Site icon Ethiopian Legal Brief

3,000 ወገኖች ከጎዳና ላይ ሊነሱ ነው!

3,000 ወገኖች ከጎዳና ላይ ሊነሱ ነው!

እነዚህ ወገኖች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ በመጀመሪያ ዙር በአዳማ፣ በሐርር፣ በደሴና በአዲስ አበባ ከተሞች ወደሚገኙ አራት የተለያዩ ማዕከላት ይወሰዳሉ ይላል የደረሰኝ መረጃ።

ለዚህም ሰዎቹን ከጎዳና ላይ በማንሳት ለማሰባሰብ እንዲያስችል ከአራት ድርጅቶች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በዚህ ዙርያ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከመቄዶኒያ፣ ከክብረ አረጋውያን ፣ከመቅድም ኢትዮጵያ ፣ከሰደቂያስ የመርጃ ማዕከላት ጋር ነገ የፊርማ ሥነ-ስርዓት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@eliasmeseret

Exit mobile version