ክሪሚናሊስቲክስ

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

ከ6 ወራት በፊት በመኪና /ባጃጅ/ አደጋ የተነሳ በእግሬ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከደረሰ ወዲህ ብሎጌን update አላደረግኩም፡፡ አሁን አገግሜያለው፡፡ ለጠየቃችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ፡፡

ከ6 ወራት ቆይታ በኋላ በዚህ ብሎግ ከሚዳሰሱ ጉዳዮች ትንሽ ወጣ ባለ ርዕስ ላይ የውይይት በር ለመክፈት ሀሳብ አለኝ፡፡ ለውይይት የመረጥኩት ርዕስ ክሪሚናሊስቲክ ወይም ደግሞ ሁላችንም በምናውቀው ቃል ፎረንሲክ ሳይንስ ነው፡፡ የዛሬው ጽሑፍ አጠቃላይ ስለ ሳይንሱ እና ለፍትሕ ስርዓቱ በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ መልካም ንባብ!

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

       ትርጓሜውና ይዘቱ

       የፎረንሲክ ሳይንስ መሰረታዊ ዕውቀት አስፈላጊነት

       ተሳስቶ ላለማሳሳት-የአስፈላጊነቱ ማሳያ

            የባሩድ ቅሪት በእጥበት ይለቃል?

            ወንጀል የተፈጸመበት የጦር መሳሪያ እንዴት ይታወቃል?

           የፖሊስ መግለጫ- ጉዳት አድራሹ ሽጉጥ ተለይቷል? 

ፋይዳው- ‘ከማዕከላዊ ወደ ላቦራቶሪ’

ፎረንሲክ ፓቶሎጂ /Forensic Pathology/

       ሞተናል የሚባለው መቼ ነው?      

ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

ትርጓሜውና ይዘቱ

እ.ኤ.አ. በ1248 ቻይና ውስጥ በሩዝ ማሳ ውስጥ ይሰሩ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል አንደኛው በስሎት ተወግቶ ተገደለ፡፡ የገዳዩን ማንነት ለማወቅ ሁሉም የማሳው ሰራተኞች ለስራ የተሰጣቸውን ማጭድ እንዲያመጡ ተደርጎ በረድፍ ተደረደሩ፡፡ ከተደረደሩት መካከል አንደኛዋን ማጭድ ዝንቦች ወረሯት፡፡ በዚህን ጊዜ ገዳዩ ወዲያውኑ ተናዘዘ፡፡ ዝንቦቹ ያረፉት ደም የነካው ማጭድ ላይ ነበር፡፡ (Bertino, 2012) በዚሁ ዓመት እዛው ቻይና ውስጥ የህክምና ዕውቀትን ለህግ ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚያደርግ የመጀመሪያው መጽሐፍ ተጻፈ፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ በቻይንኛ Xi Yuan Ji Lu በእንግሊዝኛ ትርጉሙ The Washing Away of Wrongs and Collected Cases of Injustice Rectified  በሚል የሚታወቅ ሲሆን ጸሐፊው ሰንግ ትዙ (Sung Tz’u) ይባላል፡፡ ‘የማጭዱ ገዳይ’ ታሪክ በመጽሐፉ ውስጥ ከተዘገቡት ፎረንሲክ ጠቀስ ታሪኮች መካከል አንደኛው ነው፡፡ (Siegel & Mirakovits, 2010) ይህ መጽሐፍ በፎረንሲክ ሳይንስ ዕድገት ውስጥ የመጀመሪያው የተሟላ የፎረንሲክ ሳይንስ ማኑዋል /manual/ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ (Stefoff, 2011)

ክሪሚናሊስቲክስ የፎረንሲክ ሳይንስን ለወንጀል ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚያደርግ ሳይንስ ነው፡፡ ቃሉ አንዳንዴ ከcriminology ጋር ይምታታል፡፡ ይሁን እንጂ criminology ወንጀል እና የወንጀል ባህርያትን የሚያጠና ማህበራዊ ሳይንስ እንደመሆኑ ሁለቱ ለየቅል ናቸው፡፡ (Fisher, Tilstone, & Woytowicz, 2009)

ለመሆኑ ፎረንሲክ ሳይንስ ምንድነው? ፎረንሲክ የሚለውን ቃል ብዙዎቻችን ሰምተነው እናውቃለን፡፡ ትክክለኛ ትርጓሜውን በተመለከተ ግን በብዙዎቻችን መረዳት ያለ አይመስልም፡፡ ለአንዳንዶች ፎረንሲክ ሳይንስ ሲባል የረቀቀና ጥቂት በሙያው የተካኑ ፖሊሶች ብቻ የሚረዱትና የሚጠቀሙበት ፖሊሳዊ ሳይንስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የፎረንሲክ ሳይንቲስት ለመሆን ፖሊስ ወይም መርማሪ መሆን አይጠይቅም፡፡ እንዲያውም ሳይንሱ በእግሩ እንዲቆም ያደረጉት የዘርፉ ፈር-ቀዳጆች አብዛኛዎቹ በፖሊስነት ሞያ ውስጥ አላለፉም፡፡

ፎረንሲክ ሳይንስ በአጭር አነጋገር ሳይንሳዊ ዘዴ በመጠቀም ከህግ አፈጻጸም የሚነጩ ጉዳዮችን ወይም ችግሮችን የሚፈታ ሳይንስ ማለት ነው፡፡ ሰፋ ባለ ትርጓሜው ለፍትሕ ስርዓት አገልግሎት የሚውል ማንኛውም ሳይንስ ሁሉ የፎረንሲክ ሳይንስ ነው፡፡ (Houck & Siegel, 2015) ከተፈጻሚነት አድማሱ አንጻር ሳይንሱ ለወንጀል ብቻ ሳይሆን ለፍትሐብሔር ጉዳዮችም ተግባር ላይ ይውላል፡፡ ሆኖም ሳይንሱ በጣም ጎልቶ የሚታየው ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነው በክሪሚናሊስቲክስ እና ፎረንሲክ ሳይንስ መካከል የረባ ልዩነት የለም፡፡ እንዲያውም ለአንዳንዶች ሁለቱም ተመሳሳይ ስያሜዎች ናቸው፡፡ (Stefoff, 2011)

‘fornesic’ የሚለው ቃል የመጣው forum ከሚል የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉም ህዝባዊ ወይም የህዝብ ማለት ነው፡፡ በጥንታዊ ሮማ ሴኔቱ በፎረም /ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ/ እየተገናኘ በፖለቲካና በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ክርክር /debate/ ያካሂድ ነበር፡፡ አሁን ድረስ በተለይ በአሜሪካ በህዝባዊ ክርክር /debate/ የሚወዳደሩ ተከራካሪ ቡድኖች /teams/ “forensics.” እየተባሉ ነው የሚጠሩት፡፡ (Houck,, 2007)

በነገራችን ላይ የመጀመሪያው የፎረንሲክ የሬሳ ምርመራ የተካሄደው እዛው ሮማ ውስጥ ነው፡፡ ጁሊየስ ቄሳር በጠላቶቹ 23 ጊዜ ተወግቶ ሲገደል አንቲሺየስ የተባለ ሐኪም የሬ ምርመራ ካደረገ በኋላ ቄሳርን ለሞት ያበቃችው የትኛዋ እንደሆነች ለመለየት ችሏል፡፡ (Evans, 2004) በፈረሲክ ሳይንስ ስር የሚታቀፉ ዘርፎች በጣም በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ዋና የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡

 • ክሪሚናሊስቲክስ /Criminalistics/
 • ባለስቲክስ (Ballistics/ የጦር መሳሪያ ምርመራ /Firearm examination/
 • ፎረንሲክ የአጥንት ምርመራ /Forensic Anthropology/
 • ፎረንሲክ የጥርስ ምርመራ / Forensic Odontology/
 • ፎረንሲክ የሞት እና ሬሳ ምርመራ / Forensic Pathology/
 • ፎረንሲክ ሳይኮሎጂ /Forensic Psycology/
 • ፎረንሲክ የነብሳት /insect/ ምርመራ /Forensic Entomology/
 • ፎረንሲክ አካውንቲንግ /Forensic Sccounting/
 • ፎረንሲክ የአደጋ ምርመራ / Forensic Engineering/
 • የመርዛማ ነገሮችና አደንዛዥ ፅፅ ምርመራ /Toxicology/
 • ፎረንሲክ ባዮሎጂ /የደም፤ የፈሳሽና ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ/ /Forensic Biology/
 • ፎረንሲክ ኬሚስትሪ /Forensic Chemistry/
 • የአሻራ ምርመራ / Ridgeology/
 • የሰነድ ምርመራ / Questioned Documents/
 • የወንጀል ስፍራ ምርመራ /Crime-Scene Investigation/
Pages: 1 2 3 4 5 6 7 8

13 replies »

 1. Sorry for the accident my honor teacher! Please can you tell me how I can get exit questions with their answers?

 2. you are the real resourced person, It so bad wish you speedy cure from injury.
  I was not browse the blogger for the last six months.

 3. Abrahiye sorry. Glory to God you get healed from the incident. Well come back my hero. Thanks for all.

 4. I am happy to hear that you are fine now. May God be with you. my educational background is not law but I used to follow your blogs, information and draft laws. I am benefited much out of this blog. hence, I hope you will continue helping us.
  Thank you so much

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.