ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በስልክ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ኮቪድ19 የሚያስከትለውን ቀውስ ለመከላከል አብረን በምንሠራባቸው መንገዶች ላይ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።

ውይይታቸውም በኢኮኖሚ እና በምግብ ዋስትና ላይ ትኩረቱን አድርጎ መካሄዱንም አስታውቀዋል።

“ከቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ስብሰባ በኋላ በችግር ወቅት የሚያግዟት ጠንካራ ወዳጆችን አህጉራችን እንዳበጀች ውይይታችን አረጋግጦልኛል” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ገልፀዋል።

Related Posts

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: