Draft Laws

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማቋቋሚያ /ረቂቅ/ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር……/2011

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማቋቋሚያ አዋጅ

ዜጎች በየደረጃው በሚካሄድ ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫ በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ስልጣናቸውን በተግባር እንዲያውሉ ለማድረግ ነፃ የምርጫ አስፈፃሚ አካል አስፈላጊ በመሆኑ፣

በኢትዮጲያ ዴሞክራሲን ለማጠናከርብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ከማናኛውም አካል ነፃ አድርጎ በማደራጀት ፍትሃዊ፣ ተአማኒና ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈፀም የሚያስችለው መዋቅር እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን አመላመልና አሿሿም አሳታፊና ግልጽ በማድረግና የቦርዱን የመዋቅር፤ የሰራተኛ ቅጥርና ምደባ እንዲሁም የበጀት ነጻነት በማረጋገጥ በተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችና በመራጩ ዘንድ ያለውን ተዐማኒነትና የማስፈፀም አቅሙን ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በኢ.ፌ.ድ. ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና102 መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

ምዕራፍ አንድ

ጠቅላላ

 1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ “የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ___/2011” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

 1. ትርጉም

በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

 • ሕገ መንግስትማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት  ሲሆን፤“ህገ መንግስታት” ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና  የክልል ህገ መንግስታት ማለት ነው።
 • ” ቦርድ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 3 መሰረት የተቋቋመው የስራ አመራር ቦርዱን ሙሉ አባላት ያቀፈጽህፈት ቤትና በየደረጃው ያሉ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶችን ያካተተ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡
 • “የስራ አመራር ቦርድ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቅ 1 ላይ የተመለከቱትን አምስት አባላት ያቀፈ ቦርድ ነው፡፡
 • ምርጫማለትበሕገመንግስታት እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት የሚካሄድ የጠቅላላ፣ የአካባቢ፣ የማሟያ ወይም የድጋሚ ምርጫ ነው፡፡
 • ፖለቲካ ድርጅት ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ማለት የፖለቲካ ፕሮግራም ነድፎ አላማውን በሕጋዊ መንገድ ለማራመድ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው፡፡
 • “የምርጫ ክልል” ማለት ለምርጫ አፈፃፀም እንዲያመች እና ህዝቡ ወኪሎቹን እንዲመርጥ በህግ መሰረት የሀገሪቱ ግዛት ተከፋፍሎ የሚደራጅ የምርጫ አካባቢ ነው፡፡
 • “የምርጫ ጣቢያ” ማለት በየደረጃው የሚካሄዱ ምርጫዎች ምዝገባ የሚካሄድበት፤መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት እና ቆጠራ የሚካሄድበት ቦታ ነው፡፡
 • ጽህፈት ቤት ማለት የኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ነው፡፡
 • ከፍተኛ የመንግስት ሹመት ማለት በሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዲኤታ፣ አምባሳደር፣ኮሚሸነር፤ ምክትል ኮሚሸነር፣ዋና ዳይሬክተር ወይም ተመሳሳይ ደረጃ ያለቸው ሹመቶችን ያካትታል።
 • “የስነ ምግባር ጉድለት” ማለት በየኢትዮጲያውስጥ ብዙሃኑ የሚስማማባቸውየግብረገብ እሴቶች እናበህጎችና በሙያ ስነምግባሮች ላይ የተመሰረቱ መርሆችንየሚጥሱ ተግባራት ፈጽሞ መገኘት ነው።
 • “ሰው” ማለት በህግ የሰውነት መበት የተሰጠው ወይም የተፈጥሮ ሰው ነው፡፡
 • በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ ያካትታል፡፡

ምዕራፍ ሁለት

ስለ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

 1. መቋቋም
 • ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ (ከዚህ በኋላ ‘’ቦርድ”) እየተባለ የሚጠራ የህግ ሰውነት ያለው ከማንኛውም የመንግስት ወይም ሌላ አካል ተጽእኖ ነጻ የሆነና ራሱን የቻለ አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል።
 • የቦርዱ ተጠሪነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል፡፡

ቦርዱ በአዲስ አበባዋና ፅሀፈት ቤት የሚኖረው ሲሆን፣እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ቦታ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሊከፍት ይችላል

 1. የቦርዱ አቋም
 • ቦርዱ ሙሉ ጊዜ የሚያገለግሉ አምስት አባላት ያሉት የስራ አመራር ቦርድ ይኖረዋል፡፡
 • የስራ አመራር ቦርድ አባላት በቦርዱ ሰብሳቢ ውሳኔ መሰረት የተለያዩ የቦርዱን አላማ ፈፃሚ የስራ ዘርፎችንበሃላፊነት ይመራሉ።
 • የስራ አመራር ቦርዱ ለስራው አፈጻጸም አስፈላጊ የሆኑ ንኡስ ኮሚቴዎችን ሊያቋቁምይችላል፡፡
 • ቦርዱ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችይኖሩታል።
 1. የስራ አመራር የቦርዱ አባላት አሰያየም

የስራ አመራር ቦርዱ አባለት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 102 መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሚከተለው ስነ ስርዓት መሰረት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ፤

1/ጠቅላይ ሚኒሰትሩ እጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል የሚከተሉትን አባላት ያካተተ ገለልተኛ ኮሚቴ ያቋቁማል፡-

ሀ) ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ——-1 ሰው

ለ)   ከኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ……1 ሰው

ሐ) ከኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ …………..1 ሰው

መ) ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌደሬሽን…….. 1 ሰው

ሰ)  ከኢትዮጵያ ንግድና ማህበራት ምክር ቤት ……… 1 ሰው

ረ) ከኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን ….1 ሰው

ሠ) ከሲቪል ማህበራትና ካገር ሽማግሌዎች የሚመረጡ 3 ሰዎች

2/    በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር ከተዘረዘሩት ተቋማት የሚወከሉት ወይም የሚመረጡትየኮሚቴ አባላት ገለልተኛነታቸውና ብቃታቸው የተረጋገጠ፣እንደ አግባብነቱ በአንቀጽ 6 ስር የተዘረዘሩትን የስራ አመራር ቦርድ አባልነት መስፈርቶች የሚያሟሉ ሊሆኑ ይገባል።

3/     ኮሚቴው ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማህበራትየስራ አመራር ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን ጥቆማ ይቀበላል።

4/    ኮሚቴው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 ስር በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት  ግልጽና አወዳዳሪ በሆነ አካሄድ ከተጠቆሙት ሰዎች ውስጥ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን በመለየትና ፈቃደኝነታቸውን በማረጋገጥየእጩዎቹን ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ በማድረግ፣ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ይልካል።

5/    ኮሚቴው የሚያዘጋጀው የእጩዎች ዝርዝር ምልመላው በሚካሄድበት ወቅት በስራ አመራር ቦርዱ ካሉት ክፍት ቦታዎች ቁጥር እጥፍ መሆን ይኖርበታል።

6/    ጠቅላይ ሚኒስተሩ እጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ከኮሚቴው ከተቀበለ በኋላ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በቀረቡት እጩዎች ላይ ምክክር ያደርጋል።

7/    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 5 ስር የተገለጸውን ምክክር ካደረገ በኋላ ከቀረቡት እጩዎች መካከል እንደ አስፈጊነቱ የስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ የሚሆኑትን እጩዎች እንዲሁም የስራ አመራር ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት በስራ አመራር ቦርዱ ውስጥ ባሉት ክፍት ቦታዎች ቁጥር ልክ እጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሾሙ ያቀርባል።

8/    አንድ እጩ በስራ አመራር ቦርድ አባልነት የሚሾመው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ሹመቱን ሲያጸድቀው ነው፡፡

 1. የስራ አመራር ቦርድ አባልነት መስፈርቶች

1/    አንድ ሰው የሰራ አመራር ቦርድ አባል ለመሆን የሚችለው የሚከተሉትን መስፈርቶች ሲያሟላ ነው፡-

ሀ)    ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው፣

ለ)    የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ

ሐ)    ከምርጫ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ባላቸው በተለይም በሕግ፣ በፖሊቲካል ሳይንስ፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በእስታቲስቲክስ፣ በኢንፎርሜሽን ተክኖሎጂእና ሌሎች ተዛማጅነት ባላቸው ዘርፎች ከፍተኛ ሞያዊ ብቃት ያለው፣

መ) መልካም ስነ ምግባር እና ሰብእና ያለው፣

ሠ) የተሰጠውን ሀላፊነት ለመሸከም የሚያስችል ከፍተኛ የአመራር ብቃት ያለው

2/    የቦርዱ አባላት ስብስብ የብሄርና የፆታዊ ተዋጽኦን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል።

 1. የቦርዱ ስልጣንና ተግባር

ቦርዱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፤-

 • በሕገመንግስቱ እና በምርጫ ሕግ መሰረት የሚካሄድ ማንኛውንም ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ በገለልተኝነት ማስፈጸም፣
 • የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርት መስጠትና ተመሳሳይ ትምህርት ለሚሰጡ አካላት ፈቃድ መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር፣
 • የፖለቲካ ድርጅቶችን መመዝገብ፣ በህጉ መሰረት መከታተልና መቆጣጠር፣
 • ለፖለቲካ ፓርቲዎች የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግበትን መስፈርት ማውጣትና በመስፈርቱ መሰረት ድጎማውን ማከፋፈል፣
 • በምርጫ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎችን መገናኛ ብዙሃንን አጠቃቀም መወሰን፣
 • የምርጫ ክልሎችን አከላለል በተመለከተ ጥናት አድርጎ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
 • ለምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ መስጠት፣ የመከታተልና መቆጣጠር፣
 • የቦርዱን ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቶች በሁሉም ክልልሎችና ከዚያ በታች ባሉ የአስተዳደር እርከኖች ማደራጀት፣
 • ምርጫን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የምርጫ ጣቢያዎችን ቁጥር መወሰን፣
 • ምርጫንለማስፈጸምየሚያስፈልጉ የምርጫ ክልልና የምርጫ ጣቢያዎችንበመላሃገሪቱ ማደራጀት፣
 • ገለልተኛ፣ ብቃትና የህዝብ ተአማኒነት ያላቸው የምርጫ አስፈጻሚዎች መመልመልና ማሰልጠን፣
 • ከምርጫና ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ ማጠናቀር፣ የምርጫ ህጎችንና አፈጻጸምን በመገምገም ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለይቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣
 • የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መድረክን ማስተባበር፣
 • የምርጫው ውጤቶችን ማረጋገጥና ይፋ ማድረግ፣
 • በምርጫ ሂደት ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አስተዳደራዊ መፍትሄ መስጠት፣
 • በምርጫ ሂደት የምርጫ ውጤትን የሚያዛንፍ የህግ ጥሰት ተከስቷል ብሎ ሲያምን ውጤቱን መሰረዝና ድጋሚ ምርጫ ማካሄድ፣ እንዲሁም በምርጫ ሂደት የተፈጸመ የህግ መጣስ፣ ማጭበርበር ወይም የሰላምና ጸጥታ ማደፍረስ ድርጊት የፈጸሙ ግለሰቦችን በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ፣
 • በጀት አዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ማቅረብ፣ ማጸደቅና በስራ ላይ ማዋል፣
 • በየደረጃው የሚካሄዱ ምርጫዎችን መርሃግብር ሰሌዳእንዲዘጋጅ ማድረግ ማጽደቅ እንደአስፈላጊነቱ ማሻሻልና መፈጸሙን መከታተል፣
 • ለህዘብ ተወካዮች ምክርቤት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ማቅረብ፣
 • በዚህ ሕግና በሌሎች ሕጎች የተሰጡትን ሃላፊነቶች ለመወጣት አስፈላጊ የሆኑ ማንኛውንም ተግባራትን ማከናወን፡፡
 1. የስራ አመራር ቦርድ ስልጣንና ተግባር

የስራ አመራር ቦርድ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 ለቦርዱ በአጠቃላይ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባራት በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

 • ደንቦችንና መመርያዎችን ያወጣል፣
 • ለቦርዱ የተሰጡ ዝርዝር ስልጣኖችን የሚመለከቱ የፖሊሲ አቅጣጫዎን ያስቀምጣል ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፣
 • የቦርዱ የመጨረሻው ቅሬታ ሰሚ አካል ሆኖ ያገለግላል፣ የምርጫ ውጤቶችን ይፋ ከመደረጋቸው በፊት ያጸድቃል፣
 • የምርጫ ውጤትን የሚያዛንፍ የህግ ጥሰት በተከሰተ ጊዜ የምርጫ ወጤቶችን ይሰርዛል፣ ድጋሚ ምርጫ ያካሂዳል፣
 • የስራ አመራር ቦርዱ፣ የቦርዱ ጽ/ቤት፣ የቦርዱ ሰራተኞች የስራ ሂደት እንዲሁም ቦርዱ ከሌሎች መንግሰትታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች የሚመሩበትን ፖሊሲያዘጋጃል፤ በስራ ላይ ያውላል፤
 • የቦርዱን ጽህፈት ቤት ሃላፊና ምክትል ሃላፊ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ይሾማል፤
 • የስራ አመራር ቦርዱ አባላት የሚመሩበትን የስነ ምግባር መመሪያ ያወጣል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
 1. የስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የስራ አመራርቦርዱ ሰብሳቢ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

 • የስራ አመራር ቦርዱ የበላይ ሃላፊና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኖ ያገለግላል፣
 • ቦርዱን ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ባለው ግንኙነት ይወክላል፣
 • የስራ አመራር ቦርዱን ስብሰባ ይጠራል፣ ይመራል፣
 • የስራ አመራር ቦርዱ ውሳኔዎች ባግባቡ መፈጽማቸውን ይከታተላል፣
 • የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጎችን መሠረታዊ መርሆችተከትሎ በመንግሥት በልዩ ሁኔታ በሚጸድቅ ደንብ መሠረት ሰራተኞን ይቀጥራል፣ያስተዳደራል፣
 • የቦርዱ የውስጥ አደረጃጀትና በስራ አመራር ቦርዱ አባላት መካከል ያለውን የስራ ክፍፍል ከስራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር በመመካከር ይወስናል፣
 • የጽህፈት ቤቱን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል፣ሲፀድቅም ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፤
 • የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሰራተኞችን የሙያ ብቃት ካላቸውና ገለልተኛ ከሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች መካከል ግልጽ፣ አሳታፊና አወዳዳሪ በሆነ መንገድ መቀጠራቸውን ያረጋግጣል፤
 • የፌደራልና የክልል ህገመንግስቶችን መሰረት በማድረግ የምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል፣ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
 • የቦርዱ በጀት አግባብነት ባላቸው የፋይናንስ ህጎችና መርሆች መሰረት ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣
 • የፖለቲካ ድርጅቶችን የጋራ መድረክያስተባብራል፣
 • ማንኛውንም የቦርዱንና የፅህፈት ቤቱን የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ለስራ አመራር ቦርዱ ያቀርባል፣
 1. የስራ አመራር ቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የስራ አመራር ቦርዱ ምክትል ሰብሳቢየሚከተሉት ስልጣንና ተግባራትይኖሩታል፤

 • ሰብሳቢ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፣
 • በሰብሳቢው የሚሰጠውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል።
 1. የስራ አመራር ቦርዱ የስብሰባ ሥነ ሥርዓት
 • ከስራ አመራር ቦርዱ አባላት ሶስቱ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤይ ሆናል።
 • የስራ አመራር ቦርዱ ጉባኤ ውሳኔ በአባላት ድምፅ ብልጫ ይወሰናል ሆኖም ድምፅ እኩል የሚከፈል ከሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ሐሳብ የስራ አመራር ቦርዱ ውሳኔ ይሆናል፡፡
 • የስራ አመራር ቦርዱ የራሱን ዝርዝር የአሰራርና የስብሰባ ስነ-ስርዓት መመርያ ያወጣል፡፡
 1. የስራ አመራር ቦርዱ አባላት የስራ ዘመን
 • የስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ጊዜ ሁለት የምርጫ ዘመን ይሆናል።
 • የስራ አመራር ቦርድ አባላት ድጋሚበቦርድ አባልነት ሊሾሙ አይችሉም።
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ የተመለከተው ቢኖርም በዚህ አዋጅ መሰረት ከሚሰየመው የመጀመሪያው ዙር የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ውጪ ካሉት ሶስት የስራ አመራር ቦርድ አባላት መካከል የሁለቱ አባላት የስራ ዘመን ሰባት አመት ይሆናል፡፡
 • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረትበተመለከተው አግባብ የሚሾሙ የስራ ዘመናቸው ሰባት አመት የሚሆኑ የስራ አመራር ቦርድ አባላት መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትሩለሹመት በሚቀርቡበት ጊዜ ይለያሉ፡፡
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 3 መሰረት የስራ ዘመናቸው በሚያበቃ አባላት ምትክ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 በተደነገገው መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምትክ አባላት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያሾማል፡፡
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አባሉ በራሱ ፍቃድ ስራውን ከለቀቀ ወይም በህዘብ ተወካዮች ምክርቤት፡-

ሀ)   በህመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን ባለመቻል ፣

ለ)    ግልጽ በሆነ የስራ ችሎታ ወይም ብቃት ማነስ፣

ሐ)    ከባድ የስነ ምግባር ጉድለት መኖር፣ወይም

መ)   መ)ለተከታታይ 6 ወራት በስራ ገበታላይ ባለመገኘት፡፡

ምክንያት ካልተሰናበተ በቀር ከኃሃላፊነቱ አይነሳም።

7/    የቦርድ አባል ከቦርድ ኃላፊነቱ በፈቃዱ ከለቀቀ ወይም ጊዜውን ጨርሶ ከተሰናበተ በኋላ ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ በማንኛውም ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ሊሾም አይችልም።

 1. ስራ ስለ መልቀቅና ስለመሰናበት
 • አንድ የስራ አመራር ቦርድ አባል በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ(1)፣ (2) እና (3)በተቀመጡት ምክንያቶች ከሃላፊነቱ ሊነሳ ይገባል ብሎ ያሰበ አካል ወይም ግለሰብ ጥቆማውን ለፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ማቅረብ ይችላል።
 • የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የቀረበውን ጥቆማ መርምሮ በቂ ምክንያት የሌለው መሆኑን ካመነ ጥቆማውን ውድቅ ያደርጋል፡፡ ጥቆማው ምክንያታዊና መመርመር የሚገባው ነው ብሎ ካመነ፡-

ሀ)    ከጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ፣

ለ)    ከተያዘው ጉዳይ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ሙያዊ ብቃት ያለው አንድባለሙያ እና

ሐ)    ከኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን የተወከለ አንድ ሰው

ያሉበት አጣሪ ኮሚቴ በመሰየም ጥቆማውን በተገቢ ሁኔታ እንዲጣራ ያደርጋል፡፡

3/    ጉዳዩ በመጣራት ላይ ሳለ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ክስ የቀረበበት የቦርድ አባል በጊዜያዊነት በቦርዱ ስራ እንዳይሳተፍ ሊያግደው ይችላል፡፡

4/    ኮሚቴው በሚያጣራበት ሂደት ጥቆማ የቀረበበት የቦርድ አባል እራሱን የመከላከልና መከላከያ ማስረጃ የማቅረብ መብቱ ይጠበቅለታል፡፡

5/    ኮሚቴው በሚያደረገው ማጣራት ጥቆማው ትክክል መሆኑን ካረጋገጠና ይሄም ከሃላፊነት ሊያስነሳ የሚችል ነው ብሎ ካመነ ፣ የውሳኔ ሃሳቡን ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፤ ጉባኤውም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፡፡

6/የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ከጸደቀ ጥቆማው የቀረበበት የቦርድ አባል ከሃላፊነቱ ይነሳል።

 1. የስራ አመራር ቦርድ አባላት ስነ-ምግባር

ዝርዝሩ የስራ አመራር ቦርዱ በሚያወጣው የአባላት ሥነ ምግባር መመርያ የሚወሰን ሆኖ ማንኛውም የስራ አመራር ቦርዱ አባል፣

 • የተሰጠውን አላፊነት በገለልተኘነት፣ በነፃነትና በቅን ልቦና ማከናወን አለበት፤
 • ማንኛውንም በምርጫ የሚሳተፍ የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ የግል ዕጩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመደገፍም ሆነ በመቃወም መንቀሳቀስ የለበትም፤
 • በስራ አመራር ቦርድ አባልነቱ ምክንያት ባገኘው ሚስጢራዊ መረጃ ጥቅም ማግኘት ወይም መሞከር የለበትም፤
 • የቦርዱን ሚስጥር ለ3ኛ ወገን አሳለፎ መስጠት ወይም ማባከን የለበትም፤
 • በማንኛውም ሁኔታ የቦርዱን ወይም የአባላቱን ተአማኒነት፣ገለልተኝነትና ነፃነት ከሚጎዳ ወይም ከሚያጎድፍ ማንኛውም ተግባር መቆጠብ አለበት፡፡
 1. የስራ አመራር ቦርዱ አባላት መብት

ማንኛውም የስራ አመራር ቦርድ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፣

 • ማናኛውንም የስራ አመራር ቦርዱን ስብሰባ የመሳተፍና ድምፅየመስጠት፣
 • የቦርዱን ሰነዶች የመመልከት፣
 • የስራ አመራር ቦርዱን ስብስባ ጥሪ እና አጀንዳ በወቅቱ የማግኘት፣
 • አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የመጠየቅ፣
 • በስራ አመራር ቦርድ አባልነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ክፍያ የማግኘት
 • ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በቀር በኃላፊነት ላይ እስካሉ ድረስ ያለ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፈቃድ ያለመያዝና በወንጀል ያለመከሰስ መብት።
 1. የስራ አመራር ቦርዱ አባላት የጥቅም ግጭት
 • ማንኛውም የስራ አመራር ቦርድ አባል የተሰጠውን ሃላፊነት በፍትሃዊነትና በገለልተኛነት ለመወጣት እንዳይችል የሚያደርግ ማንኛውም አይነት የጥቅም ግጭት ያለበት ጉዳይ ሲገጥመው ወዲያውኑ ለስራ አመራር ቦርዱ በማሳወቅ እራሱን ማግለል ይኖርበታል።
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፀ 1 የተጠቀሰው ሁኔታ ሲከሰት ጉዳዩ በቃለጉባኤ ተይዞ ጉዳዩ በቀሪዎቹ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ይወሰናል።
 • ከጉዳዩ ጋር የጥቅም ግጭት ያለው የስራ አመራር ቦርድ አባል ሁኔታውን ሳይገልፅ በማናቸውም መንገድ ተሳትፎ ውሳኔ የተላለፈ ከሆነ ጉዳዩ እንደገና አንዲታይ ይደረጋል፡፡
 • ማንኛውም ሰው የስራ አመራር ቦርድ አባላት በሚያዩት ጉዳይ ጋር የጥቅም ግጭት አለ ብለው ካመኑ ማስረጃውን ወዲያውኑ በቦርዱ ጽህፈት ቤት በኩል ለስራ አመራርማቅረብ ይችላሉ፡፡
 1. ስለ ይግባኝ 

1/    የስራ አመራር ቦርዱ የሚሰጣቸው የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም የምርጫ ሂደትና ውጤትን በተመለከተ የሚሰጣቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

2/    ፍርድ ቤቱ ይግባኙን በተቀበለ በአንድ ወር ጊዜ ውሰጥውሳኔ መስጠት ይኖርበታል፤ሆኖም ጉዳዩ አጣዳፊ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩ ባህሪ በሚጠይቀው ፍጥነት ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል፡፡

 1. የስራ አመራር ቦርድ አባላት ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም
 • የቦርዱ ሰብሳቢ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ከፌደራል መንግስት ሚኒስትር ጋር ተመሳሳይ ይሆናል።
 • የተቀሩት የቦርዱ አባላት ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ከፌደራል መንግስት ሚኒስትር ደኤታ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል።
 • የስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ ወይም ከግማሽ የአገልግሎት ዘመንበላይ ካገለገሉ በኋላ በፈቃዳቸው ስራ ከለቀቁ በከሀላፊነት የተነሱ የሀገርና የመንግስት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የምክር ቤት አባለትና ዳኞች መብቶችና ጥቅሞች አዋጅ መሰረት የቦርዱ ሰብሳቢ የተሰናባች ሚኒስተርን ሌሎች የስራ አመራር ቦርድ አባላት ደግሞ የተሰናባች ሚኒስተር ደኤታንመብቶችና ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡
  Pages: 1 2

3 replies »

 1. Dear Abrham, I appreciate your efforts,
  you indeed, ‘re engaged on tremendous
  contribution to legal professionals and beyond,
  Please keep it up.
  Tewodros HS

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.