Directives

የሃይማኖትና እምነት ድርጅቶች፣ ማህበራትን ለመመዝገብና ተዛማጅ አገልግሎት ለመስጠት የወጣ መመሪያ ቁጥር 19-2012

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ14/1/ሸ/ቀ/ መሰረት የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት፣ የሃይማኖትና እምነት ድርጅቶችንና ማህበራትን ምዝገባና ተዛማጅ አገልግሎቶች አሰጣጥን ህጋዊ መሰረት ለማስያዝ፣ ከክሌሎች ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ፣ የሃይማኖትና እምነት ተቋማት አመሰራረት ሂደት ለተለያዩ ችግሮች አጋላጭነቱና ተጋላጭነቱ  እየጎላ በመምጣቱ  በህጋዊ መንገድ መከላከል በማስፈለጉ፣ ህገ-ወጥ የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለከላከልና ለመቀነስ፣ ከአምልኮና ስብከት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮችን ስርአት ማስያዝ በማስፈለጉ፣ የሰብኣዊ ልማት /የበጎ አድራጎት/ ስራዎችን ከመንፈሳዊ ስራዎች መለየት አስፈላጊ በመሆኑ፣ አዳዲስ የሃይማኖት፣ የእምነት ድርጅትና ማህበርን ከመመስረት ጋር የተያያዘ የመልካም አሰተዳደር ጥያቄዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመበራከቱና ህጋዊ ስርዓት ማስያዝ በማስፈለጉ፣ የሐይማኖት ተቋማት ለሀገራችን ሠላም፣ ልማት እና እድገት የሚያበረክቱትን አስተዋፅዖ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህንኑ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል ነው፡፡

 

በአጠቃላይ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን የሐይማኖት ነፃነት፣ እኩልነት፣ የመንግስትና  የሐይማኖት መለያየት እና የመደራጀት መብት  እንደተጠበቀ ሆኖ አሰራራቸው ከህገ-መንግስቱና ከሌሎች የሃገሪቱ ህጎች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እንዲቀጥልና በግልፅነትና ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠትና ለማግኘት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

DOWNLOAD .pdf

1 reply »

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.