የንግድ ህግ

Draft Commercial Code Amharic

አዋጅ ቁጥር…./2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሕግ

draft commercial Code Amharic

መቅድም

 

የኢኮኖሚ ዕድገትን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለንግድ ሥራ ጽኑ የሕግ መሠት መጣል የግድ ይላል፡፡ በ1952 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ለዚህ ዓላማ ከግብ መድረስ አስፈላጊውን መደላድል የሚያኖር ነበር፡፡ ከዘመኑ የኢትዮጵያ የዕድገት ደረጃ አኳያ ሲታይ ከጊዜው እጅግ የቀደመ ነበር ማለትም ይቻላል፡፡

 

ሆኖም ሕጉ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ስልሳ ዓመታት ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ ንግድ እና የመዋዕለንዋይ ፍሰት እጅግ ከመጨመራቸውም በላይ እያደር ድንበር-ዘለል ባህሪ እየተላበሱ መጥተዋል፡፡ እነዚህ ክስተቶች በተለይ ኢትዮጵያ ገበያ-መር ስርዓት መከተል ከጀመረችበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሕጉ በተግባር እንዲፈተሸ ዕድል ፈጥረዋል፡፡ በመሆኑም ሕጉ ውስጥ አንዳንድ ክፍተቶች እና ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ለአፈጻጸም የማይመቹ እና ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጡ ብዙ ድንጋጌዎች እንዳሉበትም ግልጽ ሆኗል፡፡ በአጭሩ ለመጪዎቹ ዓሰርት አመታት የንግድ እንቅስቃሴን ለመምራትና ለመግዛት ቀርቶ ዛሬ ኢትዮጵያ ለደረሰችበት የኢኮኖሚ እንቅስቀሴ ደረጃም ቢሆን ሕጉ የተሟላ እና በቂ ሆኖ አልተገኘም፡፡

 

ስለዚህ የነጋዴዎቸን፣ የባለሀብቶችን እና በሕጉ ጥቅማቸው በቀጥታ የሚነካ ባለድርሻ አካላት መብቶችን በሚዛናዊ ሁኔታ ለማስተናገድ፤ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስፋፋት ብሎም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ የንግድ ሕጉን ዘመናዊ ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

 

በመሆኑም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55  ንዑስ አንቀጽ (4)

መሠረት የሚከተለው ታውጇል

 

5 replies »

  1. 7ኛ ማህበር መጨመሩ የህግ ግራውንድ አለ ብዬ አላምንም ምክንያቱም ባለ 1 ሰው ማህበር ተብሎ እንዴት ይጠራል

  2. Thank you Dear Mr. Abraham. May you attach a freely downloadable versions of Ethiopian draft laws.

    • Would you send me the final draft of commercial code.I am preparing LLM Thesis and I need it for reference,please!

  3. Thank you for propagating the laws to us. I hope we will find the draft commercial code English version soon.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.