በኢትዮጵያ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ደርሷል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 447 ግለሰቦች መካከል ስምንቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 5ቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አንድ የኤርትራ፣ የሶማሊያ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ናቸው።
በአማረ ተመስገን
Categories: COVID_19, Ethiopian News