Site icon Ethiopian Legal Brief

የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2012

የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2012

መመሪያ ቁጥር 4-2012 DOWNLOAD .pdf

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁ. 1162/2011 አንቀጽ 124 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመራጮች ትምህርት ስለሚሰጡ አካላት፣ ትምህርቱ ስለሚሰጥበት አሠራር እና ለነዚህ አካላት የማስተማር ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነምግባር ለመደንገግ የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል።

ምዕራፍ አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ

አንቀጽ 1. አጭር ርዕስ ይህ መመሪያ “የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 04/2012 ዓ.ም” ተብሎሊጠቀስይችላል።

አንቀጽ 2. ትርጓሜየቃሉአገባብሌላትርጉምየሚያሰጠውካልሆነበስተቀርበዚህመመሪያውስጥ፤

 1. “የምርጫ ሕግ” ማለት የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁ. 1162/2011 ነው፡፡
 2. “ቦርድ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 የተቋቋመውየኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድነው።
 3. “ክልል” ማለት በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 መሠረትየተቋቋመክልልሲሆንለዚህአዋጅአፈጻጸምሲባልአዲስአበባንናድሬዳዋንይጨምራል።
 4. “አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት” ወይም “ድርጅት” ማለት ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ኢትዮጵያውያን በፈቃደኝነት የሚመሠረት፣ የመንግሥት አካል ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከማናቸውም የፖለቲካ ድርጅት ያልወገነ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከኢትዮጵያ ውጭ ሕጋዊ ዓላማን ለማሳካት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ አካል ሲሆን፣ የሙያ ማኅበራትን፤ የብዙኃን ማህበራትን እና የድርጅቶች ኅብረቶችን ይጨምራል፡፡
 5. “የምርጫ አስፈጻሚ” ማለት በየደረጃው ምርጫን ለማስፈፀም በቦርዱ የሚመደብ ሰው ነው፡፡
 6. “የፖለቲካ ድርጅት” ወይም “የፖለቲካ ፓርቲ” ማለት ዜጎች ተደራጅተው የሚመሠርቱት የፖለቲካ ፕሮግራም በማውጣት በሀገር አቀፍ፣ በክልል ወይም ከክልል በታች ባለ ደረጃ በምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ በምርጫ ህግ መሠረት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው።
 7. “የመራጮች ትምህርት” ማለት ዜጎች የምርጫን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ተገንዝበው በፍላጎትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንዲሁም በምርጫው ሂደት ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን በቂ መረጃ የሚያገኙበት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በጸዳ መንገድ የሚሰጥ ትምህርትና ስልጠና ነው፡፡
 8. “የትምህርት ተቋም” ወይም “ተቋም” ማለትስልጣንባለውአካልየእውቅናፈቃድየተሰጠውዩኒቨርሲቲ፣ዩኒቨርሲቲኮሌጅ፣ኮሌጅወይምየመምህራንማሰልጠኛተቋምማለትነው፡፡
 9. “አሰልጣኝ” ማለትየመራጮችትምህርትየማስተማርፈቃድበቦርዱየተሰጠውድርጅትየመራጮችትምህርትእንዲሰጥለቦርዱአሳውቆየሚያሰማራውግለሰብነው።
 10. “ሰው” ማለትየተፈጥሮወይምበህግየሰውነትመብትየተሰጠውአካልወይምድርጅትነው።

አንቀጽ 3. የተፈጻሚነትወሰን

ይህ መመሪያ በመላ ሀገሪቱ በምርጫ ህጉ መሠረት በሚካሄድ በማንኛውም ምርጫ ወይም ህዝበ ውሳኔ ዙሪያ የመራጮች ትምህርት በሚሠጡ የሀገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማት እና አሰልጣኞቻቸው ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

አንቀጽ 4. የፆታ አገላለፅ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በሴት ፆታ የተደነገገው የወንድንም ፆታ ያካትታል።

ምዕራፍ ሁለት

የመራጮች ትምህርት ስለመስጠት

አንቀጽ 5. የመራጮችትምህርትየመስጠትኃላፊነት

 

 1. በምርጫህጉእናበዚህመመሪያመሠረትየመራጮችትምህርትየመስጠትኃላፊነትየቦርዱነው።
 2. ቦርዱመራጮችበቂምርጫነክግንዛቤየሚያገኙበትንስልትበመቀየስናየተለያዩየመገናኛዘዴዎችንበመጠቀምየመራጮችትምህርትይሰጣል፡፡
 3. ቦርዱየመራጮችትምህርትመስጠትእንዲችሉህጋዊሰውነትላላቸውአገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅቶችናየትምህርትተቋማት፤የማስተማርፈቃድይሰጣል፡፡
 4. በአዋጁመሠረትበቦርዱምሆነበቦርዱፈቃድበሚሰጣቸውተቋማትናድርጅቶችየሚሰጥትምህርትናስልጠናቦርዱከሲቪልማህበራትጋርበመመካከርየሚያዘጋጀውየማስተማሪያሰነዶችንመሠረትያደረገይሆናል፡፡
 5. የቦርዱየክልልቅርንጫፍጽሕፈትቤትቦርዱበሚሰጠውየስራመመሪያመሰረትፈቃድከተሰጣቸውየሲቪልማህበረሰብድርጅቶችእናተቋማትጋርበመተባበርየመራጮችትምህርትይሰጣል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል፣ይቆጣጠራል።
 6. ማንኛውም ሰው ያለቦርዱ ፈቃድ የመራጮች ትምህርትና መረጃ መስጠት አይችልም። ያለ ፈቃድ የመራጮች ትምህርት በሚሰጥ ማንኛውም ሰው ላይ የዚህ መመሪያ አንቀጽ 7

ድንጋጌዎችተፈጻሚይሆናሉ፡፡

 

አንቀጽ 6. የቦርዱየክልልቅርንጫፍጽሕፈትቤትኃላፊነት

 

 1. የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 5 በሚያደርገው ክትትል እና ቁጥጥር የቦርዱ ፈቃድ ሳይኖረው የመራጮች ትምህርት የሚሰጥ ድርጅት ወይም ተቋም መኖሩን እራሱ በሚያደርገው ማጣራት ወይም በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት ያረጋገጠ እንደሆነ ድርጅቱ ወይም ተቋሙ የማስተማር ፈቃድ በቦርዱ እንዲሰጠው እንዲያመለክት በደብዳቤ ያሳውቀዋል፤ የደብዳቤውን ግልባጭ ለቦርዱ ይልካል፡፡
 2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት ከቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በተገለጸለት መሠረት ድርጅቱ ወይም ተቋሙ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የፈቃድ ጥያቄውን ሳያቀርብ የቀረ እንደሆነ ይህንኑ ለቦርዱ ያሳውቃል፤ የቦርዱ ውሳኔ እስኪደርሰው ድረስ ድርጅቱ የማስተማር

 

ስራውን በጊዜያዊነት እንዲያቋርጥ ሊያዘው ይችላል፡፡ ድርጅቱ የማስተማር ተግባሩን ያላቋረጠ ከሆነ ጽ/ቤቱ በአካባቢው ላለ የሲቪል ማህበራት ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም የሲቪል ማህበሩን ለመዘገበው ወይም ለሌላ ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም ያሳውቃል፡፡

 1. የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በመራጮች ትምህርት የተከሰቱ ችግሮችን በመለየት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ለቦርዱ መረጃ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን የተከሰተው ችግር አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው ከሆነ ችግሩ እንደተከሰተ ወዲያውኑ ተገቢውን መረጃ ለቦርዱ መላክ አለበት፤ ቦርዱ ከደረሰው መረጃ በመነሳት በመራጮች ትምህርት ዙሪያ የተፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ በየወቅቱ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት እርምጃ ይወስዳል።

 

አንቀጽ 7. የመራጮችትምህርትየማስተማርፈቃድስለመጠየቅ

 1. በምርጫ ህጉ ወይም በዚህ መመሪያ አንቀጽ 8 መሠረትየመራጮችትምህርትየማስተማርመስፈርትንየሚያሟላማንኛውምሀገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅትወይምየትምህርትተቋም፦

ሀ)      ቦርዱ ለዚሁ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት እና ማስረጃዎቹን በማያያዝ    ለቦርዱማቅረብአለበት።

ለ)       የመራጮች ትምህርት ለማስተማር የመደበውን የገንዘብ መጠን ፣ የሚያስተምርበትን ቋንቋ ፣ ለምን ያህል ዜጎች ትምህርቱን ለመስጠት እንዳቀደ፣ የሰው ኃይል አመዳደቡን፣ እና የማስተማር ሥራውን የሚያካሂድበትን ክልል፣ ከተማ፣ ክፍለ ከተማ፣ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ያካተተ ሰነድ በማዘጋጀት ከማመልከቻው ጋር አያይዞ ለቦርዱ ማቅረብ አለበት።

ሐ)  ለመራጮች ትምህርት በመሪነት፣ በአስተባባሪነት፣  እና በመሳሰሉ ተግባራት የሚያሠማራቸውን ሰዎች ዝርዝር ፣ እንዲሁም እነዚሁ ግለሰቦች የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑ መሆኑን የሚያረጋግጥ በሃላፊ የተፈረመ ቃለ መሃላ ፣ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 መሠረት ቦርዱ ባዘጋጀው ቅጽ የተሟላ የአሰልጣኞች ዝርዝር(ለገጽ ለገጽ ስልጠና ብቻ ተፈጻሚ የሚሆን) እንዲሁም  ተያያዥማስረጃዎችንአባሪበማድረግከማስተማርፈቃድመጠየቂያማመልከቻውጋርለቦርዱማቅረብአለበት።

መ)  በዚህ አንቀጽ ከንኡስ አንቀጽ 1(ሀ) እስከ 1(ሐ) የተደነገጉት ቢኖሩም ድርጅቱ ወይም ተቋሙ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች ብቻ ለሚሰጠው ትምህርት ወይም ትምህርቱን የሚሰጠው ሙሉ በሙሉ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች ብቻ ከሆነ  የመራጮችትምህርትለማስተማርየመደበውንየገንዘብመጠን፣ትምህርቱንለማስተላለፍየሚጠቀምበትንቋንቋእናበዚህንኡስአንቀጽውስጥበተጠቀሱትየመገናኛብዙሃንበመጠቀምሊያቀርብያቀደውንትምህርትናያቀራረብዘዴየሚያሳይሰነድከማመልከቻውጋርማቅረብ

አለበት፡፡

 1. የመራጮችትምህርትለማስተማርከቦርዱፈቃድየሚጠይቅሀገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅትበህጋዊነትተመዝግቦበስራላይመሆኑንየሚያሳይማስረጃለቦርዱማቅረብአለበት።
 2. በዚህአንቀጽመሠረትየሚቀርብማመልከቻበድርጅቱዋናኃላፊፊርማእናበድርጅቱማህተምተረጋግጦመቅረብአለበት።
 3. ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የመራጮች ትምህርት ፈቃድ የመስጠት ሃላፊነትን ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችሊሰጥይችላል፡፡

አንቀጽ 8. ስለፈቃድ አሠጣጥ

 1. ቦርዱየመራጮችትምህርትየማስተማርፈቃድጥያቄሲቀርብለትጥያቄውንያቀረበውድርጅት፦

ሀ)በመተዳደሪያደንቡመሠረትበምርጫናከምርጫጋርተያያዥነትባላቸውጉዳዮችላይየሚሰራናበህግተመዝግቦየሚንቀሳቀስአገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅትወይምየትምህርትተቋምመሆኑን፤

ለ)           በዚህመመሪያለመራጮችትምህርትየተቀመጠውንመስፈርትየሚያሟላመሆኑን፣

ሐ)         ተግባሩን ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ያለው መሆኑን፤

መ)  ድርጅቱ፣ የድርጅቱ መሪም ሆነች በድርጅቱ የተመደበችው አሰልጣኝ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነች መሆኑን በማጣራትና ቦርዱ ያዘጋጀውን የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ ሥነ ምግባር መመሪያ ስለመቀበላቸው ድርጅቱንና አሰልጣኞቹን በማስፈረም የማስተማር ፈቃድና የአሰልጣኝ መለያ መታወቂያ ይሰጣል፡፡

 

 1. ቦርዱበዚህአንቀጽየተዘረዘሩትንለማያሟላድርጀትፈቃድአይሰጥም።አለመፍቀዱንምከነምክንያቱበጽሑፍለአመልካችያሳውቃል፡፡
 2. የመራጮችትምህርትየሚሰጥድርጅትወይምተቋምከፖለቲካፓርቲወይምየፖለቲካወገንተኝነትንከሚያመላክትማንኛውምምንጭወይምከሕገወጥምንጭገንዘብበመቀበልለመራጮችትምህርትማዋልየለበትም፡፡
 3. የመራጮች ትምህርት የሚሰጥ ተቋም የመራጮች ትምህርት ዕቅድ እና የማስተማሪያ ቁሳቁስ አዘጋጅቶቦርዱባፀደቀውየመራጮችትምህርትማኑዋልመሠረትሥራላይማዋልአለበት።

 

አንቀጽ 9.  የመራጮች ትምህርት አሰልጣኝ

 1. ማንኛዋምየመራጮችትምህርትለማስተማርየምትሰማራአሰልጣኝ፦

ሀ)       እድሜዋ 21 ዓመትናከዚያበላይየሆነ፣

ለ)       የመምረጥናየመመረጥመብቷበህግያልተገደበ፣

ሐ)  ተግባሯን ለመፈፀም ሙያዊ ብቃት፣ ልምድና ከመራጮች ትምህርት ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት   መስኮች ዝግጅት ያላት፣

መ)     የምታስተምርበትንአካባቢቋንቋየምትችል፣

ሠ)      ቀደምሲልየመራጮችትምህርትከማስተማርጋርበተያያዘበቦርዱያልታገደችወይምበፍርድቤትያልተፈረደባትመሆንአለባት።

 1. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1(መ) የተነገረውቢኖርምየመራጮችትምህርትየሚሰጥበትንየአካባቢቋንቋየምትችልአሰልጣኝበማትገኝበትአካባቢትምህርቱበአስተርጓሚእገዛእንዲሰጥቦርዱሊፈቅድይችላል፡፡
 2. ማንኛውም የማስተማር ፈቃድ የተሰጠው ድርጅትም ሆነ አሰልጣኝ ከስነ ምግባር ደንቡና ከገባው ግዴታ ውጭ ሲንቀሳቀስ/ስትንቀሳቀስ ከተገኘ/ች ቦርዱ እንደአግባብነቱ ለግለሰቧም ሆነ ለወከላት ድርጅት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ስህተቱ እንዲታረም ለማድረግ ወይም ፈቃድ እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡

 

አንቀጽ 10. አሰልጣኞችን ስለማሳወቅማንኛውምየመራጮችትምህርትንለመስጠትፈቃድየተሰጠውድርጅትየገጽለገጽትምህርትየሚሰጥከሆነ፦

 1. የመራጮችትምህርትየሚሰጡለትአሰልጣኞችይኖሩታል፤የአሰልጣኞቹንምማንነትለቦርዱማሳወቅአለበት።
 2. ድርጅቱየአሰልጣኞቹንዝርዝርለማሳወቅየሚጠቀመውቅፅበቦርዱየተዘጋጀይሆናል።

 

አንቀጽ 11. አሰልጣኝ ስለመለወጥ

ማንኛውም የመራጮች ትምህርት ገጽ ለገጽ ለመስጠት ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት አሰልጣኙን ሲለውጥ በ7 ቀናትውስጥየሚተካውንሰውለቦርዱበማሳወቅይሁንታማግኘትይኖርበታል።

 

አንቀጽ 12. የማስተማርፈቃድእናመታወቂያካርድስለመስጠት

 1. ቦርዱ በምርጫ ህጉ አንቀጽ 125 ንዑስ አንቀጽ 1 እናበዚህመመርያመሠረትፈቃድለሰጠውድርጅትየማስተማርፈቃድእናአሰልጣኝካለውለአሰልጣኟመለያመታወቂያካርድይሰጣል።
 2. ማንኛውምየመራጮችትምህርትየማስተማርፈቃድምሆነየመታወቂያካርድአገልግሎትየሚሰጠውለአንድየምርጫወቅትብቻይሆናል።

አንቀጽ 13. የመራጮችትምህርትአሰጣጥ

 1. ቦርዱለመራጮችትምህርትየሚሆንየፅሁፍ፣የምስልወይምየድምፅእናየመሳሰሉትንማስተማሪያዎችበማዘጋጀትወይምበሌላሰውእንዲዘጋጅበማድረግወይምሌላሰውአዘጋጅቶየሚሰጠውንጽሁፍ፣ድምፅወይምምስልይዘትእናብቃትበማረጋገጥለማስተማሪያነትእንዲውልሊያደርግይችላል።
 2. ማንኛውምየመራጮችትምህርትለመስጠትፈቃድየተሰጠውድርጅትወይምተቋምየሚከተለውንየትምህርትአሰጣጥበስራላይሊያውልይችላል፣

ሀ)          የገፅ ለገፅ ስልጠና ለሚመለከታቸው አካላት ወይም ሰዎች አዘጋጅቶ መስጠት፣

እና/ወይም፣

ለ)የተለያየየማስተማሪያፅሁፍ፣ምስል፣ድራማናየመሳሰለውንበማዘጋጀትእናእንዲዘጋጅበማድረግበሬድዮ፣በቴሌቪዥን፣በጋዜጣ፣በመጽሔት፣በፖስተር፣በቢልቦርድ፣በበራሪጽሁፍ፣በኢንተርኔትአውታሮችእናበመሳሰሉመገናኛዎችእንዲወጣማድረግ፡፡

 1. አንድ የማስተማሪያ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ወይም ተቋም በዚህ ንኡስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሀ) እና (ለ) መሠረትየተመለከቱትንየማስተማሪያዘዴዎችበስራላይመዋላቸውንመከታተልየሚያስችለውየአሰራርስርአትይዘረጋል፡፡አስፈላጊሲሆንምየማስተካከያእርምጃይወስዳል፡፡ቦርዱምይህንንክትትልየሚያደርግበትማንዋልወደፊትየሚያወጣይሆናል፡፡
 2. ቦርዱየመራጮችትምህርትናየመሳሰሉትንየማስተማሪያዘዴዎችበተለያዩቋንቋዎችበማዘጋጀትወይምበመተርጎምመራጩስለምርጫእንቅስቃሴበቂግንዛቤእንዲያገኝ ያደርጋል።
 3. አንድ የማስተማሪያ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ወይም ተቋም የሚሰጠው የመራጮች ትምህርት በመምረጥም ሆነ በመመረጥ እንዲሁም ሌሎች ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመጠቀም ሴቶች ከወንዶች እኩል በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠ መብት ያላቸው መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ማስተማር ይኖርበታል፤ ድርጅቱ ወይም ተቋሙ ወይም የሚያሰማራቸው አሰልጣኞች የሚጠቀሟቸው ማናቸውም የማስተማሪያ ዘዴዎችም ሆነ ቋንቋዎች፣ ሰነዶችና ቁሳቁሶች የሴቶችን እኩልነት የሚያጎለብቱ፤ በማህበረሰቡ ውስጥ የነበረውን የተዛባ አመለካከት የማያንጸባርቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 4 የተነገረውግዴታአካልጉዳተኝነትንበሚመለከትምተፈጻሚ ይሆናል፡፡
 5. ማንኛውም በምርጫ ህጉ ወይም በዚህ መመሪያ አንቀጽ 9 መሠረትቦርዱበሚሰጠውፈቃድመሠረትየመራጮችትምህርትየሚሰጥድርጅትወይምተቋምለቦርዱባቀረበውየማስተማርእቅድእናበቦርዱበተዘጋጁወይምተቀባይነትባገኙሰነዶችይዘትመሠረትማስተማርአለበት።
 6. ማንኛውምድርጅትወይምተቋምበቦርዱከተዘጋጀውውጭየማስተማሪያሰነድየሚገለገልከሆነበቦርዱከተዘጋጁሰነዶችጋርየተጣጣሙመሆናቸውንየማረጋገጥኃላፊነትአለበት፡፡

አንቀጽ 14. የመራጮችትምህርትሊሰጣቸውየሚችሉሰዎች

 1. ቦርዱየመራጮችትምህርትየሰልጣኞችንየትምህርትደረጃናሌሎችተገማችጉዳዮችንከግምትበማስገባትእንዲዘጋጅያደርጋል።
 2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌእንደተጠበቀሆኖቦርዱለመራጩህዝብ፣በየደረጃውለሚገኙየምርጫአስፈጻሚዎች፣ለምርጫታዛቢዎች፣ለጋዜጠኞች፣በሀገሪቱህግመሠረትተመዝግበውለሚንቀሳቀሱየፖለቲካፓርቲዎች፣ለመንግስታዊድርጅቶች፣ለሙያማህበራትናለሕዝባዊድርጅቶችምርጫንእናመራጮችንየሚመለከትትምህርትይሰጣልወይምበዚህመመሪያመሠረትበሌላበህግአግባብበተፈቀደለትድርጅትእንዲሰጥሊያደርግይችላል።

ምዕራፍ ሦስት

የመራጮች ትምህርት የሚሰጡ ሰዎች መከተል ስለሚኖርባቸው ስነምግባር

አንቀጽ 15. የማስተማር ኃላፊነትን በተገቢው መንገድ ማከናወን

ማንኛውምየመራጮችትምህርትለመስጠትፈቃድየወሰደድርጅትወይምድርጅቱያሰማራትአሰልጣኝ፦

ሀ)                        በመራጭነትየእድሜክልልውስጥያለማንኛውምዜጋየመምረጥመብቱን እንዲጠቀም፣

ለ)መራጮችበፖለቲካፓርቲዎችናበእጩዎችየሚደረጉየምርጫቅስቀሳዎችንበንቃትእንዲከታተሉእንዲሁምየሚቀርቡአማራጭፖሊሲዎችንናፕሮግራሞችንእንዲረዱአስፈላጊከሆነምማብራሪያየመጠየቅመብትእንዳላቸው፣

ሐ) መራጮችየሚቀርቡአማራጭፖሊሲዎችንናፕሮግራሞችንበጥንቃቄከተረዱበኋላለሚፈልጉትየፖለቲካፓርቲወይምእጩድምጽእንዲሰጡ፣

መ) መራጮች ሕግን ማክበር እና ግጭትን ከሚቀሰቅሱ ወይም ሰላምን ከሚያደፈርሱ ድርጊቶች መቆጠብ እንዳለባቸው ማስተማር አለበት/አለባት፡፡

 

አንቀጽ 16. ገለልተኛስለመሆን

 1. ማንኛውምየመራጮችትምህርትለመስጠትፈቃድየወሰደድርጅትወይምድርጅቱያሰማራትአሰልጣኝ፦

ሀ)         ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ገለልተኛ መሆን አለበት/አለባት፣

ለ)         ማንኛውንም የፖለቲካ ድርጅት ወይም እጩ ከመወገን፣ በመቃወም ወይም በመንቀፍ መንቀሳቀስ የለበትም/የለባትም፤

ሐ)        ማንኛውም ሌላ ሰው አንዱን እንዲደግፍ ሌላውን እንዲቃወም፣ እንዲነቅፍ ወይም እንዲያጥላላ  መቀስቀስ የለበትም/የለባትም።

 

 1. ማንኛውም የመራጮችን ትምህርት ለመስጠት ፈቃድ የወሰደ ድርጅት ወይም አሰልጣኝ ፡-

ሀ)  በምርጫእንቅስቃሴየሚሳተፍየፖለቲካድርጅትን፣የእጩዋንወይምየግልእጩንማንኛውንምአይነትደጋፊወይምተቃራኒምልክት፣መፈክር፣ወይምየመሳሰለውንበመለጠፍ፣በመስቀል፣በማውለብለብወይምበማንኛውምመልኩይዛመገኘት

የለባትም።

ለ)     እየተካሄደባለምርጫላይየግልአስተያየትከመስጠትየመቆጠብግዴታአለባት።

ሐ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የምትደግፈውን ፓርቲ ወይም እጩ በአደባባይ መግለጽም ሆነ ደጋፊነቷን የሚያስጠረጥር ድርጊት መፈጸም የለባትም፤

መ)   ፍጹምገለልተኛየመራጮችትምህርትየመስጠትግዴታአለባት።

 

አንቀጽ 18. የጥቅምግጭት

 

 1. ማንኛውምየመራጮችትምህርትለማስተማርፈቃድየወሰደሀገርበቀልየሲቪልማህበረሰብድርጅትወይምተቋምበንብረት፣በገንዘብ፣በዝምድናወይምበማንኛውምሌላሁኔታከምርጫተወዳዳሪእጩወይምየፖለቲካድርጅትጋርየጥቅምግንኙነትሲያጋጥመውጉዳዩንዘርዝሮወዲያውኑለቦርዱማሳወቅአለበት።
 2. ቦርዱየጥቅምግጭትያጋጠመውሰውሪፖርትሲደርሰውበሌላአካባቢእንድታስተምር፣ማስተማሯንእንድትቀጥልወይምሌላአስፈላጊነውየሚለውንትዕዛዝሊሰጥይችላል።

 

አንቀጽ 19. እውነተኝነትማንኛውምበምርጫህጉእናበዚህመመሪያመሠረትየማስተማርፈቃድየተሰጠውደርጀትወይምተቋምወይምአሰልጣኝ፦

 1. በማንኛውምጊዜየምታስተምረውየመራጮችትምህርት፣የምታሰራጨውመረጃ፣ወይምለቦርዱየምታቀርበውሪፖርትበእውነተኛማስረጃየተደገፈመሆንአለበት።

 

 1. የምታስተምረውየመራጮችትምህርትዝግጅት፣ዕቅድእናየትምህርትአሠጣጥቦርዱባፀደቀውየትምህርትይዘትናቅደምተከተልእናየምርጫዑደትመሠረትመሆንይኖርበታል።ይህንንየሚቀይርከሆነየቦርዱንይሁንታማግኘትይኖርበታል፡፡
 2. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 21(3) መሰረትለመራጮችትምህርትከቦርዱየገንዘብድጋፍያገኘከሆነገንዘቡንለታቀደለትዓላማብቻማዋልአለባት።

 

አንቀጽ 20. ህግ ማክበር

 1. ማንኛውም የመራጮች ትምህርት የማስተማር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ወይም ድርጅቱ የመደባት አሰልጣኝ ህገ መንግሥቱን፣ የምርጫ ህጉን እና ሌሎች የሀገሪቱን ህጎች እንዲሁም በዚህ ስነምግባር መመሪያ የገባችውን ግዴታ ማክበር አለባት።
 2. ማንኛውምየመራጮችትምህርትለማስተማርህጋዊፈቃድየተሰጠውደርጅትወይምአሰልጣኝበዚህመመሪያከገባውየስነምግባርግዴታውጪሲንቀሳቀስከተገኘቦርዱእንደየሁኔታው፤

ሀ)      ማስጠንቀቂያበመስጠትስህተቱንእንዲያርምለማድረግ፣ወይም

ለ)  የማስተማርፈቃድእናየአሰልጣኝመታወቂያወረቀትንእስከመሰረዝሊደርስየሚችልእርምጃሊወስድይችላል።

 1. ማንኛውም የመራጮች ትምህርት እንዲሰጥ ፈቃድ የተሰጠው ደርጅት ወይም ተቋም

ሀ)  የመራጮችትምህርትለማስተማርየተሰጠውንየተረጋገጠየፈቃድቅጂእናመለያመታወቂያየመያዝእናአግባብባለውሰውሲጠየቅምማሳየት፣

ለ)        በህግመሠረትብቻየማስተማር፣

ሐ)  የምርጫሂደትበትክክልእንዳይካሄድከሚያደርግእንቅስቃሴእናከተሰጠውፈቃድውጭከመንቀሳቀስየመቆጠብ፣

መ)        በዚህ መመሪያ በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

ፍቃድየተሰጠውድርጅትየመደባትአሰልጣኝህገወጥድርጊትበመፈፀሟወይምይህንንመመርያበመጣሷምክንያትቦርዱማስጠንቀቂያየሰጣትእንደሆነአፋጣኝማስተካከያበመውሰድለቦርዱየማሳወቅግዴታአለበት።

አንቀጽ 21. የገንዘብምንጭ

 1. ማንኛውምደርጅትወይምተቋምየመራጮችትምህርትማካሄጃወጪንበራሱይሸፍናል።
 2. የመራጮችትምህርትየሚሰጡድርጅቶችወይምተቋማትለዚሁተግባርየሚያስፈልጋቸውንየገንዘብድጋፍለማግኘትለሚያደርጓቸውጥረቶችበሚያቀርቡትጥያቄመሰረትቦርዱየድጋፍደብደቤሊጽፍላቸውይችላል፡፡
 3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተነገረውእንደተጠበቀሆኖቦርዱየተደራሽነትችግርባለባቸው

አካባቢዎችለሚሰጠውየመራጮችትምህርትበትብብርለሚሰሩድርጅቶችወይምተቋማት በስምምነትላይየተመሰረተየገንዘብድጋፍሊሰጥይችላል፡፡

አንቀጽ 22. ሪፖርት ስለማቅረብ

 1. ማንኛውም የመራጮች ትምህርት ለማስተማር ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ፡-

ሀ. ማስተማሩን እንዳጠናቀቀ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሥራ ክንውን ሪፖርትን እና በቦርዱ  የሚጠየቁተገቢሰነዶችንለቦርዱማቅረብአለበት።

ለ. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በየሶስት ወሩ ለቦርዱ ማቅረብ አለበት።

ሐ. በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 1(ሀ) እና (ለ) ከተጠቀሱትሪፖርቶችጋርእንቅስቃሴውንየሚያሳይበፅሁፍ፣የቪዲዮ፣የምስልእናየድምፅሰነዶችንበአባሪማስረጃነትማቅረብይኖርበታል፡፡

መ. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም በማንኛውም ጊዜ በቦርዱ ሲጠየቅ ሪፖርት ማቅረብ አለበት።

 1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 21(3) መሰረትየገንዘብድጋፍከቦርዱየሚያገኝድርጅትወይምተቋምከሚያቀርበውየስራክንውንሪፖርትጋርየተሰጠውንየገንዘብድጋፍአጠቃቀምሪፖርትማቅረብይኖርበታል፡፡

ምዕራፍ አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

አንቀጽ 23. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውምሰውይህንመመሪያበስራላይለማዋልየመተባበርግዴታአለበት።

አንቀጽ 24. ቅጣት

በዚህመመሪያየተደነገገውንየስነምግባርግዴታያልፈፀመወይምየጣሰሰውአግባብባለውህግመሰረትይቀጣል።

አንቀጽ 25. ማኑዋል ስለማውጣት

ቦርዱይህንንየስነምግባርመመሪያበስራላይለማዋልየሚያስችልዝርዝርየአፈጻጸምማኑዋልሊያወጣይችላል።

አንቀጽ 26. የተሻሩ ህጎች እና አሠራሮች

ከዚህመመሪያጋርየሚቃረንማንኛውምመመሪያወይምአሠራርበዚህመመሪያበተሸፈኑጉዳዮችላይተፈጻሚአይሆንም።

አንቀጽ 27. የተፈጻሚነት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ምጀምሮየፀናይሆናል።

 

ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

Exit mobile version