Site icon Ethiopian Legal Brief

ቅጣትን ስለማክበድና ስለማቅለል

ቅጣትን ስለማክበድና ስለማቅለል

አንድ ፍርድ ቤት ቅጣትን በሚወስንበት ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሕጉ የደነገጋቸው የማቅለያ ወይም የማክበጃ ምክንያቶች አሉ፡፡

4.1. የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

እነዚህ ምክንያቶች በጠቅላላና በልዩ ሁኔታ ቅጣት የሚያከብዱ ምክንያቶች ተብለው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡

ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

በልዩ ሁኔታ ቅጣትን ለማክበድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተብለው በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተጠቀሱት ምክንያቶች ተደራራቢወንጀሎች እና ደጋጋሚነት /ደጋጋሚ ወንጀለኛነት/ ናቸው፡፡

     የወንጀሎች መደራረብ አለ የሚባለው ምን ዓይነት ሁኔታዎች በሚኖሩበት ጊዜ እንደሆነ አንዲሁም አንድ ሰው ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው በወንጀል ሕጋችን መሠረት የሚባለው ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟሉ እንደሆነ እና የቅጣት አወሳሰኑ በቀድሞው ሕግም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ ምን እንደሚመስል “ደጋጋሚነት፣ ተደራራቢ ወንጀሎች እና የቅጣት አወሳሰን” በሚለው የዚህ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የቀረበ በመሆኑ እዚህ ላይ በድጋሚ መግለፁ አላስፈላጊ ነው፡፡ ከልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች አንጻር ሊሰመር የሚገባው ነጥብ ቢኖር እነዚህ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ አንድ ሰው ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘበት በሕጉ ልዩ ክፍል ውስጥ በተደነገገው የቅጣት ጣራ ሳይገደብ ቅጣት በአጥፊው ላይ ሊወስን የሚችል መሆኑ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘበት የሕጉ ልዩ ክፍል ድንጋጌ ላይ ከተጠቀሰው ቅጣት ወለል በታች ወይም ደግም ከተደነገገው ቅጣት ጣራ በላይ ሊቀጣ አይችልም፡፡ ይሁን እንጅ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ይህ ለመደበኛ ሁኔታ አግባብነት ያለው መርህ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ 

4.1.2.  ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ  ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

     ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን አስመለክቶ በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 81 ድንጋጌ ላይ ተመልክተው የነበሩት ጉዳዮች የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎባቸው የአዲሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 84 ድንጋጌ ሆነው ተካተዋል፡፡ ጠቅላላ የቅጣት የማክበጃ ምክንያቶች የሚባሉት ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመው በጨካኝነት፣ በከሀዲነት፣ በወስላታነት፣ በወራዳነት፣ መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኝነት፣ በጥላቻ፣ በክፋት የሆነ እንደሆነ፣ ወንጀለኛው ወንጀል ማድረግን ሙያ ወይም ልማድ አድርጎ ይዞ እንደሆነ፣ የወንጀሉ አፈጻጸም ዘዴ፣ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ፣ ቦታና የአፈጻጸሙ አኳኋን የወንጀለኛውን አደገኛነት የሚያሳይ የሆነ እንደሆነ፣ ወንጀሉ የተፈፀመው ወንጀል ለመፈፀም ስምምነት ባደረጉ ሰዎች ወይም ቡድኖች ሲሆን፣ ወንጀሉ የተፈፀመው በተለያዬ ምክንያት ጥበቃ ወይም እንክብካቤ በሚሹ ሰዎች ላይ ሲሆን፣ ወ.ዘ.ተ. ነው፡፡

    በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተደረጉትን መሻሻሎች ስንመለከት በወንጀል ሕጉ ሐተታ ዘምክንያት ላይ በትክክል እንደተገለፀው መሠረታዊ የሚባሉ አይደሉም፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል “ስግብግብነት” የሚል ቀደም ሲል ያልነበረ ተጨምሯል፣ “ከወንበዴዎች ጋር ማህበርተኛ በመሆን” ወንጀሉ ተፈፅሞ ከሆነ ይል የነበረው “ወንጀል ለመስራት ከተቋቋመ ቡድን ጋር በመስማማት” በሚል ተተክቷል፣ ወንጀሉ የተፈፀመው “ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የሚቆጠር ወላጅ ከሆነ ሰው ላይ ከሆነ” ይል የነበረው “በቅርብ ዘመዱ” ላይ የሆነ እንደሆነ በሚል ተተክቷል፡፡ “በሕገ መንግስት በተቋቋመ ባለሥልጣን” ላይ እንደሆነ ይል የነበረው “በሕግ በተቋቋመ ባለሥልጣን”ላይ እንደሆነ በሚል ተተክቷል፡፡ ወንጀሉ “በሀይማኖት ባለሥልጣን” ላይ የተፈጸመ እንደሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ መሠረት ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ተደርጎ ይቆጠር የነበረ ሲሆን ከአዲሱ የወንጀል ሕግ ላይ ግን ተሰርዟል፡፡

    ከጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች አንጻር ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ሦስት የሚሆኑ ነጥቦች አሉ፡፡ እነርሱም፡-

  1. ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ተብለው በሕጉ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በሕጉ ልዩ ክፍል ለአንድ ለሆነ ወንጀል ማቋቋሚያ ወይም ለቅጣት ማክበጃ ምክንያት ተደርገው በተመለከቱ ጊዜ የወንጀሉን ቅጣት ዳግመኛ ለማክበድ ተፈፃሚ አይሆኑም (አንቀጽ 84(2))፡፡ ማለትም አንድ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም ዳግመኛ ቅጣቱን ሊያከብድ አይችልም፡፡ ለምሳሌ “ጨካኝነት” ጠቅላላ ቅጣትን ከሚያከብዱ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ይህ ቃል በሕጉ ልዩ ክፍል ወንጀሉን ከሚያቋቋሙት ሁኔታዎች አንዱ ሆኖ ወንጀለኛው በዚህ ድንጋጌ መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ቅጣት በሚወሰንበት ጊዜ በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተመለከተው “ጨካኝነት” ዳግመኛ ግምት ውስጥ ገብቶ ቅጣቱ ሊከብድበት አይችልም፡፡

     ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት በሚኖርበት ጊዜ ያለውን የቅጣት አወሳሰን በተመለከተ የቅጣት ማክበጃ ጠቅላላምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ የምክንያቶችን ዓይነትና ብዛት፣ እንዲሁም የወንጀሉን ከባድነት /የቀድሞው ሕግ ትልቅነት ይል ነበር/ ግምት ውስጥ በማስገባት ለወንጀሉ በሕጉ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ የቅጣት ጣራ ሳያልፍ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ማክበድ ይችላል (አንቀጽ 183)፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ሰው በፈፀመው አንድ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቶ ቅጣቱ በሚወሰንብት ወቅት የቱንም ያህል ብዛት ያላቸው ወይም ክብደታቸው ከፍተኛ የሆነ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ቢኖሩም በአጥፊው ላይ የሚወሰነው ቅጣት ተከሳሹ ጥፋተኛ በተባለበት አንቀጽ ከተደነገገው ከፍተኛ የቅጣት ጣራ ሊያልፍ አይችልም፡፡

4.2. የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችንም እንዲሁ በሁለት ከፍሎ ማየት ይችላል፡፡

  1. ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች፣እና

2. ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች

ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

                                    /አንቀጽ 83፣ ቁጥር 8ዐ/

በልዩ ሁኔታ ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተብለው በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 80 እንዲሁም በአዲሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 83 ላይ በግልፅ የተጠቀሱት ምክንያቶች ዝምድናና የጠበቀ ወዳጅነት ቢሆኑም በሕጉ ልዩ ክፍል ውስጥ ፍርድ ቤቱ በመሠለው ቅጣት ማቅለል ይችላል የተባለባቸው ምክንያቶች ሁሉ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ናቸው (አንቀጽ 83(1))፡፡

የወንጀል ሕጉ ዝምድና ለአንዳንድ ዓይነት ወንጀሎች እንደ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ተደርጎ እንደሚወሰድ የደነገገ ቢሆንም የዝምድናውን ደረጃ በግልፅ አላመለከተም፡፡ ነገር ግን ዝምድና አለ የሚባለው መቼ ነው የሚለውን በተመለከተ ሕግ አውጭው ያለውን አቋም ለመረዳት በቤተሰብ ሕጉ ላይ የተደነገገው የዝምድና ግንኙነት መመዘኛ ለዚህ ጉዳይ ሊያገለግል ይችላል፡፡

     “የጠበቀ ወዳጅነት” የሚለውም እንደዚሁ በሕጉ ትርጉም ያልተሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ግንኙነቱ በቂ ምክንያት ተደርጐ ሊቆጠር የሚችል መሆን አለመሆኑን እንደሚወስን መረዳት ይቻላል፡፡

ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ያለውን የቅጣት አወሳሰን በተመለከተ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 83(2) እና 122 ላይ እንደተመለከተው የወንጀለኛው ጥፋት በጣም ከባድ ካልሆነና የዝምድና ወይም የወዳጅነት ትስስሩ /ግንኙነቱ/ እጅግ ጥብቅ ከሆነ ወንጀለኛውን በማስጠንቀቅ ወይም በወቀሳ ብቻ ፍርድ ቤቱ ሊያልፈው ይችላል ፡፡ ከዚህ ውጭ ባሉ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ግን ፍርድ ቤቱ በመሠለው ቅጣትን ማቅለል የሚችል ቢሆንም የሚወሰነው ቅጣት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ለየቅጣቱ ዓይነት ከተደነገገው መነሻ ቅጣት ዝቅ ሊል አይችልም /የቀድሞው ቁጥር 185፣አዲሱ አንቀጽ 18ዐ/፡፡ ይህም ማለት፡-

4.2.2. ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች እና የቅጣት አወሳሰን

/የድሮው 79፣አዲሱ 82

ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን አስመለክቶ በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 79 ድንጋጌ ላይ ተመልክተው የነበሩት ጉዳዮች የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎባቸው የአዲሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 82 ድንጋጌ ሆነው ተካተዋል፡፡ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች የሚባሉት የወንጀለኛው የዘወትር ጠባይ መልካም ሆኖ ያጠፋው በዕውቀት ማነስ፣ ባለማወቅ፣ በየዋህነት፣ ወይም ባለታሰበ ድንገተኛ አጋጣሚ፣ ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈፀመው በተከበረና በግል ጥቅም ላይ ባልተመሰረተ ምክንያት መሆን፣ ወይም ከፍተኛ ቁሳዊ እጦት ወይም የሕሊና ስቃይ ስለደረሰበት መሆን፣ወ.ዘ.ተ. ነው፡፡

በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተደረጉትን መሻሻሎች ስንመለከት መሠረታዊ የሚባሉ አይደሉም ማለትም በቀድሞው ሕግ ላይ የተመለከቱት የተወሰነ ማሻሻያ ብቻ ነው የተደረገባቸው፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል “እጅን ለፍርድ ባለሥልጣን ከሰጠ በቅጣት ማቅለያነት እንደሚያዝለት የቀድሞው የወንጀል ሕግ ተገልፆ የነበረው ሰፋ ተደርጎ “እራሱን ለፍትሕ አካላት ካቀረበ” በሚል የተተካ ሲሆን ወንጀለኛው ተከስሶ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ በክስ ማመልከቻው ላይ የተመለከተውን የወንጀል ዝርዝር በሙሉ ያመነ እንደሆነ በቅጣት ማቅለያነት ይያዝለታል የሚል አዲስ ሀረግ ተጨምሮበታል፡፡

ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተብለው በሕጉ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በሕጉ ልዩ ክፍል በማቅለያነት በተመለከቱ ጊዜ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎች የወንጀሉን ቅጣት ለማቅለል ዳግመኛ ተፈፃሚ አይሆኑም፡፡ በዚህም መሠረት አንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም ዳግመኛ ቅጣትን ሊያቀል አይችልም ማለት ነው፡፡

      እንዲሁም በሕጉ በግልፅ ከተመለከቱት ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ውጭ ፍርድ ቤቶች ሌሎች ሁኔታዎችንም የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች አድርገው ሊቆጥሩ ይችላሉ /አንቀጽ 86/፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን፡-

  1. ለምን በቂ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አድርጐ እንደተቀበለው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ መግለፅ አለበት፣
    1. ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን እንጂ ልዩ የቅጣት ማቅለያ   ምክንያቶችን ፍርድ ቤቱ ሊፈጥር አይችልም፡፡

      ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ያለውን የቅጣት አወሳሰን በተመለከተበወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 184 እንዲሁም በአዲሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 179 ላይ እንደተመለከተው ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ እንደ ነገሩ ሁኔታ የቅጣቱ ዓይነት ወይም የቅጣቱ መጠን ይቀየራል፡፡ ለምሳሌ፡-

ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ይወስናል፡፡

4.3. የልዩ ልዩ ቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ምክንያቶች መደራረብ

       ቅጣትን የሚያቃልሉና የሚያከብዱ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች በአንድነት ሲገኙ ቅጣት የሚወሰነው እንዴት ነው የሚለውን በተመለከተ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 189 ስር በምን መልኩ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንደሚወስን ተመልክተው እናገኛቸዋለን፡፡ ይኸውም፡-

  1. የተደራረቡት ቅጣትን የሚያከብዱና የሚያቃልሉ ጠቅላላ ምክንያቶች ከሆኑ ፍርድ ቤቱ፣
    1. አስቀድሞ የሚያከብዱ ጠቅላላ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ አስገብቶ ቅጣቱን ያከብዳል፣
    1. በመቀጠል የሚያቃልሉትን ጠቅላላ ምክንያቶች መሠረት አድርጐ ቅጣቱን ይቀንሳል/አንቀጽ 189/1/፣ቁጥር 84/

            2. የተደራረቡት ደጋጋሚ ወንጀለኛነት እና ተደራራቢ ወንጀሎች ከሆኑ /ማለትም ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በአንድነት ከተገኙ/ ፍርድ ቤቱ፡-

Exit mobile version