በድሬዳዋ አስተዳደር ሀርላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በአስተዳደሩ የተላለፈውን የህዝብ ትራንስፖርት እገዳ የጣሰው አሽከርካሪ የሞት አደጋ አድርሷል፡፡

ዛሬ ዓርብ ረፋድ ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው የሚንባስ ተሸከርካሪ ከሀረር ወደ ድሬዳዋ አቅጣጫ ይጓዝ ከነበረ FSR አይሱዙ ጋር ተጋጭቷል፡፡

ግጭቱ ባደረሰው አደጋ በሚኒባስ ዉስጥ ተሳፍሮ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

እገዳውን ተላልፎ ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ የአካል ጉዳት ደርሶበት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

By Abrham Yohannes

Abrham Yohannes Hailu Licensed Lawyer & Consultant

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.