ቸልተኝነት እና አስተዋዩ ውሻ

ከውል ውጪ በሚደርስ ኃላፊነት ህግ ውስጥ የቸልተኝነት ጥያቄ ከተነሳ ምላሹ ለብዙ ፍርድ ቤቶች ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ በብዙ የህግ ስርዓቶች ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው የቸልተኝነት መለኪያ “የአንድ አስተዋይ ሰው ሚዛን” ሲሆን ይህም አንድ አስተዋይ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን ኖሮ ምን እንደሚያደርግ በመላምታዊ ፍሬ ነገር ላይ ተመስርቶ ማሰላሰልና ድምዳሜ ላይ መድረስን ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ ቸልተኝነትን በአንድ አስተዋይ ሰው እይታ መዝኖ መወሰን አስቸጋሪ ከሆነ ይህን መለኪያ ለአንድ አስተዋይ ውሻ ተፈፃሚ ማድረግ ደግሞ በጣም ፈታኝ ብቻ ሳይሆን አስገራሚም ጭምር ነው፡፡

በአሜሪካም ኢሊዮኒስ ግዛት በኪርካም እና ዊል (Kirkham Vs. Will) መካከል በታየ አንድ የይግባኝ ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በጉዳዩ የተነሳው ጭብጭ የአንድ አስተዋይ ውሻ መለኪያን በመጠቀም እልባት ሰጥቶበታል፡፡ ክሱ የተጀመረው “የተከሳሽ ውሻ በንክሻ ላደረሰብኝ ጉዳት የውሻው ባለቤት የሆነው ተከሳሽ ካሳ ሊከፍለኝ ይገባል፡፡” በሚል ከሳሽ ባቀረበው ክስ ሲሆን ተከሳሹም በበኩሉ ከሳሽ የተነከሰው ውሻውን በመተናኮሉ ስለሆነ በራሱ ጥፋት ለደረሰበት ጉዳት ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡

ክሱ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ ከተደረገ በኋላ በይግባኝ ክርክሩ ላይ በዋነኛነት የተነሳው ጭብጥ “መተናኮል አለ ወይስ የለም?” የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ ውሳኔውን የሰጡት ዳኛ ይህንን ጭብጥ ለመወሰን እንደመመዘኛ ወይም መስፈርት የተጠቀሙት የተለመደውን የአስተዋይ ሰው ሚዛን ሳይሆን የአንድ አስተዋይ ውሻ መለኪያ ነበር፡ በዚህ ሚዛን ወይም መለኪያ መሠረት መተናኮል አለ ወይስ የለም? የሚለውን ጥያቄ ለመወሰን በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ‘አንድ አስተዋይ ውሻ’ ከሳሽ ካሳየው እንቅስቃሴ አንጻር ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጣል? የሚል መላምታዊ ጥያቄ አንስቶ ድምዳሜ ላይ መድረስን ይጠይቃል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተፈጻሚ ባደረግው መለኪያ መሰረት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል፡፡

የወንጀል ህግ አንቀጽ 23 -የዐቃቤ ህግ የወንጀል ተጠያቂነት (ምርጥ የሰበር ውሳኔ)

የሰበር መ/ቁ 40687[1]

ሀምሌ 19 ቀን 2002 ዓ.ም

 

ዳኞች፡ ሐጎስ ወልዱ

                  ሂሩት መለሰ

                  ብርሀኑ አመነው

                  አልማው ወሌ

                  ዓሊ መሐመድ

አመልካች፡ አቶ ዮሐንስ ወልደገብኤል – አልቀረቡም

ተጠሪ፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን – አልቀረቡም

                መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

                ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 42486 መስከረም 29 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 33771 ሰኔ 27 ቀን 2001 ዓ.ም የከፍተኛውን ፍርድ ቤት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በማፅናት የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአመልካችና በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳሽ በነበረው አቶ ወርቁ በረደድ ላይ ጥር 16 ቀን 1998 ዓ.ም ባቀረበው የወንጀል ክስ አመልካችን ሁለት የወንጀል ክስ አቅርቦባቸው የነበረ መሆኑን መዝገቡ ያሣያል፡፡ ተጠሪ አመልካችና በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ ወርቁ በረደድ በአዋጅ ቁጥር 214/74 አንቀፅ 23 ንዑስ አንቀፅ 1(ሀ)(ለ) እና 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ከፍትህ ሚኒስትር ከተሰጣቸው ውክልና ውጭ በኤግዚቢትነት የተያዘው እና በማስረጃነት ለፍርድ ቤቱ መቅረብ የሚገባውን ወርቅ እንዲሰጥ አስተያየት በመስጠት ወርቁ ከተሸጠ በኋላ በኤግዚቢትነት ያለ አስመስለው በማስረጃ ዝርዝር በመጥቀስ በስልጣን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ያቀረበውን ሁለተኛ የወንጀል ክስ የተጠሪ የሰውና የፅሑፍ ማስረጃዎች እንደ ክሱ አቀራረብ ያላስረዱባቸው መሆኑን በመግለፅ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ውሣኔ የሰጠበት በመሆኑ በሰበር የመከራከሪያ ጭብጥ ሆኖ አልተያዘም፡፡ Continue reading የወንጀል ህግ አንቀጽ 23 -የዐቃቤ ህግ የወንጀል ተጠያቂነት (ምርጥ የሰበር ውሳኔ)

Saudi Arabia detains Mohammad al-Amoudiin in anti-corruption probe

DUBAI (Reuters) – Saudi Arabia detained 11 princes, four current ministers and tens of former ministers in a probe by a new anti-corruption body headed by Crown Prince Mohammed bin Salman, Saudi-owned Al Arabiya television reported.

According to a senior Saudi official who declined to be identified under briefing rules, those detained include:

– Prince Alwaleed bin Talal, chairman of Kingdom Holding 4280.SE

– Prince Miteb bin Abdullah, minister of the National Guard

– Prince Turki bin Abdullah, former governor of Riyadh province

– Khalid al-Tuwaijri, former chief of the Royal Court

– Adel Fakeih, Minister of Economy and Planning

– Ibrahim al-Assaf, former finance minister

– Abdullah al-Sultan, commander of the Saudi navy

– Bakr bin Laden, chairman of Saudi Binladin Group

– Mohammad al-Tobaishi, former head of protocol at the Royal Court

– Amr al-Dabbagh, former governor of Saudi Arabian General Investment Authority

– Alwaleed al-Ibrahim, owner of television network MBC

– Khalid al-Mulheim, former director-general at Saudi Arabian Airlines

– Saoud al-Daweesh , former chief executive of Saudi Telecom 7010.SE

– Prince Turki bin Nasser, former head of the Presidency of Meteorology and Environment

– Prince Fahad bin Abdullah bin Mohammad al-Saud, former deputy defence minister

– Saleh Kamel, businessman

– Mohammad al-Amoudi, businessman

Reporting by Rania El Gamal; Editing by Andrew Torchia and Paul Tait