የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 344(1)'ን ሕጋዊ ሂደት በተመለከተ

Question & AnswerCategory: Questionsየፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 344(1)'ን ሕጋዊ ሂደት በተመለከተ
Suraphia asked 3 weeks ago

ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሲሆን፤ የአሰሪው መስሪያ ቤት በይግባኝ ባዮች (ሰራተኞቹ) ላይ የሰጠው ውሳኔ በፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሔር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ፀንቶ በሰበር ችሎት የተሻረ እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት ለፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት የተመለሰ ነው፤ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱም ማስረጃ ከተቀበለ እና በፅሑፍ ካከራከረን በኋላ የመሰለውን ወስኗል በመሆኑም ይግባኝ ባዮች በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 344(1) መሰረት የአስተዳደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ማመልከቻ ማስገባት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ስላላወቅን ሕጋዊ ሂደቱን ታመላክቱን ዘንድ በማክበር አንጠይቃለን፡፡