Directives

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአጀንዳ አቀራረፅ የሚመራበትን አሠራር ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 5/2000 ዓ.ም

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

 የአጀንዳ አቀራረፅ የሚመራበትን አሠራር ለመወሰን

 የወጣ መመሪያ  ቁጥር 5/2000 ዓ.ም

 ምዕራፍ አንድ

 ጠቅላላ

 አንቀፅ 1

 አውጪው ባለስልጣን

የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 3/1998 ዓ.ም. አንቀፅ 143 ንዑስ አንቀፅ 7 እና አንቀፅ 191 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።

 አንቀፅ 2

 አጭር ርዕስ

 

ይህ መመሪያ «የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአጀንዳ አቀራረፅ መመሪያ ቁጥር 5/2000 ዓ.ም» ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

 አንቀፅ 3

 ትርጓሜ

 

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሠጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡- 1.    «ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.» ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው።

 1. «ምክር ቤት» ማለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡
 2. «ሁለቱ ምክር ቤቶች» ማለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ናቸው።
 3. «ደንብ» ማለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሠራር እና የአባላት የስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 3/1998 ዓ.ም ነው።
 4. «አፈ-ጉባኤ» ማለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ነው።
 5. «የቀድሞ አፈጉባኤ» ማለት የስራ ዘመኑን ከሚጀምረው ምክር ቤት በፊት በነበረው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ ሰው ነው።
 6. «ኮሚቴ» ማለት የምክር ቤቱን ተግባር ለማከናወን እንደሁኔታው በምክር ቤቱ የሚቋቋም የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ወይም አስተባባሪ ወይም ቋሚ ወይም ጊዚያዊ ኮሚቴ ነው።
 7. «አማካሪ ኮሚቴ» ማለት በምክር ቤቱ ደንብ አንቀፅ 142 መሠረት የተደራጀው የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ ነው።
 8. «የፓርላማ ቡድን» ማለት አንድ ፓርቲ ወይም በምርጫ ክልሎች እርስ በርሳቸው ያልተወዳደሩ፣ በአንድ ፖለቲካ ፕሮግራም የተወዳደሩ ፓርቲዎች አባላት ስብስብ ሆኖ ከ10 የማያንስ መቀመጫ ያለውን ወይም ያላቸውን ፓርቲ ወይም ፓርቲዎች የያዘ ነው።
 9. «የመንግሥት አጀንዳ» ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለምክር ቤት የሚቀርብ ማንኛውም አጀንዳ ነው፡፡
 10. «አባል» ማለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነው፡፡
 11. «ሰው» ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሠጠው አካል ነው።

 አንቀፅ 4

 አላማ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአጀንዳ አቀራረፅ አባላቱን እና የፓርላማ ቡድኖችን የሚያሳትፍ ግልፅ አሠራርን በመዘርጋት ምክር ቤቱ የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ማስቻል ነው፡፡

 ምዕራፍ ሁለት

 ስለ ምክር ቤቱ የአጀንዳ አቀራረፅ

 አንቀፅ 5

 አጀንዳ የማመንጨት ስልጣን

 

ይባ ንዳ

 

 1. በመንግስት፣
 2. በአፈጉባኤው፣
 3. በኮሚቴዎች፣
 4. በምክር ቤት አባላት እና
 5. በፓርላማ ቡድን ሊሆን ይችላል።

አንቀፅ 6

 አጀንዳ የማፅደቅ ስልጣን

 1. ምክር ቤቱ የሚወያይበት ማንኛውም አጀንዳ የሚፀድቀው በአማካሪ ኮሚቴ ይሆናል።
 2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው ቢኖርም በዚህ መመሪያ አንቀፅ 9 እና በደንቡ ውስጥ በተለየ ሁኔታ የተደነገጉት ጉዳዮች በአማካሪ ኮሚቴ ሳይፀድቁ ለምክር ቤቱ በአጀንዳነት ይቀርባሉ፡፡

አ ንቀፅ 7

 አማካሪ ኮሚቴ አጀንዳ ስለሚያፀድቅበት ሁኔታ

 1. አማካሪ ኮሚቴ ለውይይት የሚቀርበውን አጀንዳ በስምምነት ይወስናል። ስምምነት የተደረሰበት አጀንዳ በምክር ቤቱ መጽደቅ ሳያስፈልገው በቀጥታ ለውይይት ይቀርባል።
 2. በአማካሪ ኮሚቴ ስምምነት ያልተደረሰበት አጀንዳ በአፈጉባኤው አማካኝነት ለምክር ቤቱ ቀርቦ በአባላት አንድ ሶስተኛ ድምፅ ከተደገፈ በቀጥታ ለውይይት ይቀርባል።
 3. በማንኛውም ጊዜ የመንግስት አጀንዳ ቅድሚያ ተሰጥቶት ለውይይት ይቀርባል።

 

አ ንቀፅ 8

 በአማካሪ ኮሚቴ ስምምነት ያልተደረሠበት አጀንዳ

 ለምክር ቤቱ የሚቀርብበት አሠራር

 

 1. አፈጉባኤው፤ በአማካሪ ኮሚቴ ስምምነት ያልተደረሠበትን አጀንዳ ከነምክንያቱ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡
 2. ስምምነት ባልተደረሠበት አጀንዳ ላይ የተለያየ አስተያየት ያንፀባረቁ ቡድኖች ሀሳባቸውን በአጭሩ እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡
 3. ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ አጭር ውይይት ሊያደርግ ይችላል፡፡
 4. አፈጉባኤው፤ በራሱ ወይም ከአባላት በሚቀርብ ሞሽን በቂ ውይይት ተደርጓል ብሎ ሲያምን በጉዳዩ ላይ ድምፅ እንዲሠጥ ያደርጋል፡፡
 5. በአንቀጽ 9/3/ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዳዩ በአጀንዳነት እንዲያዝ ምክር ቤቱ ከወሰነ፤ የእለቱ የምክር ቤቱ የአጀንዳ ነጥብ በመሆን ለምክር ቤቱ ውይይት ይቀርባል፡፡
 6. በምክር ቤቱ የውይይት ጊዜ አመዳደብ እና የተናጋሪ አመራረጥ መመሪያ መሠረት የውይይት ጊዜ እና የንግግር ጊዜ ይመደባል፡፡
 7. አፈጉባኤው፤ የተመደበውን የንግግር   ጊዜ  በጽ/ቤቱ  ሠራተኞች   አማካኝነት

ለሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት እና የተናጋሪ አባላትን ስም ዝርዝር እንዲያቀርቡ ያደርጋል፡፡

 አንቀፅ 9

 በአማካሪ ኮሚቴ ሳይፀድቁ ለም/ቤቱ

 የሚቀርቡ አጀንዳዎች

 1. በተቃዋሚዎች ቀን ምክር ቤቱ ውይይት የሚያደርግበት በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚቀርብ አጀንዳ በአማካሪ ኮሚቴ ውስጥ ያሉ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲ (የፓርላማ ቡድን) ተወካዮች ቅድሚያ የሚሰጡት የተቃዋሚ አጀንዳ ይሆናል፡፡ ሆኖም አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ (የፓርላማ ቡድን) ቢያንስ በዓመት 1 ጊዜ አጀንዳ የማስያዝ እድል ይኖረዋል፡፡
 2. በደንቡ አንቀፅ 11 ንዑስ አንቀፅ 2 የተጠቀሰውን የምክር ቤቱን የመክፈቻ ስነስርዓት የሚመለከት አጀንዳ በቀድሞው አፈጉባኤ ተቀርፆ ለምክር ቤቱ ይቀርባል፤
 3. በምክር ቤቱ ደንብ አንቀፅ 33 መሠረት በእለታዊ አጀንዳ ያልተቀረፀ ነገር ግን የአፈጉባኤውን ፍቃድ ያገኘ ለሕዝብ ጠቀሜታ ያለው አስቸኳይ ጉዳይ በአባላት ወይም በፓርላማ ቡድን ሲቀርብ በምክር ቤቱ ውይይት ይደረግበታል፤
 4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 የተጠቀሰው የአፈጉባኤውን ፈቃድ ያገኘ ሞሽን በምክር ቤቱ 50 አባላት ከተደገፈ ለውይይት ይቀርባል፤ ለውይይት የሚያስፈልገው ጊዜም በምክር ቤቱ የውይይት ጊዜ አመዳደብ እና የተናጋሪ አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 6/2000 መሠረት ይመደባል፡፡
 5. አፈ-ጉባኤው፤ የሚከተሉትን ጉዳዮች በአጀንዳነት ቀርፆ በቀጥታ ለምክር ቤቱ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ሀ/ ቃለ መሃላ ማስፈፀም፤

ለ/  በሀገሪቱ  ውስጥ  አሳዛኝ  ሁኔታ  የተከሠተ   መሆኑን   ለምክር   ቤቱ   መግለፅ፤

ሐ/  የሞቱ  አባላትን  ወይም  የመንግስት  ባለስልጣናትን   ወይም   የታዋቂ  ሰዎችን የህይወት  ታሪክ  ማቅረብ  እና  የህሊና  ፀሎት  እንዲደረግ  መጠየቅ፤

መ/ በአባላት የቀረበን ከአባልነት የመልቀቅ ጥያቄ ለምክር ቤቱ ማሳወቅ፤

ሠ/ የአንድ የምክር ቤት አባል የህግ ከለላ እንዲነሳ ያደረገው ጉዳይ

የቀረ ስለመሆኑ ለምክር ቤቱ ማሳወቅ፤

ረ/  ለወዳጅ አገራት ፓርላማ የሚላክ ወይም ከወዳጅ አገራት ፓርላማ የተላከ የደስታ ወይም የሀዘን መግለጫን ለምክር ቤቱ ማሳወቅ፤

ሰ/  የም/ቤቱ ቃለጉባኤ እንዲፀድቅ ለምክር ቤቱ ማቅረብ፤

እጅግ   አስቸኳይነቱ   በመንግስት   ታምኖበት   ለአፈጉባኤው   የተላከ አገራዊ የሠላም እና ደህንነት ጉዳይ፡፡

 1. አፈ-ጉባኤው፤ እንደሁኔታው የሚከተሉትን ጉዳዮች ለአማካሪ ኮሚቴው አቅርቦ የውይይት ጊዜ እንዲመደብ ካደረገ በኋላ በአጀንዳነት ቀርፆ ለምክር ቤቱ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

. የኮሚቴዎች ሊቃነመናብርትን፣ ምክትል ሊቃነመናብርትን እና አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርቦ ማስመረጥ፤

. ምክር ቤቱ በህግ መሠረት በሚወከልባቸው አካላት ውስጥ የሚወክሉ አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርቦ ማሠየም፤

. በደንቡ አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 3 መሠረት በአንድ አባል የተፈፀመን ከባድ ወይም ተደጋጋሚ የስነምግባር እና የስነስርዓት ጥፋትን አስመልክቶ በአፈጉባኤው የሚቀርብ ሞሽን፤

. በህገ መንግስቱ አንቀፅ 71/1/ መሠረት የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ለሁለቱ ምክር ቤቶች

. የሚያቀርበውን ንግግር፣ በንግግሩ ላይ የሚቀርቡ የድጋፍ እና የማሻሻያ ሞሽኖችን፤ የቀረበ ሀገራዊ ረቂቅ በጀት እና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ

. የሚሰጠው የበጀት መግለጫ፤

. በደንቡ አንቀፅ 70 መሠረት የሚቀርብ የበጀት ቅነሳ ሞሽን፤

በደንቡ    አንቀጽ    76/3/   መሠረት    ለም/ቤቱ   የሚቀርብ    የጠቅላይ ሸ. ሚኒስትሩ ሪፖርት፤

በደንቡ   አንቀፅ   47   በተዘረዘሩት   ምክንያቶች   በተያዘ   አጀንዳ   ላይ ቀ. የሚሰጥ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ የተላለፈ ጉዳይ፤

በደንቡ   አንቀጽ   76/4/   መሠረት   ለምክር   ቤቱ   በቀጥታ   የሚቀርብ በ.    የመንግስታዊ አካላት ሪፖርት፤

በደንቡ   አንቀፅ   87   መሠረት   ሚኒስትሮች   እና   ጠቅላይ   ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ቀርበው የቃል መልስ የሚሰጡበት አጀንዳ /ጉዳይ/።

 1. አፈ-ጉባኤው የሚከተሉት የሞሽን አይነቶች ማስታወቂያ ሳያስፈልጋቸው ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ሀ. የማሻሻያ ሞሽን (Amendment Motion)፣

ለ. ንዑስ ማሻሻያ ሞሽን (Sub Amendment Motion)፣

ሐ. የሥነ-ስርዓት ጥያቄ የሚያነሳ ሞሽን፣

መ. በእለታዊ አጀንዳ የተቀረጸን ጉዳይ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ወይም በተያዘው ቅደም ተከተል እንዲፈጸም ወይም ቅድሚያ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሞሽን፣

ሠ. በኮሚቴ በቀረበ ሪፖርት ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ  ውሳኔ  እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ሞሽን፣

ረ. አንድ ረቂቅ ህግ ወደ ኮሚቴ  ሳይመራ በቀጥታ  ወደ ሁለተኛ ደረጃ  ንባብ ተሸጋግሮ ዝርዝር ውይይት እንዲደረግበት የሚጠይቅ ሞሽን፣

ሰ. ምክር ቤቱ በአንድ አጀንዳ ላይ በቂ ውይይት ስላደረገ ውይይቱ ቆሞ ውሳኔ እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ሞሽን (Closure Motion)፣

ሸ. በአጀንዳ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ውሳኔው ለሌላ  ጊዜ  እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ሞሽን (Delay Motion)፣

 አንቀፅ 10

 ረቂቅ አጀንዳ ለአማካሪ ኮሚቴ

 ስለሚቀርብበት ሁኔታ

 1. በመንግሥት እና በፓርላማ ቡድን የሚመነጭ አጀንዳ በተጠሪዎቻቸው አማካኝነት ይቀርባል።
 2. በአፈጉባኤው፣ በኮሚቴዎች እና በምክር ቤት አባላት የሚመነጭ አጀንዳ በአፈ-ጉባኤው አማካኝነት ለአማካሪ ኮሚቴ ይቀርባል፡፡
 3. ማንኛውም በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚፈለግ የአማካሪ ኮሚቴው ስልጣን የሆነ ሞሽን ከምክር ቤቱ ስብሰባ ከሁለት ቀን በፊት በአፈ-ጉባኤው በኩል ለምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ በጽሑፍ ማስታወቂያ መቅረብ አለበት።
 4. አማካሪ ኮሚቴው የማስታወቂያ ሞሽኑ ስርዓትን ተከትሎ በአግባቡ የቀረበ መስሎ ከታየው ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ ሊያደርግ ይችላል።
 5. በአባላት መንጭቶ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚቀርብ የህግ ረቂቅ በጽሑፍ ሆኖ በአባሉ ፊርማ ተደግፎ በአፈ ጉባኤው በኩል ለአማካሪ ኮሚቴ መቅረብ አለበት።
 6. በኮሚቴ መንጭቶ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚቀርብ ረቂቅ ህግ በኮሚቴው ሊቀመንበር ተፈርሞ በአፈጉባኤው በኩል ለአማካሪ ኮሚቴ መቅረብ አለበት።
 7. በህግ ስልጣን በተሠጣቸው ሌሎች አባላት የመነጨ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚቀርብ ረቂቅ ህግ በተቋሙ የበላይ ኃላፊ ፊርማ ተደግፎ በአፈጉባኤው በኩል ለአማካሪ ኮሚቴ

መቅረብ አለበት።

 1. በፓርላማ ቡድን መንጭቶ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚቀርብ ረቂቅ ህግ በመሪው ወይም በተጠሪው ፊርማ ተደግፎ ለአማካሪ ኮሚቴ መቅረብ አለበት።
 2. በመንግስት መንጭቶ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ የሚቀርብ ረቂቅ ህግ በመንግስት ተጠሪ በኩል ለአማካሪ ኮሚቴ መቅረብ አለበት፡፡
 3. አፈጉባኤው በም/ቤቱ ደንብ መሠረት የተዘጋጀ ረቂቅ ህግ ሲደርሰው በቀጣዩ የም/ቤቱ ስብሰባ በአጀንዳነት እንዲቀረፅ ለአማካሪ ኮሚቴው ማቅረብ አለበት፡፡ ረቂቁ በደንቡ መሠረት ያልተዘጋጀ ከሆነ ችግሩን በመግለፅ ተስተካክሎ እንዲመጣ ለአቀረበው አካል ይመልሰዋል፡፡
 4. የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት አፀዳደቅ ሂደትን ለመወሰን በወጣው መመሪያ መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ይቀርባል፡፡
 5. ማንኛውም የቃል መልስ የሚፈልግ ጥያቄ የሚያቀርብ አባል በመመሪያ ቁጥር 3/2000 መሠረት ጥያቄውን ቢያንስ ከአስር ቀን በፊት ለአፈጉባኤው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፡፡
 6. ማንኛውም ረቂቅ አጀንዳ የሚያቀርብ ሰው የረቂቁን ቅጅ ከአማካሪ ኮሚቴው የስብሰባ እለት ከሁለት ቀን በፊት ለአፈ-ጉባኤው መላክ አለበት።

 አንቀጽ 11

 የተቀረፀ አጀንዳ ለም/ቤቱ ውይይት

 የሚቀርብበት ስርዓት

 1. አፈጉባኤው፤ በአማካሪ ኮሚቴው ስምምነት የተደረሠበት ወይም በራሱ የፀደቀ አጀንዳን እና ተያያዥ ሠነድ ለም/ቤቱ ጽ/ቤት ይልካል።
 2. የሚመለከተው የጽ/ቤቱ የስራ ክፍል በሚሰጠው ቅደም ተከተል መሠረት አጀንዳ ይቀርፃል፤ ከምክር ቤቱ የስብሰባ እለት ከ48 ሰዓት በፊት በማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲለጠፍ እና ከተያያዥ ሰነዶች ጋር ለአባላት እንዲሠራጭ ያደርጋል።
 3. የአጀንዳ ቅደም ተከተል በአፈጉባኤው ይወሰናል።
 4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 የተደነገገው ቢኖርም በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 9(6)መ መሠረት የአጀንዳ ቅደም ተከተል ማስተካከያ እንዲደረግ ወይም ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ሞሽን ቀርቦ በአባላት ከተደገፈ የቅደም ተከተል ማሻሻያ ሊደረግ ወይም አንድን አጀንዳ ወደሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ይችላል።
 5. ከላይ በአንቀጽ 11 ንዑስ አንቀፅ 4 መሠረት ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈ አጀንዳ ለምክር ቤቱ በሚቀርብበት እለት ከሌሎች አጀንዳዎች ቅድሚያ ሊያገኝ ይችላል።

ምዕራፍ ሶስት

 ልዩ ልዩ ድንጋጌ

 አንቀፅ 12

 የሌሎች መመሪያዎች ተፈፃሚነት

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ እና አሠራር በዚህ መመሪያ ውስጥ በተሸፈኑ (በተመለከቱ) ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

አ ንቀፅ 13

 መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ ከፀደቀበት ከሚያዚያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

ተሾመ ቶጋ /አምባሳደር/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አፈ-ጉባኤ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.