Uncategorized

“ቺኩንጉንያ” አዲስ ወረርሽን በድሬደዋ

Source: https://m.dw.com/am

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር “ቺኩንጉንያ” የተባለ ለአካባቢው አዲስ የሆነ ወረርሽኝ መከሰቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታወቀ።የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የበሽታውን ምንነት ለማረጋገጥ ናሙናዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከው በተደረገ ምርመራ በሽታው ቺኩጉንያ መሆኑ መረጋገጡን ተናግረዋል።በዚህ እና በሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች ከ3700 በላይ ሰዎች መታመማቸውንም ሃላፊው ተናግረዋል።
«ብዙ ሰዎች ታመዋል ወረርሽኝም ነው ። እስካሁን በደረሰን ሪፖርት ወደ 3756 አካባቢ ሰዎች ታመዋል ነገር ግን ከተላከው ናሙና ውጤት ሁሉም በዚህ በአዲሱ ወረረርሽኝ ታመዋል ማለት አይቻልም። አካባቢያችን ወባ እንደዚሁም ደንጊም አለ።ስለዚህ እነዚህ አሁን ሪፖርት የተደረጉ ሰዎች በጠቅላላ በዚህ በ«ቺኩንጉንያ»ታመዋል ማለe አይቻልም።ምናልባት ደንጊም ሊሆን ይችላል።ወባም ሊሆን ይችላል።»

በአካባቢው ከሚታወቁት ወባ እና ደንጊ ከተባሉት በሽታዎች የህመም ምልክት ጋር የሚቀራረብ ስሜት እንዳለው በተነገረው በዚህ በሽታ ተይዘው የነበሩ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በሽታው አቅም ያሳጣል።«ሁኔታው የመገጣጠሚያ የሰውነት አካልን ከአቅም በታች የማድረግና የአፍ ምሬት አለ። ራስ ምታት ከፍተና የሆነ ትኩሳት አለ።ፈሳሽ እነዚህን እነዚህን የመሳሰሉ ለጉዳት ያጋልጡሃል በሰው ቁጥጥር ስር ያደርግሃል።»
ቺኩንጉንያ ከዚህ ቀደም በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በቅርቡ በደቡብ ክልል ተከስቶ እንደነበር ያስረዱት ዶክተር ፉአድ ምናልባትም ከአጎራባች ክልሎች ወደ ድሬዳዋ ተዛመቶ ይሆናል የሚል ግምት እንዳለ ተናግረዋል። ዶክተር ፉአድ የበሽታው አስተላላፊ ነፍሳት ድሬዳዋ ውስጥ ያሉ ቢሆንም ባለመበከላቸው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሰዎችን ቢነክሱም በሽታውን የሚያስተላልፉ አልነበሩም ብለዋል።በርሳቸው ግምት ምናልባት በበሽታው የተበከሉ ነፍሳት ወይም ወደ ድሬዳዋ የመጣ በበሽታው የተያዘ ሰውን የነከሱ ነፍሳት ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም።

Categories: Uncategorized

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.