የምግብ ምዝገባና የገበያ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

ፍቃድ ሰጪው አካል

የኢትዮጵያ የምግብ፣መድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን

የአገልግሎት ክፍያ

አዲስ ምዝገባ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ምግቦች 1650 ብር

ዳግም የምግብ ምዝገባ ለማካሄድ  870 ብር

የምርት ወይም የአሰራር ለውጥ ማድረግ 870 ብር

ቅድመ-ሁኔታዎች

አዲስ ምዝገባ ለማካሄድ

– የተሟላ ማመልከቻ

– የምግቡ አመራረት ሂደት፣ይዘት፣የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት እና

የመሳሰሉ መረጃዎች የያዘ ሰነድ (Dossier)

– ለምርቱ ላቦራቶሪ ጥራት ምርመራ አገልግሎት የሚውል test method & Reference standard

ዳግም ምዝገባ ለማካሄድ

– በነባሩ የተመዘገበ ምግብ የአመራረት ሂደት፣ ይዘት፣ የምርመራ ዘዴ እና ሌሎች

በምርቱ ላይ የተደረጉ ለውጦች አለመኖራቸው የሚገልጽ ደብዳቤ

– አመታዊ የምግቡ አመራረት ሂዳት ግምገማ ሪፖርት

የምርት/አሰራር ለውጥ ለማድረግ

– የተሟላ ማመልከቻ

– የአሰራር ወይም የይዘት ለውጥ የተደረገበት ምግብ ይዘት፣ አመራረት

ሂደት፣ የምርመራ ዘዴና ሌሎች መረጃዎች የያዘ ሰነድ

– ለምግቡ ላቦራቶሪ ጥራት ምርመራ የሚያስፈልግ test method & Reference standard እና

– ሌሎች በምግብ ምዝገባና ፈቃድ ቁጥጥር መመርያዎች ላይ የተገለፁ መስፈርቶች

Related Posts

2 thoughts on “የምግብ ምዝገባና የገበያ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

Leave a Reply to shiwonzish Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: