Rule Making Notice

የመድኃኒት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ ቁጥር …../2013፤ ረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ – EFDA

በረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪየኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በምግብና መደኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 72 (2) መሰረት አዋጁን ለማስፈጸም መመሪያ የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

Source: የመድኃኒት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ ቁጥር …../2013፤ ረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ – EFDA

በረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በምግብና መደኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 72 (2) መሰረት አዋጁን ለማስፈጸም መመሪያ የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ የፌዴራል መንግስት ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት በረቂቅ መመሪያ ላይ ህብረተሰቡ ሀሳብ እንዲሰጥ በጋዜጣ ጥሪ መደረግ እንደሚገባው የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 8 ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ባለስልጣኑ፡-

 1. የመድኃኒት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ ቁጥር …../2013፤
 2. የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤ ላኪ እና አከፋፋይ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር …../2013፤ እና
 3. የመድኃኒት የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር …../2013

 

የተመለከቱ ረቂቅ መመሪያዎች ያዘጋጀ በመሆኑ በረቂቆቹ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የረቂቆቹን ቅጂ ከባለስልጣኑ ድረ-ገጽ www.fmhaca.gov.et ወይም ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው የባለስልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ በመውሰድ እስከ የካቲት 20 ቀን 2013 ከቀኑ 9፡00 ድረስ በጽሑፍ ለባለስልጣኑ የህግ ክፍል ቢሮ ቁጥር 204 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ contactefda@efda.gov.et ወይም በፖስታ ቁ. 5681 እንድትልኩ በአክብሮት ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ ለበለጠ መረጃ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡”

 

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፡፡

የረቂቅ መመሪያው ቅጂ

የመደኃነት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ

2012

መግበያ

የመደኃነት አቅርቦትን ለማበረታታት መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኝ ሰሆን፤ የመደኃነት ጥራት፣ ደህንነት እና ፈዋሽነት የተጠበቀ እንዲሆን የተለያዩ የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፤

መደኃኒትን የማምረት፣ የማስመጣት፣ የማከፋፈል ወይም የመሸጥ ስራ ላይ የመሰማራት የማንኛውም ሰው መብት ቢሆንም፤ ይህንን ተግባሩን በህግና ስርዓት እንዲመራ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የምግብና መደኃነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2012 ወጥቶ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ቢሆንም፤

የመደኃኒት የመሸጫ ዋጋ የመወሰን የነጋዴው ነጻ መብት ቢሆንም መንግስት ዘርፉ እንዲበረታታ ከታክስ ነጻ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች የሚደረጉ ሲሆን፤ ከአምራች እስከ ሻጭ ባለው ሰንሰለት በዋጋ ላይ ተጽኖ የሚፈጥር ለውጥ ሳይኖር ምክንያተዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በየወቅቱ በመስተዋሉ፤

ምክንያታዊ የልሆነ ጭማሪን ለመቆጣጠር በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 26 ንኡስ አንቀጽ (6) በአምራች ወይም በአስመጪ የችርቻሮ ዋጋ ያልተለጠፈበትን መደኃኒት መሸጥ የተከለከለ መሆነ የተደነገገ በመሆኑ፤

በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 53 ንኡስ አንቀጽ (7) የመደኃኒት አምራች ወይም አስመጪ የመደኃኒቱን የችርቻሮ ዋጋ በምርቱ ማሸጊያ ላይ መለጠፍ እንዳለባቸው የሚደነግግና ይህም ተግባራዊ የሚሆነው አዋጁ ከወጣ ከአስራ ስምንት ወራት በኋላ ስለመሆኑ በአንቀጽ 74 ንኡስ አንቀጽ (2) የሚደነግግ በመሆኑ፤

የመደኃኒቱን የችርቻሮ ዋጋ በምርቱ ማሸጊያ ላይ ተግባራዊ ስለመደረግበት አግባብ ግልጽ ስርዓት ማስቀመጥ በማስፈለጉ፤

የኢትዮጵያ የምግብና መደኃኒት ባለስልጣን በምግብና መደኃነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2012 አንቀጽ 71 ንኡስ አንቀጽ (2) መሰረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

 

 1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የመደኃነት የችርቻሮ ዋጋ አቀማመጥ መመሪያ ቁጥር…/2012” ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

 1. ትርጉም
 • “አዋጅ” ማለት የኢትዮጵያ ምግብና መደኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 ነው፤
 • “ችርቻሮ” ማለት መደኃኒት ለተጠቃሚ የሚሸጥበት ሁኔታ ነው፤
 • “የችርቻሮ ዋጋ” ማለት መደኃኒት ለተጠቃሚ የሚሸጥበት ዋጋ ነው፤
 • በአዋጁ ውስጥ ትርጉም የተሰጣቸውና በዚህ መመሪየ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትና ሐረጋት በአዋጁ የተሰጣቸው ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡
 • ሰው” ማለት በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ወይይ የተፈጥሮ ሰው ነው፤
 • ባለስልጣን ማለት የኢትዮጵያ የምግብና መደኃኒት ባለስልጣን ነው፤
 • የወንድ የጾታ አገላለጽ ሴትንም ያጠቃልላል፡፡
 1. የተፈጻሚነት ወሰን
 • ይህ መመሪያ በውጭ አገር በማምረት ወይም የተመረተ መደኃኒት ወደ አገር ውስጥ በሚያስመጡ እና በአገር ውስጥ በሚያመርቱ የመደኃኒት አምራቾች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
 • የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) ቢኖርም በልዩ ሁኔታ በሚገቡ እና በሚሰራጩ መደኃኒቶች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
 1. የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋን የማሳተም ኃላፊነት
 • ማንኛውም የመደኃኒት አምራች መደኃኒቱን ለጅምላ አከፋፋይ ወይም በህግ በሚፈቀድ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋም ከማስተላለፉ በፊት በመደኃኒቱ ማሸጊያ ላይ በኢትዮጵያ ብር የመደኃኒቱን በችርቻሮ የመሸጫ ከፍተኛ ዋጋ ማተም ወይም መለጠፍ አለበት፡፡
 • በንኡስ አንቀጽ (1) የተገለጸው ቢኖርም መደኃኒቱ በውጭ የተመረተ እንደሆነና አስመጨውና አምራቹ የመደኃኒቱ የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋ በአስመጪው በማሸጊያው ላይ እንዲታተም ስምምነት ያደረጉ እንደሆነ አስመጪ ዋጋውን በመደኃኒቱ ማሸጊያ ላይ ማሳተም አለበት፡፡
 • በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (2) የተደረገ ስምምነት ባለስልጣኑ እንዲያውቀው መደረግ አለበት፡፡
 1. ዋጋ ስለሚታተምበት ጊዜ
 • ማንኛውም መደኃኒት ገበያ ላይ ከመቅረቡ በፊት በማሸጊያው ላይ የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋው የተለጠፈበት መሆን አለበት፡፡
 • በአንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ (1) መሰረት ዋጋ የመለጠፍ ኃላፊነት የአምራቹ በሚሆንበት ጊዜ የመደኃኒቱ ማሸጊያ በሚዘጋጅበት አብሮ በማሳተም ወይም መደኃኒቱ ከታሸገ በኋላ ለአስመጪ ወይም ጅምላ አከፋፋይ ወይም ለአገልግሎት ሰጪ ተቋም ከመተላለፉ በፊት የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋ በመደኃኒቱ ማሸጊያ ላይ መታተም አለበት፡፡
 • በአንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ (2) መሰረት ዋጋ የመለጠፍ ኃላፊነት የአስመጪ ሲሆን፤ መደኃኒቱን ከምራቹ በሚቀበልበት ወቅት ወይም ለሚረከቡት አካላት ከማስተላለፉ በፊት የመደኃኒቱን የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋ መለጠፍ አለበት፡፡
 • ጅምላ አከፋፋይ ወይም ቸርቻሪ የመደኃኒትን የችርቻሮ ከፍተኛ ዋጋ ለማሳተም አይችሉም፡፡
 1. የዋጋ ለውጥ መኖር
 • በአምራች ወይም በአስመጪ ከታተመው መደኃኒትን በችርቻሮ የመሸጫ ከፍተኛ ዋጋ በላይ መሸጥ የተከለከለ ነው፡፡
 • የመደኃኒት በችርቻሮ የመሸጫ ከፍተኛ ዋጋ በታች ቀንሶ ዋጋ ለመሸጥ ይቻላል፡፡
 • የመደኃኒት በችርቻሮ የመሸጫ ከፍተኛ ዋጋ ከታተመ በኋላ የማምረቻ ወይም የማጓጓዣ ዋጋ በመጨመሩ የዋጋ ለውጥ ማድረግ ያስፈለገ እንደሆነ የተፈጠረውን ልዩነት ለባለስልጣኑ በማሳወቅ ማሻሻያ ለማድረግ ይቻላል፡፡
 • የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (3) ኢኮኖሚያዊ ተጽኖው ከመፈጠሩ በፊት በችርቻሮ ገበያ ውስጥ በተሰራጨ መደኃኒት ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
 1. የዋጋ ህትመት ሁኔታ
 • በመደኃኒት የችርቻሮ መሸጫ ከፍተኛ ዋጋ በመደኃነቱ ማሸጊያ ላይ መታተም ያለበት በግልጽ በሚታይ፣ በማይለቅ እና በመደበኛ ሁኔታ መደኃኒቱ ሲከፈት ሊጠፋ ወይም ሊቀደድ በማይችልበት ሁኔታ መሆን አለበት፡፡
 • የመደኃኒቱ ማሸጊያ ብልቃጥ፣ ፕላስቲክ ወይም መሰል ቁስ እንደሆነ የችርቻሮ ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋ የሚታተመው በራሳቸው ላይ ይሆናል፡፡ ሆኖም በነጠላ ማሸጊያ ካርቶን ያለው እንደሆነ በካርቶኑ ላይ ለማተም ይቻላል፡፡
 1. መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከ…ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

Categories: Rule Making Notice

Tagged as: ,

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.