በአዲስ አበባ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ሁለት ሰዎች በጅብ መበላታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ሁለት ሰዎች በጅብ መበላታቸው ተገለጸ።

የመጀመሪያው ክስተት የተፈጠረው በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ሃና ማርያም አካባቢ ልዩ ቦታው አስቴር ሱቅ አካባቢ ነው።

ጾታቸው ወንድ የሆነው እኝህ ግለሰብ የ50 ዓመቱ ባለጸጋ እና ጾታቸው ወንድ አንድ ግለሰብ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት 4 ሰዓት አካባቢ ሲጋራ ለመግዛት ወደ ሱቅ እንደወጡ በጅብ መበላታቸውን የአካባቢው ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ቆይቶ የአካባቢው ሰው ሰውየውን ቢፈልግም ከልብስ እና ከራስ ቅላቸው ውጪ ማግኘት አለመቻላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሁለተኛው በጅብ ተበልተው ህይወታቸው ያለፈው በዚሁ የካ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ላምበረት መናሀሪያ አካባቢ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምቷል።

ከሁለት ቀን በፊት በጅብ ተበልተዋል የተባሉት እኝህ ግለሰብ በቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ እናት ሲሆኑ የአዕምሮ ህመምተኛ እንደነበሩም ሰምተናል።

የአካባቢው ፖሊስ ግን ግለሰቧ በጅብ ተበልተዋል መባሉን ሰምቶ በትክክል ሴትዮዋ በጅብ መበላታቸውን እየመረመርን ነው አሁን ላይ የሴት ጸጉር አግኝተናል ተጨማሪ ምርመራዎችን እያደረግን ነው ብሏል።

ምንጭ: ኢትዮ ኤፍ ኤም

በሳሙኤል አባተ
ሚያዝያ 7 ቀን 2012 ዓ.ም

Related Posts

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: