መንግስት ከውጭ በሚያስገባው የምግብ ዘይት ላይ የዋጋ ማስተካከያ አደረገ

መንግስት ከውጭ በሚያስገባው የምግብ ዘይት ላይ የዋጋ ማስተካከያ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መንግስት ከውጭ በሚያስገባው የምግብ ዘይት ላይ የዋጋ ማስተካከያ ማድረጉን አስታወቀ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጥራት እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሸቴ አስፋው የምግብ ዘይቱ ላይ ከዚህ ቀደም ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ በሊትር የ4 ብር ከ30 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉን ተናግረዋል።

አያይዘውም ዘይት ለማቅረብ ከክልሎች ተወክሎ የመጣ ማንኛውም አስመጪ ድርጅት በዚህ ዋጋ ለአከፋፋዮችና ለቸርቻሪዎች ማስረከብ እንደሚጠበቅበትም ነው የተናገሩት።

ቸርቻሪዎች ከአስመጪዎች የተረከቡትን ምርት በተመሳሳይ 4 ብር ከ30 ሳንቲም በመጨመር ለህብረተሰቡ ሽያጭ መፈጸም እንደሚገባቸውም አስረድተዋል።

ከዚህ ዋጋ ውጭ ግብይት ሲፈጽም በተገኘ ማንኛውም የንግድ ማህበረሰብ ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል።

ከተቀመጠው ዋጋ ውጭ ምርቱ ሲሸጥ ከተገኘ ህብረተሰቡ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Related Posts

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: