Rule Making Notice

የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤ ላኪ እና አከፋፋይ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር …../2013፤ ረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ – EFDA

Medicine and Medical device IEW control Directive በረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ

Source: የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤ ላኪ እና አከፋፋይ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር …../2013፤ ረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ – EFDA

በረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በምግብና መደኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 72 (2) መሰረት አዋጁን ለማስፈጸም መመሪያ የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ የፌዴራል መንግስት ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት በረቂቅ መመሪያ ላይ ህብረተሰቡ ሀሳብ እንዲሰጥ በጋዜጣ ጥሪ መደረግ እንደሚገባው የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 8 ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ባለስልጣኑ፡-

  1. የመድኃኒት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ ቁጥር …../2013፤
  2. የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤ ላኪ እና አከፋፋይ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር …../2013፤ እና
  3. የመድኃኒት የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር …../2013

 

የተመለከቱ ረቂቅ መመሪያዎች ያዘጋጀ በመሆኑ በረቂቆቹ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የረቂቆቹን ቅጂ ከባለስልጣኑ ድረ-ገጽ www.fmhaca.gov.et ወይም ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው የባለስልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ በመውሰድ እስከ የካቲት 20 ቀን 2013 ከቀኑ 9፡00 ድረስ በጽሑፍ ለባለስልጣኑ የህግ ክፍል ቢሮ ቁጥር 204 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ contactefda@efda.gov.et ወይም በፖስታ ቁ. 5681 እንድትልኩ በአክብሮት ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ ለበለጠ መረጃ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡”

 

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፡፡

Categories: Rule Making Notice

Tagged as: ,

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.