አለን ነጋሪት

ስለ “አለን ነጋሪት” አገልግሎት ጥቂት መግለጫ

“ምድር በዛፉ ሕግ በመፃፉ!” የሚል የሀገራችን ምሳሌያዊ አነጋገር አለ።
ይህ ብቻ መሰላችሁ “መነኩሴ በቆቡ ወንበር በኪታቡ” ይላል የአበው እና እመው ብሒል። በዘመኑ የአማርኛ አጠቃቀም ወንበር(ዳኛ)፣በኪታቡ(በሕግ መፅሀፉ) ማለት ነው።
ባጭሩ በሕግ ላይ እየሰሩ ከሆነ ሕጉ ያስፈልግዎታል።

አንዱ ጠበቃ ምን አለ መሰላችሁ?
አዲስ ከወጣ ሕግ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ገጥሞት ሕጉ መውጣቱን እያወቀ ግን አዋጁን ሊያገኘው አልቻለም

እና ምን አለ?

“አዋጁማ ወጥቷል…
በጄ ላይ ቢኖር፣
ሙግቴን አድምቼ
በረታሁ ነበር!!”

ከእንግዲህ ታትመው የወጡ አዋጆችን እና ደንቦችን ሌሎችንም ሕጎችን ለስራዎ ሲያስፈልጎ ወይም እንደ ቀልጣፋ የሕግ ባለሙያ እራስዎን በየወቅቱ ከሚወጡ ሕጎች ጋር ዝግጁ ለማድረግ በየዌብሳይቱ መዋተት፣ “ወጣ አልወጣ? የትስ አገኘዋለሁ” ብሎ መብሰልሰል፣ ወዳጅ ዘመድ የስራ ባልደረባ ጋር በማሰስ ውድ ጊዜዎን ማባከን አከተመ።

በማ? …በአለን ነጋሪት!!

አለን ነጋሪት አዳዲስ የሚወጡ ሕጎችን ተከታትሎ ከማተሚያ ቤት ወደ መስሪያ ቤት ሊያደርስልዎ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በገፃችን ላይ ባሉት የኢሜይል አድራሻዎቻችን ይመዝገቡና የቋሚ ደንበኝነት ቅፁን ይሙሉ።

ለፍ/ቤቶች፣ለመንግስትና ለግል ድርጅቶች፣ለተለያዩ ከሕግ ጋር የተያያዙ የምርምር ስራዎችን ለሚሰሩ ተቋማት፣ለጠበቆች፣ለሕግ ባለሙያዎች፣መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎችና ፍላጎቱ ላላቸው ግለሰቦች…የሚወጡትን ሕጎች ዋና ቅጂ ከእፍታው ላይ ጨልፈን ያሉበት ድረስ ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ለጊዜው አገልግሎቱን የጀመርነው በአዲስ አበባ ለምትገኙ ደንበኞቻችን ሲሆን በቀጣይ በመላው ሀገሪቱና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ኢትዮጽያውያንም እናዳርሳለን።

የቋሚ ደንበኝነት ቅፁን ከሞሉ አመቱን ሙሉ ሚወጡ ሕጎች አያመልጥዎትም።ቢሮዎ ድረስ ከች እናደርግልዎታለን።

እስካሁን ድረስ በርካታ ጠበቆችና ድርጅቶች አገልግሎቱን ለማግኘት ተመዝግበዋል።እርሶስ?

ስለ አገልግሎቱ ዝርዝር ማብራሪያና እንዲሁም የደንበኝነት ክፍያ በተመለከተ በኢሜይል: abooooka@gmail.com ይጠይቁን።

1 reply »

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.