Cassation Decisions

ተተኪ ወራሽነት- የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም

የሟች ልጆች ቀድመው ከሞቱና ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ትተው ከሆነ ተወላጆቹ ወሊጆቻቸውን ተክተው ሟችን መውረስ

ሟች ልጆች የሌሉት ከሆነ እናትና አባት ሁለተኛ ደረጃ ወራሾች እንደሚሆኑና አባት ወይም እናት ቀድመው ከሞቱም የእነሱን ፈንታ ልጆቻቸው ወይም ወደታች የሚቆጠሩ ተወሊጆች እነሱን ተክተው እንደሚወርሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 843፤ 844/2 ተመልክቷል፡፡ በአባት ወይም በእናት በኩል ወደታች የሚቆጠር ከሌለ ውርሱ በሙሉ በሌላው መስመር ላለ ወራሽ እንደሚተላለፍ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 844/3 ያመለክታል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 47957 ቅጽ 10[1]

ተተኪ ወራሽነት የተፈጻሚነት ወሰን ወደታች በሚቆጠሩ ተወሊጆች እንጂ ወደ ጎን በሚቆጠር ዝምድና ትስስር አይደለም፡፡

የሟች አባትና እናት ሟችን ቀድመው ከሞቱ የእነርሱ ተወላጆች ማለትም የሟች ወንድምና እህት ወይም የወንድሞቹና የእህቶቹ ተወላጆች እናትና አባቱን በመተካት በሟች ውርስ እንደሚካፈሉ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 843 እና 844 ድንጋጌዎች ይዘት የሚያሳየን ጉዳይ ነው፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 844(3) ድንጋጌ ከሟች እናት እና አባት በአንዱ መስመር ወራሽ ቢታጣ የሟች ውርስ ወደ ሌላው መስመር በሙሉ ሊተላለፍ እንደሚችል ደንግጓል።

ሰ/መ/ቁ 45587 ቅጽ 10[2]

የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 842/3/ ስር እንደተመለከተው የሟች ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ሲሆኑ ልጆች ቀድመው ከሞቱና ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ትተው ከሆነ ተወላጆቹ ወላጆቻውን ተክተው ሟችን እንደሚወርሱ ያመልክታል፡፡ የተተኪ ወራሽነት የተፈፃሚነት ወሰን ወደ ታች የሚቆጥሩ ተወሊጆች እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

ሰ/መ/ቁ/ 110040 ቅጽ 20[3]


[1] አመልካች እነአቶ ተፈሪ ሐጎስ /3 ሰዎች/ እና ተጠሪ ተጠሪ አቶ ተስፋይ ገ/እግዚአብሔር ጥር 5 ቀን 2002

[2] አመልካች እነ ወ/ሮ አተረፈች ዘውዴ እና ተጠሪአቶ ዘውዴ ወሰኔ  ሐምሌ 29 ቀን 2002 ዓ.ም

[3] አመልካቾች እነ ወ/ሮ እሴተማርያም አክሎግ/3 ሰዎች/ (ተጠሪ የለም) የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.