የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኮማንድ ፖስት አይተዳደርም!
የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና በህዝብ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኮማንድ ፖስት አይተዳደርም ብሏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስተዳድረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የሚኒስትሮች ኮሚቴ ነው።
ይህ እንዲሆን የተደረገው ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጥሎ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ‘ኮማንድ ፖስት’ የሚለው የአስተዳደር ስያሜ የፈጠረውን አሉታዊ ስሜት ለማስወገድ በማለም እንደሆነ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ትላንት በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።
በነገራችን ላይ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአምስት (5) ወራት ነው ተግባራዊ የሚደረገው።
የመብት እገዳዎችና እርምጃዎችን ዝርዝር ሁኔታ በየጊዜው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚሁ ዓላማ በሚያቋቁመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እየተወሰነ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia