Property Law

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ2005 ዓ.ም የ20-80 እና 40-60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት የኅብረት ሥራ ማህበር አደራጅቶ ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1-2013

አውጭው ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ታህሳስ 2013 ዓ.ም.

1. መግቢያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና በተጠሪ ተቋማት በ2005 ዓ.ም በተደረገው የ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ወቅት ተመዝግቦ ከሚጠባበቀው ፈቃደኛ የሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ አቅም ያላቸውን በመኖሪያ ቤት የኅብረት ሥራ ማኅበር በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረግና የቤት ፈላጊውን ችግር መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ይህን መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጓል፤

ይህም ዜጎችን በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ተደራጅተው የቤት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንዲችሉ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀመጠውን መመዘኛ ሊያሟሉ የሚችሉትን ቤት ፈላጊዎች ግልፅ፣ ተደራሽ፣ አሣታፊ፣ ያልተገባ ተጠቃሚነት በመከላከል ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራርና የአደረጃጀት ስርአት በመፍጠር የሚሰራ ይሆናል:: ይህን አላማ ተፈጻሚ ለማድረግም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፣ ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 3 (ሠ) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.