገር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ውጤታማና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የአስተዳደር ህግ ስርዓት አለ ለማለት ከሚከተሉት ሶስት ዋነኛ መርሆዎች አንፃር እየተመነዘረ መገምገም አለበት፡፡

የአስተዳደር ፍትሕ

አስተዳደራዊ በደል በፍርድ የሚታረምበትና አስተዳደራዊ ፍትሕ የሚገኝበት የፍርድ ሂደትና መንገድ እንዲሁም ተሞክሮ በአገራችን ውስጥ የተለመደና በግልጽ የሚታወቅ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ የአስተዳደር ህግ ልቡ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አስተዳደራዊ በደል አለቅጥ በተንሰራፋበት አገር ውስጥ የአስተዳደር ህግ ትንፋሽ ያጠረው ህላዌነቱ የሚያጠራጥር ህግ ነው፡፡ የከለላው መጠን የአስተዳደር ፍትህ ደረጃ አንጻራዊ መለኪያ ነው፡፡

የስራ አስፈፃሚው ተጠያቂነት

የዚህ መርህ ዋና አላማ ህግ የማስፈፀም ስልጣን ያለው አካል ለሚፈፅመው ድርጊት እና ለሚወስደው እርምጃ በህዝብ ፊት ተጠርቶ እንዲጠይቅና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማስገደድ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን የተቀበለ አካል ወይም ባለስልጣን የሚፈፅመው ድርጊት የህግ ድጋፍ ሊኖረው ይገባል፡፡ ስለሆነም ህግ አውጪው ፊት ተጠርቶ ቀርቦ ለህጋዊነቱ ማብራሪያ የሚሰጥበት ስርዓት ከሌለ በቀር ተጠያቂነት አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደሩ በዜጎች መብት ለሚያደረሰው ጉዳት በፍርድ ሂደት ለድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡

መልካም አስተዳደር

በዚህ መርህ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሁሉን አቀፍ ተቀባይነት ላገኙ መሪ ደንቦች መገዛት አለበት፡፡ እነዚህም የፍትሀዊነት ምክንያታዊነት፣ የሚዛናዊነትና የግልፅነት መርሆዎችን በዋንኛነት ያጠቃልላሉ፡፡ አስተዳደራዊ ውሳኔ በህጉ መሰረት መውሰዱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የውሳኔው መሰረት ከቅን ልቦና የመነጨ፣ ለባለጉዳዩ ግልፅ በሆነ አሰራርና መንገድ ያልተወሰደ ካልሆነ በስተቀር የመንግስት አስተዳደር ወደ መልካምነት ደረጃ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡ የአስተዳደር ህግ እነዚህን መርሆዎች እውን እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ የእድገት ደረጃ የአንድ አገር የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ጠቋሚ መለኪያ ነው ማለት እንችላለን፡፡

[1] R.S. French, Administrative Justice in Australian Administrative law, in Robin creyke & John mc millan(eds) Adminstrative Justice: the core and the fringe (Proceedings of the 1999 National Administrative law forum (Australia, Australian Institute of Administrative law Inc. 2000)

10 replies »

 1. Excuse me to ask as such…. the purpose of these question is to work the assignment which took from AAU, I need to get your suggestion. thank you for your …….

  1. ፌደራል ፍርድቤቶች የከተማ መሬት ግጪት ጉዳይ የመየት ስልጣን አላቼዉ?
  2. ፌደራል ፍርድቤቶች ለህዝብ ጥቅም ሲባል የተነሱ በለ ይዞታዎች እና በመንግስት መሀል የምነሱ ግጭቶች ለመየት ስልጣነቸዉ ምን ህማስላል?
  3. ለምንድናዉ ለኢዝብ ጥቅም ስባል የተነሱ በላ ይዞታዎች የአስታዳር ዉሳነ ስቀዋሙ የህግ እና የጭብጥ ፍሬ ናገር ለይ ይግባኝ የተካላከለዉ ?

 2. እጅግ በጣም አመሰግንሀለሁ። በጣም አስተማሪ መረጃዎችን እያካፈልከን ነው፣ ተባረክልኝ።

 3. Thanks Abresh!

  2017-02-02 17:49 GMT+03:00 Ethiopian Legal Brief :

  > Abrham Yohannes posted: “የአስተዳደር ህግ ባለሙያዎች የአስተዳደር ህግን አስፈላጊነት ሲያስረግጡ
  > “የአስተዳደር ህግ ባይኖር ኖሮ ልንፈጥረው ይገባ ነበር፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ ጥማት የሁሉም ዜጋ
  > ችግር እንደመሆኑ በተለይ በኛ አገር የአባባሉ ትክክለኛት ከተገቢ ጥራጣሬ በላይ ነው፡፡ በህንዳዊ የአስተዳደር ህግ ምሁር
  > አይ.ፒ. ማሴይ “የአስተዳደር ህግ” መጽሐፍ ላይ መግቢያቸውን ያሰፈሩትና ራሳቸውም ታዋቂ ምሁርና”
  >

 4. Nice ARTICLE my dear

  getu

  On Thu, Feb 2, 2017 at 5:50 PM, Ethiopian Legal Brief wrote:

  > [image: Boxbe] This message is eligible
  > for Automatic Cleanup! (comment-reply@wordpress.com) Add cleanup rule
  >
  > | More info
  >
  >
  > Abrham Yohannes posted: “የአስተዳደር ህግ ባለሙያዎች የአስተዳደር ህግን አስፈላጊነት ሲያስረግጡ
  > “የአስተዳደር ህግ ባይኖር ኖሮ ልንፈጥረው ይገባ ነበር፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ ጥማት የሁሉም ዜጋ
  > ችግር እንደመሆኑ በተለይ በኛ አገር የአባባሉ ትክክለኛት ከተገቢ ጥራጣሬ በላይ ነው፡፡ በህንዳዊ የአስተዳደር ህግ ምሁር
  > አይ.ፒ. ማሴይ “የአስተዳደር ህግ” መጽሐፍ ላይ መግቢያቸውን ያሰፈሩትና ራሳቸውም ታዋቂ ምሁርና”
  >

 5. Ato Abraham i am benefited from your professional writings on law.Please Ethiopia needs and require defined administrative law which is a good tool for problem solving for the country.Please send me some representative administrative laws of different countries and our draft law to me through my email destalorenso@yahoo.com. Thanks

 6. ኣብርሽየ እንዲህ ዓይነት በጣም ጠቃሚ ፅሑፍን ጀባ ስላልከን በጣም እናመሰግናለን።

 7. Really I thank you a lot since we lawyers in riches by your access to the
  soft copy on different legal areas via our email.This is very great!
  Abresh! I am in need of administrative law books, articles and the like on
  Administrative law rulemaking and adjudication process. please if you have
  would I get via sisoman2007@gmail.com.
  thank you in advance!

  2017-02-02 6:49 GMT-08:00 Ethiopian Legal Brief :

  > Abrham Yohannes posted: “የአስተዳደር ህግ ባለሙያዎች የአስተዳደር ህግን አስፈላጊነት ሲያስረግጡ
  > “የአስተዳደር ህግ ባይኖር ኖሮ ልንፈጥረው ይገባ ነበር፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የአስተዳደር ፍትሕ ጥማት የሁሉም ዜጋ
  > ችግር እንደመሆኑ በተለይ በኛ አገር የአባባሉ ትክክለኛት ከተገቢ ጥራጣሬ በላይ ነው፡፡ በህንዳዊ የአስተዳደር ህግ ምሁር
  > አይ.ፒ. ማሴይ “የአስተዳደር ህግ” መጽሐፍ ላይ መግቢያቸውን ያሰፈሩትና ራሳቸውም ታዋቂ ምሁርና”
  >

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.