የሶማሊያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር ሀሰን ሁሴን ለንደን ውስጥ በኪንግ ኮሌጅ ሆስፒታል በኮቪድ-19 ታመው ህክምና ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ ዕሮብ ሚያዝያ 1 ቀን መሞታቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል፡፡
ኑር አድድ በመባል የሚታወቁ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እ.ኤ.አ. ከህዳር 2007 እስከ የካቲት 2009 ባሉት ጊዜያት በሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ያገለገሉ በ 83 ዓመታቸው አርፈዋል ፡፡
ሞታቸውን ተከትሎም በሶማልያ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ታውጇል።
Categories: COVID_19