የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማቋቋሚያ /ረቂቅ/ አዋጅ

ምዕራሶስት

የቦርዱ ዋና ጽህፈት ቤት፣

 1. የቦርዱ ጽህፈት ቤት

ቦርዱ በአንድ ዋና ኃላፊና በአንድ ምክትል ዋና ኃላፊ የሚመራ ጽህፈት ቤት ይኖረዋል

 1. የጽህፈት ቤቱ ኃላፊና ምክትል ኃላፊ አሰያየምና ተጠሪነት
 • የጽህፈት ቤቱ ኃላፊና ምክትል ኃላፊ ግልጽና አሳታፊ በሆነ የምልመላ ሂደት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 ለስራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመት የተመለከቱትን አግባብነት ያላቸው መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ተመርጠው በስራ አመራር ቦርዱሰብሳቢ አቅራቢነት በቦርዱ ይሰየማሉ፡፡
 • የጽህፈት ቤቱ ዋና ኃላፊ ተጠሪነቱ ለስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ ሲሆን የምክትል ሀላፊው ተጠሪነት ለፅሀፈት ቤቱ ዋና ሀላፊ ይሆናል፡፡
 1. የጽህፈት ቤቱ ዋና ኃላፊ ስልጣንና ተግባር

የጽህፈት ቤቱ ዋና ኃላፊ በስራ አመራር ቦርዱ እና በስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢበሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያና አቅጣጫ መሰረትየሚከተሉትን ስልጣንና ተግባራት ያከናውናል፡-

 • የቦርዱን የድጋፍ ሰጪ የስራ ዘርፍ በበላይ ሃላፊነት ይመራል፤
 • የቦርዱን ስልጣንና ተግባር አፈጻጸም ያሳልጣል፣ ያስተባብራል እንዲሁም ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፤
 • ከቦርዱ ሰብሳቢ ጋር በመመካከር የቦርዱን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል፤
 • የቦርዱን ቃለጉባኤና ሌሎች ሰነዶች በአግባቡ ይይዛል፤
 • የቦርዱ ውሳኔዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች እንዲተላለፉ ያደርጋል፤
 • በቦርዱ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ያለድምጽ በመሳተፍ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፤
 • ስለጽህፈት ቤቱ የስራ እንቅስቃሴ በየጊዜው ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ሰብሳቢ ያቀርባል፤
 • በቦርዱ ሰብሳቢ የሚሰጡትን ሌሎችተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ ስልጣንና ተግባር

የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሚከተሉት ስልጣንናተግባራትን ያከናውናል፡-

 • በዋና ሃላፊው ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
 • የጽህፈት ቤቱ ዋና ሃላፊ በሌለበት ጊዜ ሃላፊውን ተክቶ ይሰራል፡፡
 1. የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት
 • በሁሉም ክልሎች ምርጫ የሚያስተባብር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይቋቋማል፡፡
 • የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ቦርዱ በሚያወጣው መመርያ መሰረት ገለልተኛነታቸውና ሙያዊ ብቃታቸው ከተረጋገጠ የክልሉ ነዋሪዎች መካከል በቦርዱ ሰብሳቢ አቅራቢነት በቦርዱ ይሰየማሉ፡፡
 • ቦርዱ የክልሎችን የቆዳ ስፋት፣ የህቡን አሰፋፈርና የመራጮችን ብዛት መሰረት በማድረግ ለክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተጠሪ የሆኑ እንደ አግባብነቱ የዞን እና የምርጫ ክልልማስተባበሪያ በቋሚነት ሊያቋቁም ይችላል።
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) የተገለጹት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች ተግባር፤ሀላፊነትና አሰራር ቦርዱ በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
 1. የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተግባርና ሃላፊነት

እያንዳንዱ የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በስራ አመራር ቦርዱ እና በስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ እንዲሁም እንደ አግባብነቱ በቦርዱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያና አቅጣጫ መሰረትየሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል

 • በክልል ደረጃ የሚካሄደውን ምርጫ ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤
 • በስሩ የሚቋቋሙት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች ስለሚደራጁበት ሁኔታ ለቦርዱ ጽህፈት ቤት ሀሳብ ያቀርባል፤
 • ለምርጫ የሚያስፈልለጉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ለሚመለከታቸው ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶችና የምርጫ ክልልና ጣቢያዎች በወቅቱ መድረሳቸውን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፤
 • ከቦርዱና የስራ ሂደቱ ሀላፊነት ያለው የስራ አመራር ቦርድ አባል በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የስነዜጋና የመራጮች ትምህርት ይሰጣል፣ያስተባብራል፤
 • የመራጮች አመዘጋገብ፣ የእጩዎች አቀራረብና የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እየተካሄደ መሆኑን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፤
 • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የሚነሱትን ቅሬታዎችና ተቃውሞዎች በክልል ደረጃ እየመረመረ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይወስናል፤
 • የክልሉን የምርጫ ሂደትና ውጤት በሚመለከት ለቦርዱ ጽህፈት ቤት ሪፖርት ያቀርባል፤
 • ለምርጫ አፈጻጸም በሚያመች መልኩ አግባብ ያላቸውን መረጃዎች እየሰበሰበና እያጠና በየጊዜው ለቦርዱ ጽህፈት ቤት ሪፖርት ያቀርባል፤
 • ስለስራ እንቅስቃሴው በየወቅቱ ለቦርዱ ጽህፈት ቤት ሪፖርት ያቀርባል፤
 • የስራ አመራር ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በክልል እና በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መድረክ እንዲዋቀ ርያደርጋል፣በክልል የሚቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መድረክ ያስተባብራል፤
 • የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይቋቋማል፤
 • የስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢና የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ምዕራፍ አራት

ስለ ቦርዱ በጀት

 1. በጀት
 • ቦርዱ ራሱን የሚያዘጋጀዉን አመታዊ በጀት ለህዝብ ተወካዮች ምከርቤት ቀርቦ ይፀድቃል፤
 • የገንዘብ ሚኒስቴር፣በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት ለቦርዱ የተመደበለትን በጀት በጸደቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በጀቱን ወደ ቦርዱ የባንክ ሂሳብ ያስገባል፡፡
 • ቦርዱ የሶሰት አመት በጀት ግምት እንዲወስንለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይችላል።
 • ቦርዱ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ስጦታና የገንዘብ እርዳታን ከሶስተኛ ወገኖች ሊቀበል ይችላል።
 1. የሂሳብ መዛግብት

1/ ቦርዱ የተሟላና ትክክለኛ የሆነ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል፡፡

2/ የቦርዱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሠነዶች በዋና ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል፡፡

ምዕራፍ አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

 1. የመተባበርና የማስፈጸም ግዴታ
 • ማንኛውም የፌደራልም ሆነ የክልል የመንግስት አካል ከቦርዱ ለሚቀርብለት ህጋዊ ጥያቄ ትብብር የማድረግና የማስፈጸም ግዴታ አለበት።
 • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን ግዴታ በመጣስ የምርጫ ሂደት እንዲስተጓጎል ያደረገ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባላቸው ህጎችና መርሆች መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል፣ እንዲሁምየምርጫ ሕጉ በሚደነግገው መሰረት በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል
 1. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ

ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በአዋጅ ቁጥር 532/1999 መሰረት ተሹመው በስራ ላይ ካሉ የቦርድ አባላት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠያቂነት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በስራ አመራር ቦርድ አባልነት እንዲቆዩ ሊወስን ይችላል፡፡

 1. መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ

በአዋጅ ቁጥር 532/1999 መሰረት ተቋቁሞ ለነበረው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥተው የነበሩ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ መሰረት ለተቋቋመው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተላለፈዋል፡፡

 1. ደንብና መመሪያ የማውጣት ስልጣን

የስራ አመራር ቦርዱ ይህንን አዋጅ ለማፈፀም የሚያስፈልጉ ደንቦችንና መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል።

 1. የተሻሩ ህጎች

1/የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ድንጋጌዎች በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ለይ ተፈፃሚነት ያላቸውም፡፡

2/ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ህጎችና ልማዳዊ አሰራሮች በዚህ አዋጅ ላይ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም።

 1. አዋጁ የሚፀናበትጊዜ

ይህ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

                      አዲስ አበባ ህዳር ____ቀን 2011 .

ሳህለወርቅ ዘውዴ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

 

Related Posts

3 thoughts on “የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማቋቋሚያ /ረቂቅ/ አዋጅ

 1. Dear Abrham, I appreciate your efforts,
  you indeed, ‘re engaged on tremendous
  contribution to legal professionals and beyond,
  Please keep it up.
  Tewodros HS

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: