ኢትዮ ቴሌኮም ያለአግባብ ከሂሳባቸው ላይ እየቆረጠባቸው መሆኑን ደንበኞች ተናገሩ

ከኢትዮ ቴሌኮም ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ በገንዘባችን ከገዛነው ላይ ያለአግባብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ደንበኞች ተናገሩ፡፡

ደንበኞቹ ብዙዎቻችን ቤት በተቀመጥንበት በዚህ ሰዓት ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ ተቋሙ ገንዘባችንን ያለአግባብ እየቆረጠብን ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ሆነዋል፡፡

በቤት በሚቆዩበት ጊዜ ደግሞ ረጅሙን ጊዜአቸውን የሚያጠፉት በስልኮቻቸው ኢንተርኔት በመጠቀም መሆኑን ነግረውናል፡፡

ነገር ግን እንዚህ ተጠቃሚዎች በተለይ ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚሞሉት ጥቅል አልበረክት እንዳላቸው እና ቴሌ ያለአግባብ ገንዘብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ገንዘብ ካለአግባብ ከመቁረጥ ባለፈም የኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቆራረጠ እና ፈጣን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው ነግረውናል፡፡

የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለደንበኞቻቸው የዋጋ ቅነሳ እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮምም እንደ ተቋም የዋጋ ቅነሳ ማድረግ ሲኖርበት ጭራሽ ያለ አግባብ ገንዘባችንን መቁረጡ አሳስዝኖናልም ብለውናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ያአግባብ ገንዘብ እየቆረጠብን ነው፣ የኢንተርኔት አገልግሎቱም ፈጣን አይደለም የሚለው ቅሬታ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ተቋሙ ምላሽ ሊሰጠን አልፈቀደም፡፡

በትዕግስት ዘላለም
ሚያዝያ 6 ቀን 2012 ዓ.ም

Related Posts

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: