Uncategorized

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሞኑን ለተፈጠረው የሃይል መቆራረጥ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሞኑን ለተፈጠረው የሃይል መቆራረጥ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ።

ተቋሙ ለአዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የግብአት እጥረት እንዳጋጠመውም አስታውቋል፡፡

የአዳዲስ መስመሮችን ዝርጋታ ለማካሄድ የሚያግዙ የኤሌክትሪክ ግብአቶች እጥረት በማጋጠሙ አዳዲስ ደንበኞችን ከ ሃይል አቅርቦት ጋር ለማቀላቀል እጥረት ማጋጠሙን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገበየው ልካሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የግብአት አቅርቦቱ በሚፈለገው ደረጃ ወደ ሃገር ውስጥ እየገባ ባለመሆኑ ምክንያት ለአቅርቦቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን እያገኘን አይደለም ያሉን አቶ ገበየው እጥረቱ ሊያጋጥም የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሆኑን ነግረውናል፡፡

ምንም እንኳን ግብአቶቹን የሚያቀርቡ ከ 12 በላይ አገር በቀል ድርጅቶች በሃገር ውስጥ ቢኖሩም በሚፈለገው ልክ ግብአቶቹን ለማግኘት እክል መፍጠሩንም ነግረውናል፡፡

በርግጥ ይህ ሁኔታ በመዲናዋ የሃይል አቅርቦትን ለሚጠቀሙ ትላልቅ ድርጅቶችም ሆነ በ ግለሰቦች ዙሪያ በሚቀርበው የሃይል አቅርቦት ላይ የሃይል እጥረት አያጋጥምም ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ አስፈላጊና ቅድሚ ልንሰጣቸው የሚገቡ እንደ ሆስፒታሎችና ሌሎችም መሰረታዊ ተቋማት ላይ ቀድመን በቂ የሃይል አቅርቦት እንዲያገኙ ሰርተናል ስለዚህ በዚህ ላይ የሚያጋጥም እጥረት አይኖርም ብለውናል፡፡

ከሰሞኑ በመዲናዋ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተከሰተውን የሃይል መቆራረጥ በተመለከተ የሃይል አቅርቦቱ ሊከሰት የቻለው ከሰሞኑ የተስተዋለው ከፍተኛ ንፋስና ዝናብ በ ትራንስፎርመሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽን ሰተውናል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም የሃይል አቅርቦት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ትራንስፎርመሮችን የመቀየር ስራዎች በመሰራት ላይ በመሆኑ በቀጣይ ችግሩ ይፈታል ብለውናል።

ተቋሙም ለተፈጠረው የሃይል አቅርቦት መቆራረጥ ለተገልጋዩ ይቅርታን ጠይቋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሚያዝያ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

Categories: Uncategorized

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.