የሰነድና የሰው ማስረጃ መጣረስ ከውል ሕግ አንጻር

Question & AnswerCategory: Questionsየሰነድና የሰው ማስረጃ መጣረስ ከውል ሕግ አንጻር
Suraphia asked 2 weeks ago

ጉዳዩ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ለመከላከል ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ የሚያስረዳውና የሚደግፈው የከሳሽን ጥያቄ ሕጋዊነት ወይም ክሱን ከሆነ ለምሳሌ የሰነድ ማስረጃው ውል ሆኖ  ውሉ ደግሞ አስቀድሞ ከከሳሽ ክስ ጋር በሰነድ ማስረጃነት የተያያዘ ቢሆንና ተከሳሽ ከውሉ ዝርዝር ስምምነቶች ውጪ የሆነን ነገር ወይም በአጠቃላይ ከውሉ በተቃራኒ የሚያስረዱለትን የሰው ምስክሮች  አቅርቦ ቢያሰማና ይህ የማስረጃ መጣረስ በፍርድ ቤቱ ቢታለፍ ድርጊቱ መሰረታዊ የህግ ስሕተት ነው ወይስ አይደለም? ከዚህ በተጨማሪም የሰነድ ማስረጃው (ውሉ) ያስረዳውን ጭብጥ የሚቃረን የሰው ምስክር ቢሰማ በሕግ ፊት/በዳኝነት ሒደቱ ተቀባይነት የሚኖረው የትኛው ነው?  እንዲሁም በፍ/ሕግ ቁጥር 2003 ፣ 2005 እና 2006 (2) መሰረት ውሉ በቂ ማስረጃ በመሆኑ የሰው ምስክርስ ሊሰማ የሚችልበት የሕግ አግባብ አለ’ንዴ? በአጠቃላይ የሰነድና የሰው ማስረጃ መጣራስ በፍርድ ሂደት እንዴት ይታያል? በፍትሐብሔር በተለይም በውል ክርክር ከሰነድና ከሰው ማስረጃ በፍርድ ሒደት ውስጥ ሚዛን የሚደፋው የትኛው ነው? በጣም አመሰግናለው!