Site icon Ethiopian Legal Brief

የተሻሻለው የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012 ዓ.ም

የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012 .(የተሻሻለው)

መግቢያ

 

በምርጫሂደትየአገርውስጥየምርጫታዛቢዎችመኖርነፃእናገለልተኛምርጫእንዲኖርበማድረግያለውንሚናበመገንዘብ፤

የአገርውስጥየምርጫታዛቢዎችንማንነት፣የፈቃድአሰጣጥስርዓቱንእናተግባርናሃላፊነታቸውንእንዲሁምመብቶቻቸውንበግልፅማስቀመጥአስፈላጊበመሆኑ፤

በአገር ውስጥ በምርጫ ታዛቢነት የሚሰማሩ ድርጅቶች አና ተወካዮቻቸው ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነምግባር መርሆዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ፤

የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድየኢትዮጵያየምርጫ፣የፖለቲካፓርቲዎችምዝገባእናየምርጫስነ

ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 114 እስከ  117 እና በቦርዱ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር1133/2011 አንቀፅ 7 ንኡስ አንቀፅ (7) እና አንቀፅ 8 ንኡስ አንቀፅ (1) በተሰጠውስልጣንመሠረትየሚከተለውንመመሪያአውጥቷል።

ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ

 

አንቀፅ 1.        አጭር ርዕስ

 

ይህ መመሪያ “የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ስነ-ምግባርመመሪያቁጥር

5/2012 ዓ.ም” ተብሎሊጠቀስይችላል።

 

አንቀፅ 2.    ትርጓሜ

የቃሉአገባብሌላትርጉምየሚያሰጠውካልሆነበስተቀርበዚህመመሪያውስጥ፤

ቁጥር 1162/2011 ዓ.ምነው፡፡

3) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው።

ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት በማንኛውም መደበኛ ሁኔታ ይደርሳሉ ተብሎ ያልተገመቱ እና ያልተጠበቁ፣ ከአመልካቿ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት የሚደርሱ እና እንዳይደርሱ መከላከል ወይም ማስቆም የማይቻሉ ክስተቶች ናቸው፡፡

 

አንቀፅ 3. የጾታ አገላለጽ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በሴት ጾታ የተገለጸው አነጋገር ሌላኛውንም ጾታ ያካትታል፡፡

 

አንቀፅ 4. የተፈፃሚነት ወሰን

ይህመመሪያበጠቅላላምርጫ፣በአካባቢምርጫ፣በማሟያምርጫ፣በድጋሚምርጫወይምበህገመንግሥቱእናበአዋጁመሠረትየሚካሄድህዝበውሳኔላይለመታዘብከቦርዱፈቃድበተሰጣቸውየሀገርውስጥየምርጫታዛቢዎችላይተፈፃሚይሆናል።

ክፍል ሁለት ስለታዛቢነት ፈቃድ ጥያቄ አቀራረብና ስለፈቃድ አሰጣጥ

 

አንቀፅ 5.         የታዛቢነት ጥያቄ ስለማቅረብ

 

 

አንቀፅ 6.        የታዛቢነት ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ያለበት መመዘኛ

 

 1. ማንኛውምየምርጫታዛቢነትፈቃድእንዲሰጠውየሚጠይቅአገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅት፡

ሀ) ሕጋዊ ሰውነት ያለው፣

ለ) ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና የመንግስት አካል     ያልሆነ፣

ሐ) የቦርድ አባላቱና መሪዎቹ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑ፣

መ) የሚያሰማራቸውታዛቢዎችምርጫንበገለልተኝነትለመታዘብየሚችሉእንዲሁምድርጅቱየማስፈፀምአቅምያለው፣መሆንአለበት፡፡

 1. ማንኛውምፈቃድጠያቂድርጅትየሲቪልማህበረሰብድርጅቶችህብረትከሆነሁሉምአባልድርጅቶችበዚህመመሪያየተደነገጉትንግዴታዎችማሟላታቸውንማረጋገጥአለበት።

 

አንቀፅ 7.  ከታዛቢነት ማመልከቻ ጋር ተያይዘው ስለሚቀርቡ ሰነዶች

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6 መሠረትከሚቀርብየምርጫታዛቢነትማመልከቻጋርየሚከተሉትሰነዶችበአባሪነትተያይዘውመቅረብአለባቸው።

ሀ) ፈቃድ ጠያቂው ድርጅት ስልጣን ካለው መንግስታዊ ተቋም የተሰጠውና በአገር በቀል የሲቪል ማህበርነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያሳይ  ማስረጃ፣

ለ) ድርጅቱበቦርዱየተዘጋጀውንየስነምግባርደንብአክብሮለመንቀሳቀስፈቃደኛመሆኑንየሚገልጽበተቋሙማህተምናየበላይኃላፊፊርማየተረጋገጠሰነድ፣

ሐ) ቦርዱለዚሁባዘጋጀውቅጽላይየሚሞላሆኖድርጅቱበምርጫታዛቢነትየሚያሰማራቸውተወካዮችበቦርዱየተዘጋጀውንየስነምግባርደንብአክብረውለመንቀሳቀስየተስማሙስለመሆኑበእያንዳንዱተወካይፊርማየተረጋገጠሰነድ፣

መ) በዚህ አንቀጽ በፊደል ተራ (ሐ) ከተመለከተውሰነድጋርተያይዞየሚቀርብየተወካይዋሙሉስምእናየወከለችውንድርጅትስምበጀርባውየያዘተወካይዋበቅርብጊዜየተነሳችውሁለትየፓስፖርትመጠንጉርድፎቶዎች፣

ሠ) የተወካይዋን ማንነት የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ ኮፒ፡፡

 

አንቀጽ 8. በምርጫ ታዛቢ ድርጅት ስለሚቀርቡ ወኪሎች

 

ሀ) ኢትዮጵያዊዜግነትያላት፣

ለ) እድሜዋ 21 ዓመትእናከዚያበላይየሆነ፣

ሐ) የመምረጥእናየመመረጥመብቷበሕግያልተገደበ፣

መ) የታወቀ ብልሹ ስነ-ምግባር የሌላት፣

ሠ) በእጩተወዳዳሪነትያልተመዘገበች፣

ረ) ቀደም ሲል በምርጫ ታዛቢ ተወካይነት ተሰማርታ በቦርዱ ያልታገደች መሆን አለባት።

ማንኛውምየምርጫታዛቢድርጅትምርጫንየሚታዘበውበቦርዱተመዝግባፈቃድእናመታወቂያወረቀትበተሰጣትተወካዩአማካይነትነው፡፡

ይችላል፡፡

 

አንቀፅ 9. ስለፈቃድ አሰጣጥ

 

በማስፈረምየታዛቢነትየምስክርወረቀትይሰጣል፡፡

 

አንቀፅ 10.የታዛቢነትመታወቂያካርድስለመስጠት

 

ይሆናል።

 

ሀ) የቦርዱን ሎጎ /አርማ/፣

ለ) የወከለችውን ድርጅት ስም

ሐ) የተወካይዋን ሙሉ ስም፣

መ) የቦርዱ ማህተም፣

ሠ) መታወቂያው የሚፀናበት ጊዜ፣

ረ) የመታወቂያ ቁጥር፣

ሰ) ፈቃዱን የሠጠችው ኃላፊ ስም እና ፊርማ፣

ክፍልሶስትየአገርውስጥየምርጫታዛቢመብትናግዴታ

 

አንቀፅ 11. የአገር ውስጥ ምርጫ ታዛቢ መብት

ከቦርዱየምርጫታዛቢነትየምስክርወረቀትያገኘድርጅትተወካይ፤

ሀ)በምርጫጣቢያበመዘዋወርየምርጫውንሂደትማለትምየመራጮችምዝገባን፣የእጩዎችምዝገባንናየምርጫቅስቀሳንእንደዚሁምየድምፅአሰጣጥን፣የቆጠራሂደትንእናየውጤትአገላለጽንየመከታተልናተገቢመረጃጠይቃየማግኘትመብት፣

ለ)  የምርጫ ሰነዶችን የመመልከት፤ የድምጽ አሰጣጥ እና የድምጽ ቆጠራ ሂደቱን የመታዘብ፣

ሐ)  በምርጫው ሂደት የታዘበቸውን ወይም ያጋጠማትን ጉድለቶች ለቦርዱ ወይም በየደረጃው ላሉ የቦርዱ ጽ/ቤቶች የማቅረብ፣

መ) ከማንኛውም መንግስታዊም ሆነ ከማናቸውም ሌላ ተቋም ወይም ሰው ተፅእኖ ነፃ የመሆን፣

ሠ)  ምልከታዋን፣ ትዝብቷን ወይም ግኝቷን እና የደረሰችበትን ድምዳሜ አስመልክቶ ለህዝብ ይፋ መግለጫ የመስጠት፣

ረ)  ከቦርዱና ከአካባቢ ባለስልጣናት እንደዚሁም በየደረጃው ከሚገኙ የምርጫ አስፈፃሚ አካላት ትብብር የማግኘት፣ መብት አላት፡፡

 

አንቀጽ 12. የአገር ውስጥ ምርጫ ታዛቢ ግዴታ

 

1) ከቦርዱ የምርጫ ታዛቢነት የምስክር ወረቀት ያገኘች የምርጫ ታዛቢ:-

ሀ) የታዛቢነት መታወቂያዋን በግልጽ ማንጠልጠል፣

ለ)  የምርጫ አስፈፃሚዎች የሚሰጧትን መመሪያ ማክበር፣

ሐ)  የምርጫው ሂደት በትክክልና በብቃት እንዳይካሄድ ከሚያደናቅፍ ተግባር መቆጠብ፣

 

መ)  ቦርዱ ያወጣውን የስነ-ምግባር መመሪያ ማክበር፣

ሠ)  ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅታ ለቦርዱ የማቅረብ፣ግዴታ አለባት፡፡

2) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1(ሠ) የተመለከተው ሪፖርት በሚከተለው አኳኋን መቅረብ አለበት፤

ሀ) ማንኛውም ተወካይ ለወከለችው ድርጅት ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅታ የተሰማራችበት የምርጫ ጣቢያ ወይም የምርጫ ክልል ውጤት በተገለፀ ከ7 እስከ 10 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የማቅረብ ግዴታ አለባት።

ለ)  ማንኛውም የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢ ድርጅት ስለታዘበው የምርጫ እንቅስቃሴ ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅቶ ቦርዱ የምርጫውን ውጤት ይፋ ካደረገበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ የሪፖርቱ ይዘትም፦

 1. ድርጅቱበምርጫታዛቢነትሥራውየሸፈነውክልል፣ዞን፣የምርጫክልልወይምምርጫጣቢያብዛትእናየመረጃአሰባሰብዘዴውን፣
 2. በእያንዳንዱየምርጫእንቅስቃሴሂደት፣በምርጫዝግጅት፣በመራጮችምዝገባ፣በእጩዎችምዝገባ፣በምርጫዘመቻ፣በድምፅአሰጣጥ፣በድምፅቆጠራእናበውጤትአገላለፅላይየታዘባቸውንሁኔታዎችናየተጠቀመባቸውመረጃዎች፣
 3. የትዝብትሪፖርቱበምርጫሂደቱያለውንየፆታተዋፅኦዝርዝርየሚያሳይመሆን

አለበት፡፡

 

አንቀፅ 13. ምርጫን ለመታዘብ ስለሚያስፈልጉ ወጪዎችና ስለስልጠና  

 

ማንኛውምየሀገርውስጥየምርጫታዛቢተቋምየወከላቸውታዛቢዎችተግባራቸውንከመጀመራቸውበፊት፦

ሀ)  ስለ ምርጫ ሂደቶች፣

ለ) በምርጫ ህጐች እና አሠራሮች እንዲሁም

ሐ)  በዚህ መመሪያ ድንጋጌዎች ላይ የተሟላ ስልጠና እንዲያገኙ እና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ አለበት።

 

ክፍልአራት

የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነምግባር ድንጋጌዎች

 

አንቀፅ 14. ህግን ስለማክበር

 

ማንኛውምፈቃድየተሰጠውድርጅትወይምወኪሏ፦

ሀ) አዋጁን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን እንደዚሁም ሌሎች ተዛማጅ ህጎችን ማክበር፣

ለ)  በቦርዱ የተሰጣትን የመታወቂያ ካርድ በግልጽ በማንጠልጠል መንቀሳቀስ እና  ማንነቷን የሚያረጋግጥ ፎቶ ያለው ማንኛውም አይነት መታወቂያ ወይም  ፓስፖርት ማሳየት አለባት

 

አንቀጽ 15.  የምርጫአስፈፃሚዎችንስልጣንማክበር

 

ማንኛውም ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ወይም ወኪሏ፦

ሀ)  የቦርዱን እና በየደረጃው ያሉ የምርጫ አስፈፃሚዎችን፣ የፀጥታና ደህንነት እንደዚሁም የሌሎች የመንግስት አካላት የሚሰጧትን ህጋዊ ትዕዛዝና መመሪያ መቀበልና ማክበር፣

 

ለ)  ከምርጫ አስፈፃሚዎች እንደዚሁም ከሌሎች ታዛቢዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ መስራት አለባት።

 

አንቀጽ 16.   ምክር ስላለመስጠት

 

 

ማንኛውምፍቃድየተሰጠውየሀገርውሰጥየምርጫታዛቢድርጅትእናተወካይዋ፤

ሀ)  ለምርጫ አስፈፃሚዎች ከኃላፊነታቸው ጋር የተያያዘ መመሪያ ወይም ምክር መስጠት

የለባትም፣

ለ)  የሚመለከቷቸውን የጎሉ ስህተቶችን ለምርጫ አስፈፃሚዎች ሪፖርት ከማድረግ ውጭ ምክር በመስጠት ችግሮችን ለመፍታት አለመንቀሳቀስ፣

ሐ)  የአፈታት ሂደቱን ከመታዘብ ውጭ የውይይቱ አካል በመሆን በቅሬታ /አቤቱታ/ በመፍታት ሂደት ውስጥ መሳተፍ፣ የለባትም፡፡

 

አንቀፅ 17.   ገለልተኛ ስለመሆን

 

ፈቃድየተሰጠውየሀገርውስጥየምርጫታዛቢድርጅትወይምወኪሏ፦

ሀ) ተግባራቷን ከወገንተኝነት በፀዳ አኳኋን ማከናወን፤ ከማንኛውም አካል ጋር በማንኛውም ሁኔታ ገለልተኝነቷን ከሚጎዳ ወይም ወገንተኝነትን ከሚያሳይ እንቅስቃሴ መቆጠብ፣

ለ)  የፖለቲካ ድርጅቶችን ወይም እጩን ወገንተኝነት ሊገልፅ ከሚችል በነዚህ አካላት ወይም ሰዎች ከተዘጋጀ የጉብኝት፣ የግብዣ ወይም ሌላ መሰል እንቅስቃሴዎች ላይ ከመሳተፍ መታቀብ፣

ሐ)  ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወይም እጩን ከመደገፍ ወይም ከመንቀፍ መቆጠብ፤ ከባለስልጣናት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከእጩ ተወዳዳሪዎች ከመራጮችና ከመገናኛ ብዙኃን ጋር የተያያዘ ወይም አወዛጋቢ በሆነ የምርጫ ጉዳይ ላይ ወገንተኝነትን ከማሳየት ወይም ከመግለጽ መታቀብ፣ አለባት።

 

መ)የማንኛውንምበምርጫእንቅስቃሴውስጥያለየፖለቲካድርጅትንወይምእጩን፣ማንኛውንምአይነትምልክትወይምየቅስቀሳቁሳቁስበግቢዋ፣በቢሮዋ፣በመጓጓዣዋ፣በራሷላይእንደሁኔታውበማሳየት፣በመያዝ፣በማስቀመጥ፣በመስቀል፣በመለጠፍወይምበመልበስበመሳሰለውሁኔታመንቀሳቀስ፣ማሳየትወይምይዛመገኘትየለባትም።

 

አንቀጽ 18. የምርጫን ሚስጥራዊነት እና የመራጮችን መብት ስለማክበር

 

ማንኛውምፈቃድየተሰጠውድርጅትወይምተወካይዋ፤

ሀ)    መራጩድምፁንለማንእንደሰጠወይምማንንእንደሚመርጥመጠየቅየለባትም።

ለ)    በምትታዘብበት ወቅት የምርጫ ሂደቱን በሚያውክ ሁኔታ የምስል እና የድምፅ መቅረጫ መሳሪያ መጠቀም   የለባትም፡፡

ሐ) መራጭድምፅበሚስጢርየሚሰጥበትክፍልወይምለዚሁየተከለለቦታካሜራምሆነሌላየድምፅወይምየምስልመቅረጫመሳሪያመጠቀምየለባትም።

መ)  ማንኛውንም ለመመዝገብ የቀረበች መራጭ ወይም ድምፅ ለመስጠት የተገኘች መራጭ ወይም የምርጫ አስፈፃሚ ያለፈቃዷ ወይም በግልፅ እየተቃወመች በፊልም መቅረጽ፣ ፎቶግራፍ ማንሳት ወይም በቃለ-መጠይቅማወያየትየለባትም፡፡

ሠ)  የመራጮችምዝገባመረጃዎችበሰነድላይሲሰፍሩወይምመራጩበድምፅመስጫውወረቀትላይየምርጫምልክትሲያደርግ፣ተደብቃበፊልምመቅረጽወይምፎቶግራፍ

ማንሳትየለባትም፡፡

ረ)  የድምፅ ሰጪዎችን የግላዊነት መብት በሚነካ አኳኋን የመራጮችን መዝገብ፣ የመራጮችን ምዝገባ መታወቂያ ወይም ማናቸውንም ሌላ ሰነድ በፊልም መቅረጽ፣ ፎቶግራፍ ማንሳት ወይም ኮፒ ማድረግ የለባትም፡፡

አንቀፅ 19.   ጥቅም አለመቀበል ወይም አለመስጠት

 

ማንኛውምየአገርውስጥየምርጫታዛቢድርጅትወይምተወካይዋከማንኛውምበምርጫእንቅስቃሴከሚሳተፍየፖለቲካድርጅት፣እጩ፣ደጋፊወይምማንኛውምሰውወይምአካልበምርጫሂደትማንኛውንምተግባርለማድረግወይምላለማድረግወይምበደጋፊነትለመንቀሳቀስበማሰብጥቅም

መቀበል ወይም መስጠት፣ ለመቀበል ወይም ለመስጠት መዋዋል ወይም ቃል መግባት የተከለከለ ነው ፡፡

 

አንቀፅ 20.   የጥቅም ግጭት

 

ሀ)    የምርጫሂደትንከመታዘብተግባሯጋርየተያያዘየጥቅምግጭትንለቦርዱማሳወቅአለባት።

ለ)  የጥቅም ግጭት የሚያስከትል ወይም ሊያስከተል በሚችል በማንኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ መሣተፍ የለባትም፡፡

 

 

 

 

ቦርዱ በዚህ አንቀፅ መሠረት የጥቅም ግጭት ካጋጠመው ሰው ወይም ከሚመለከታት የምርጫ አስፈፃሚ ሪፖርት ሲደርሰው ጉዳዩ ነፃ፣ ቀጥተኛና ፍትሃዊ ምርጫን የማያደናቅፍ መሆኑን በራሱ በማጣራት በቦታው ላይ ሥራውን እንዲቀጥል ወይም ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር ወይም ከታዛቢነቱ እንዲሰረዝ ሊወስን ይችላል። ውሳኔውንም ወዲያውኑ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል።

 

አንቀፅ 21. ሀቀኝነት/ እውነተኝነት

 

ማንኛውምየአገርውስጥየምርጫታዛቢድርጅትምሆነድርጅቱየሚያሰማራትተወካይ፦

ሀ) በማንኛውምጊዜየምታቀርበው፣የምታሰራጨውመረጃወይምሪፖርትሀቀኛ፣በበቂማስረጃየተደገፈግልፅናየማያሻማመሆንአለበት።

ለ) ያቀረበችውወይምያሰራጨችውሪፖርትወይምመረጃተቀባይነትባለውአሰራርየተሰበሰበ፣የተጠናቀረ፣የታተመእናየተፈረመበትመሆንአለበት።

ሐ) የምታገኘው መረጃ በሚመለከተው አካል ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ ስታገኘው ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ በመረጃነት መጠቀም የለባትም።

 

አንቀፅ 22. ቅንነት

 

 1. ማንኛውምየአገርውስጥየምርጫታዛቢድርጅትወይምተወካይዋየታዛቢነትተግባሯንበምታከናውንበትሂደትቅንነትየተሞላበትስነምግባርሊኖራትይገባል።
 2. ተወካይዋየተጣለባትንኃላፊነትለመወጣትየማያስችልሁኔታሲያጋጥማትጉዳዩንወዲያውኑለላካትድርጅትማቅረብአለባት።

 

አንቀፅ 23. ስለምርጫው ውጤት አስቀድሞ አስተያየት መስጠት ስለመከልከሉ

 

ማንኛውም የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢ ድርጅት ወይም ተወካይዋ፡-

 1. የምርጫውጤትበቦርዱበይፋከመገለፁበፊትበሀገርውስጥምሆነከሀገርውጪሆኖስለምርጫውውጤትአስተያየትመስጠትክልክልነው።
 2. በዚህ አንቀጽ በተራ ቁጥር 1 የተቀመጠውእንደተጠበቀሆኖየምርጫታዛቢድርጅቱንስለሚወክሉትየምርጫታዛቢዎችዝግጅትእናየመሳሰሉትላይአስቀድሞመግለጫሊሰጥ

ይችላል፡፡

ክፍል አምስት ልዩልዩ ድንጋጌዎች

 

አንቀፅ 24. ፈቃድ የሚታገድበት ወይም የሚሠረዝበትሁኔታ

 

 1. ቦርዱአንድየአገርውስጥየምርጫታዛቢወይምተወካይዋየምርጫሂደትንእንድትከታተልየሰጠውንፈቃድእንደአግባብነቱበሚከተሉትምክንያቶችሊያግድወይምሊሠርዝይችላል፤

 

ሀ. አግባብነት ያለቸው ህጐችን ወይም የተስማማችበትን የስነ-ምግባርመመሪያየሚጥስተግባርፈፅማስትገኝ፣

ለ. በህግከተደነገገውውጭማንኛውንምአድልኦለየትኛውምእጩወይምፖለቲካፓርቲአሳይታ

ስትገኝ፡፡

 1. ቦርዱየሰጠውንፈቃድሲሰርዝወይምሲያግድውሳኔውንየወሰነበትንምክንያትበመግለጽለሚመለከተውሰውማሳወቅአለበት።

አንቀፅ 25.   ስለሚወሰድ እርምጃ

 

የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢ ወይም ተወካይዋ ከዚህ የስነ-ምግባርመመሪያእናከገባችውግዴታውጪስትንቀሳቀስከተገኘችቦርዱእንደሁኔታው፦

ሀ) ማስጠንቀቂያ በመስጠት ስህተቷን እንድታርም ወይም ተወካይዋ እንድትቀየር ሊያደርግ፣

ለ) ለአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢነት የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዝ ወይም /እና ፣

ሐ) ድርጊቱየሌሎችህጎችንድንጋጌዎችየሚጥስከሆነበህግእንድትጠየቅጉዳዩንስልጣንላለውአካልሊመራውይችላል።

 

 

አንቀፅ 26.   የመተባበር ግዴታ

 

ማንኛውምሰውይህንንመመሪያበስራላይለማዋልየመተባበርግዴታአለበት።

 

አንቀፅ 27.   ተፈፃሚነት የሌላቸው   መመሪያዎች እና አሰራሮች

 

ማንኛውምከዚህመመሪያጋርተቃራኒየሆነመመሪያወይምአሠራርበዚህመመሪያበተሸፈኑጉዳዮችላይተፈፃሚነትየለውም።

 

አንቀፅ 28.   መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

 

ይህ መመሪያ ከየካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ምጀምሮየፀናይሆናል።

 

 

ብርቱካን ሚደቅሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

Exit mobile version